Translate

Wednesday, November 30, 2016

ሰበር ዜና — ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል

ክንፉ አሰፋ
30 ኖቬምበር 2016 – የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
Dr. Merera Gudina
ዶ/ር መረራ ጉዲና
በዛሬው እለትፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በጣጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሁኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።

በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁነታ መወያየታቸው ይታወሳል።


የኢትዮጵያ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኛል ብለው በምርጫ እና በሰላማዊ አግባብ ሲታገሉ የነበሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደታፈኑ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር በአውሮፓ ህብረት ተጋብዘው መገኘታቸው ወንጀል መሆኑን የገዥው ፓርቲ ልሳኖች ሲያራግቡት እንደነበር አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment