Translate

Thursday, November 17, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በቃፍታ ሁመራ ከሕወሃት ሰራዊት ጋር እየተፋለሙ ነው

Patriotic Ginbot 7 fighters attacked TPLF
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል።


 በአሁኑ ወቅት በአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች እና በሕወሃት ሰራዊት መካከል በቃፍታ ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ኢሳት በስፍራው የሚገኙ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

 “የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪዎች ንቅናቄው ለአንድ ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ሲፈጽም መቆየቱን እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዝርዝር ዘገባውን በምሽት ዝግጅት ይዘን እንቀርባለን።” ኢሳት።

 ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ዜና መቀመጫቸውን በውጭ ሃገራት ባደረጉ አክቲቪስቶች ድርጊቱን “ከፋኝ” የሚባል ሃይል ፈጽሞታል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ድረገጾች ተሰራጭቷል።

 “ከፋኝ” ከረጅም አመታት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ይንቀሳቀስ የነበረ ሃይል ሲሆን የድርጅቱ መስራቾች ከሌሎች ግንባሮች ጋር ተጣምረው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን” እንደመሰረቱ ይታወቃል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር” ከጥቂት አመታት በፊት በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመራው “ግንቦት 7” ጋር ውሕደት በመፈጸም “አርበኞች ግንቦት 7” እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። 

No comments:

Post a Comment