Translate

Monday, November 28, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 በግጨው እና ማይለሚን በተባሉ ቦታዎች ባካሄደው ውጊያ በሕወሃት ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
Patriotic Ginbot 7 fighters in action
ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔው አወቃቀር ክልል 3 ብሎ በሚጠራው አካባቢ ግጨው በተባለው ቦታ ከወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ጋር ባደረገው እረጅም ሰዓት የፈጀ ውጊያ 22 በመግደልና 29 ደግሞ በማቁሰል በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል የቆሰሉ ወታደሮችም ዲቪዥን ወደሚገኘው ሆስፒታል እንደተጓጓዙም የሪፖርተራችን መረጃ ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም ህዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚሁ በአማራ ክልል ዳንሻ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይለሚን በተባለው ቦታ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ውጊያ 12 በመግደልና 14 በማቁሰል የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ሹማምንቶችን ቅስማቸውን የሰበረ አንፀባራቂ ድል እንዲሁም የወገንን አንጀት ያራሰ ድል መጎናፀፉን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል፡፡
በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ድጋፍ እያገኘና ህዝብን ከጎኑ ማሰለፍ የቻለው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ባደረጋቸው ተከታታይ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች የሃገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረበትን ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡንና ይዞት የተነሳው አላማም በሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን አምባገነናዊ ስርዓት ገርስሶ በመጣል ሃገርና ህዝብን መታደግ በመሆኑ የአካባቢ ነዋሪ ማህበረሰብም ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገለት ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment