Translate

Sunday, October 18, 2015

“ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ ፅሁፎች በኢትዮጵያ ከተሞች እየተሰራጩ ነው

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ
“ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ እና ሌሎች ፅሁፎች በአርባ ምንጭ ከተማ በዋና ዋና ቦታዎች ላይ በብዛት ተለጥፈው ታዩ፡፡
Patriotic Ginbot7 flyers distributed in Ethiopian cities
ጠንከር ያለ የፀረ-ህወሓት ህዝባዊ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ የአርባ ምንጭ ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ጀግኖች የአርባ ምንጭ ወጣቶች በከተማዋ ውስጥ ተደራጅተው ከፍተኛና ያልተቋረጠ የነፃነት ተጋድሎ በማድረግ አንድነትንና ዴሞክራሲን ለማምጣት ደጋግመው የህይወት ዋጋ ሲከፍሉ ከመቆየታቸውም ባሻገር ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለየ ሁኔታ በረሃ እየወረዱ የትጥቅ ትግሉን መቀላቀላቸውን አሁንም በአስደማሚ ሁኔታ ቀጥለውበታል፡፡ ከአንድ ሰፈር ብቻ ከ15 በላይ ወጣቶች አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለው በከፍተኛ እልህ፣ ሞራል እና ወኔ በትግል ላይ ይገኛሉ፡፡

በበረሃ በእሳት በከተማ በእምቢተኝነት እየተፋለሙ ህወሓትን አላስቆም አላስቀምጥ ያሉት እነዚህ ጀግና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የአርባ ምንጭ ወጣቶች ከትናትና በፊት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም “ድል ለአርበኞች ግንቦት 7!” “ሞት ለወያኔ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፈሩባቸው ሰፋፊ ወረቀቶች እና የግድግዳ ላይ ፅሁፎች አርባ ምንጭን ከፍነዋታል፡፡
ድል ፋና ቀበሌ፣ መናሃሪያ፣ ስታድየም፣ ወደ ማረሚያ ቤት የሚወስደው ጎዳና፣ የከተማዋ መግቢያና መውጫ ድልድዮች… መፈክሮች ከተለጠፉባቸው ቦታዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ይህ የአርባ ምንጭ ህዝብ የትግል መንፈስ ከፍታ ያስደነገጣቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ደህንነቶች እንደለመዱት ያገኙትን ወጣት ሁሉ እያፈሱ ወደ ወህኒ ማጋዛቸውን ተያይዘውት ይገኛሉ፡፡
የህወሓት ደህንነቶች ከወጣቶቹ አፈሳ ጎን ለጎን በስብሰባ ከመጠመዳቸው በተጨማሪ ወደ ገጠርም እየወረዱ “የሽብር ወረቀት ተበትኗል በጃችሁ ቢገባ እንዳታነቡት…” በማለት ለገበሬው ማህበረሰብም ማስጠንቀቂያ አዘል ሰበካ እያደረጉ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት የጀግኖቹ መዲና አርባ ምንጭ ከተማ እስከ አፍንጫቸው በታጠቁ የፌደራል ፖሊስ እና የልዩ ኃይል ጦር ዙሪያዋን ታጥራ ትገኛለች፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማም የተቃውሞ ወረቀቶች በሰፊው እንደተበተኑ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment