Translate

Sunday, November 27, 2016

በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ዋለ

ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስትቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ  ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም ልዩ ስሙ ሃመረ በተባለ ቦታ ላይ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሃት /ኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸው ታውቛል።

ከሁመራ ወደ ቀራቀር በሚወሰደው መንገድ ላይ ቁስቋም ማሪያም አካባቢ በሚገኝ ዳገት ላይ፣ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አባል በነበረውና ሊያዝ ሲል በማምለጥ ጫካ በገባው ጎቤ መልኬ በሚመራው የነጻነት ሃይሎች ጦርና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ውጊያ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

ከነጻነት ሃይሎች በኩል ከጎንደር እስር ቤት ሰብሮ በመውጣት ታጋዮችን የተቀላቀለውና በተዋጊነቱ ተደናቂ የነበረው ሞላ አጃው የተሰዋ ሲሆን፣ 2 ሌሎችን ጓደኞችም መሰዋታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በድንገት በተከፈተባቸው ውጊያው በመደናገጥ ገደል ገብተው  ማለቃቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በግጨው አካባቢ በአርበኞች ግንቦት7 እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ደግሞ  በርካታ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች አልቀዋል። ከሳምንት በፊት ወደ አካባቢው  የመጡ ወታደሮች ውጊያውን መቋቋም ስላቃታቸው ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ  ከጎንደር በ14 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች ትክል ድንጋይን አልፈው ወደ  ሳንጃ እየተጠጉ ነው ፡፡
ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮችን እያገዘ ሲሆን  ፣ የቆሰሉ አርበኞችን በማንሳት እና በመርዳት ድጋፍ እየሰጠ ነው ፡፡ በቋራ ገለጎ እና ክልል 6 በተደረገው ወጊያም አገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ  ኪሳራ ደርሶበታል ። የተገደሉት ወታደሮች  በ3 ትራክተሮች ተጭነው ቋራ ላይ ተቀብረዋል። አብዛኛው የሰሜን ጎንደር ከተሞች በሰሜን በሰሜን በኩል አማባ ጊዮርጊስ ፡ ገደብየ ፤ ዳባት ፤ደባርቅ ድረስ በምእራብ ሳንጃ ፤ አሸሬ ፤
ሰሮቃ ፤ ጠገዴ ፤ ማእራብ አርማጭሆ እንዲሁም በደቡብ በኩል አለፋ ፣ ሻውራ ፣ ደልጊ  እና ቋራ  በመሳሰሉት አካባቢዎች ላይ ውጥረቶች ያሉ በመሆኑ ሕ/ተሰቡ በነቂስ በመውጣት እነዚህን የነፃነት ታጋዮችን በማገዝ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ከነፃነት ታጋዮች እና ከአርበኞች ግንቦት 7 ለፍትህና ለነፃነት ንቅናቄ  ጥሪ ቀርቧል።
ገዢው ፓርቲ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ስለሚካሄደው ጦርነት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የሰጠው መግለጫ የለም።

No comments:

Post a Comment