Translate

Tuesday, November 17, 2015

ብልግናና እና ስልጣን ( ሄኖክ የሺጥላ )


ባለጌ ብልግናውን በትምህርት ፣ በሥርዓት በተገመደ ባህል ፣ በቤተሰብ እና በሚከተለው ሃይማኖት ካላረቀ ዱርዬ ይሆናል ። ይህ ዱርዬ ወታደር ከሆነ ደሞ ፣ የጠመንጃው አፈሙዝ እና ብልግናው ጥጋብ ይደርብለት'ና የወጣለት አምባገነን ይሆናል ። የኢትዮጵያ ችግር ይሄ ነው ። አመጸኛ ባለጌ ጀግና ሆኖ ፣ የሚፈራው አጣ ፣ የሚያከብረው አጣ ፣ የሚሰማው አጣ ።
ዛሬ ሀገራችን የገባችበት መከራ ምንጩ ፣ የስድ ጓዶች ፣ የመሃይም ጀነራሎች ፣ የባለጌ ሚንስትሮች ፣ የዱርዬ ጳጳሶች እና የወሮበላ ዳኞች ሀገር ስለሆነች ነው ። ባለጌ ብልግናው እሱ ጋ አይቆምም ፣ የ ባለጌ ትውልድ አባወራ ፣ የባለጌ ልጆች አባት ፣ የባለጌ ስርዓት ባለቤት ይሆናል ። ለዚህም ነው ባለጎችን የሚያግባባቸው እና የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም አለመግባባታቸው ነው የሚባለው ። በባለጌ ስርዓት ውስጥ ይሉኝታ የለም ፣ ሰው ምን ይለኛል የለም ፣ ሀፍረት የለም ፣ ክብር የለም ፣ ታሪክ የለም ፣ ሕዝብ የለም ፣ እምነት የለም ፣ ነገ የለም !
ሕፍረቱን ያጣ ስርዓት ፣ ስርዓቱን የተነጠቀ ሕዝብ ፣ ጨዋነት የራቀው መንግስት ፣ የመዋረድ እና የማጎብደድ ርካሽነት የሚያይበት አእምሮም ነብስም የለውም ። ስለዚህ በሊቢያ መታረድም ሆነ በሱማሊያ ጦር መማገድ ሃገራዊ ውድቀት ሳይሆን እንደ አንድ የማህበረሰብ የለት ተለት ተራ ክንውን ተደርጎ የሚወሰደው ።

ድርቅ አሳሳቢ የተፈጥሮ ቀውስ ነው ፣ ረሃብ አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ ነው ፣ ሞት የዚህ አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ መቋጫ ነው ። ባለጌ ስርዓት ፣ መሃይም መንግስት ፣ ዱርዬ አስተዳደር እነዚህ ጉዳዮች እንደ ሃገራዊ ጉዳይ ሳይሆን እንደ ጠላ ቤት አምባጓሮ ነው ሊፈታቸው የሚያስበው ፣ የዚህም ሁነኛ ማሳያ በኮረም የቤት እመቤቷ ወይዘሮ ብርቱካን ልጇን በረሃብ እንድተነጠቀች የ ቢቢሲ ( BBC ) ዜና ጣቢያ መዘገቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( በባለጌዎች የሚመራ ባለጌ ተቋም ) ይህችን ሴትዮ ያለችበት ድረስ በመሄድ ፣ ልጇ የሞተው በረሃብ እንዳልሆነ እንድትናዘዝ አድርገዋታል ። በግድ ይቅርታ ሲያስጠይቁ እና ሲያሸማቅቁ ይህች ሴት ሁለተኛዋ ብርቱካን መሆኗ ነው ።
አሳፋሪ ነው ! ህሊና የሌለው ባለጌ ስርዓት ይህንን ያደርጋል ፣ በለስ ሲበላ ያደገ ለማኝ ወታደር ፣ ስልጣን ሲይዝ በረሃብ ይቀልዳል ፣ በተራበ ይቀልዳል ፣ ረሃብ በነጠቀው ሰው ይቀልዳል ። ምክንያቱም አስተዳደጉ ፣ ባህሉ ፣ የሕይወት ተመክሮው ፣ ማንነቱ እና የዛሬ ምንነቱ ባንድ ላይ በብልግና ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ ፣ በዘለፋ እና በንቀት ፣ በጉራ እና በሴስ ፣ በሱስ እና በስርያ ማንነቱን የተረጎመ ጥርብ ባለጌ ስለሆነ ፣ የሰው ነገር ፣ የሀገር ነገር ፣ የጨዋ ነገር ፣ የነገ ነገር የሚባል አንዳችም ነገር በደሙ ውስጥ የለም ። ባለጌን በሃሳብ አታሸንፈውም ፣ ምክንያቱም ማሰብ እን አሃሳብ አያውቅም ፣ ለያንዳንዱ ሃሳብህ እኩሌታ ስድብ ፣ እኩሌታ ብልግና ፣ እኩሌታ ነውር እንደ መልስ ያቀርብልሃል ። ምክንያቱም መባለግ ባህሉ ነው ፣ ነውር ወይም ጸያፍ የሚባል ነገር ሲያድግ አያውቅም ፣ እያደገ አያውቅም ፣ ካደገ ወዲያም አያውቅም ። እንደ አረም ጫካ ውስጥ ተፈጥሮ ፣ እንደ ብልቃጥ በየከተማው ቦይ እና መሸታ ቤት የሚንጫጫ፣ የሚጮህ ፣ የምያቃጭል ፣ ነውረኛ እና ስድ አደግ ስለሆነ ።
ዛሬ መሪዎቻችን ባለጌዎች ናቸው ፣ ባለጌ የወለዳቸው ነው ፣ ባለጌ ልጆች በተራቸው የወለዱ ናቸው ። ዛሬ በየ ሺሻ ቤቱ ፣ በየ ሀሺሽ መሸጫው ፣ በየ ገላ መነገጃው ውስጥ ፣ ደላላው ፣ ተጠቃሚው ፣ አስተናባሪው እና አቀናባሪው አባት እና ልጅ ናቸው ። ሀፍረተ ቢስ እና ርካሽ መሪዎች! ባለጌ እና የነውረኛ ልጆች !
ሃዋርድ ዝን የተባለ ታዋቂ የጥበብ ሰው " All protest literature says to the reader , “ have hope you are not lone “ “ ማለት ነው ሲል ይገልጸዋል ።
ልዋሰው
All vagabond fathers, all vulgar fathers and corrupted systems are telling the corrupter and the corrupted that “ have hope you are not alone “ ነው የሚለው ።
መደምደሚያ
በከሸፈ ትውልድ መሃል እንደ ሻማ የሚቀልጡ አባቶች ስላልነሳን ፣ እኛ ግን ጠፍተን አንጠፋም ። ለመንገዳችን ብርሃን ፣ ልልባችን ተስፋ የሚሆኑ እና የሆኑ ስል እና ብስል አባቶች ስላሉን ፣ እኛ ግን አንወድቅም ! ተስፋችን ፣ በገለባ ሕልም ጉብ ያለ ራእይ አይደልም ፣ እኛነታችን በአምካኝ ብኩን ወጠጤ ፣ በከሸፈ ጥርብ መሃይም ፣ መሃይምነቱን በወረሰ ዘላን ጎረምሳ የሚዳፈን አይደለም ። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ነን ፣ ኢትዮጵያዊነታችን ደሞ ኃይል ነው ፣ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለውን ኃይል ባለጌ መሪ አያከሽፈውም ፣ አያሸንፈውም ፣ እንደውም ጫፉን አይነካውም ። እንደነሱ ጭካኔ እና አውሬነት ቢሆን ዛሬ እኛ ዱዳ ፣ በድን እና ምውት መሆን ነበረብን ፣ ግን ዛሬም የምንተነፍሰው ፣ ዛሬም ቀና ብለን የምንሄደው ፣ ዛሬም ለለማኝ እና ለሰሃን አጣቢ ፣ ለጩሎ እና ለእንቁላል ተሸካሚ ያልተንበረከክነው ኢትዮጵያዊያኖች ስለሆነን ነው !
እነወጣለን ፣ ከቆረጥን ይህንን ባለጌ እና ነውረኛ ስርዓት መጣል እንችላለን ። በደማችን የያዝነው ማንነታችን በደማቸው ከያዙት ርካሽነት እጅግ የተሻለ ነውና ፣ እንበርታ !
ባለጌ እና ስልጣን ጥፋት ስለመሆናቸው አንርሳ ! ከባለጌ ወታደር ፣ ከዱርዬ መንግስት ፣ ከሸቃይ ሚንስትር ምን እንጠብቅ ?!

No comments:

Post a Comment