Translate

Thursday, December 8, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ሰራዊት በሁመራ አዲስ አለም ዲንሻ አብደራፊ በካበታና በሰሜን ጎንደር አርበደበደ።

አባይ ሚዲያ ዜና
የአርበኞች ግንቦት የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊና የግንባሩ ቃለ አቀባይ የሆኑት አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ በወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተናገሩ። እንደ ቃለ አቀባዩ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት ወታደሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በጥልቀት ሰርገው ገብተዋል። የፓለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊውም በማከልም እነዚህ ሰርገው የገቡት ወታደሮች ከወያኔ ጦር ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው እንደቀጠሉ ይናገራሉ።

አቶ መንግስቱ ወልደ ስላሴ በጎንደር ውስጥ የነጻነት ሃይሎች ከወያኔ ወታደሮች ጋር በሚያደርጉዋቸው ትግሎች ውስጥ የአርበኞች ግንቦት ሰርጎ ገብ ወታደሮች ከነጻነት ሃይሎች ጎን ተሰልፈው እየተዋደቁ እንደሆነም አረጋግጠዋል። ባለፉት ወራት በተለያዩ የአማራው ክፍሎች በተለይም በጎንደር ውስጥ ወያኔን ለመውጋት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር የአርበኞች ግንቦት ወታደሮች በጥምረት በመሆን ከገዢው ሰራዊት ጋር እየተፈለሙ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የአርበኞች ግንቦት ሃይሎች በካበታ ሁመራ ዳንሻ አዲስ አለም አብደራፊ እንዲሁም በተለያዩ የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች የተሳካ ጥቃት በወያኔ ላይ እንዳደረሰና ድልም እንደቀናው ቃለ አቀባዩ አክለዋል።
አቶ መንግስቱ ወልደ ስላሴ ገዢው የህውሃት መንግስት ይህ ሁሉ ጥቃቶች በኤርትራ መንግስት ነው የደረሰብኝ የሚለውን ክስና የማይረባ ፕሮፖጋንዳ በማጣጣል እንደውም የአርበኞች ግንቦት ሰራዊት በርግጥም ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆኖ ወያኔን ተናንቆ እየተፋለመ ነው ብለዋል። የህውሃት መንግስት ባሳለፍነው ወር የአርበኞች ግንቦት ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ሊገቡ ሲሉ ገደልኩዋቸው የተቀሩትን ማረኩዋቸው ብሎ የለቀቅውን ዜና እንደተለመደው ውሸትና መሰረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳ በማለት ገልጸውታል።

No comments:

Post a Comment