Translate

Wednesday, December 21, 2016

ሰበር መረጃ — የላክናቸው ሁሉ አይመለሱም የሰሜን ዕዝ ስምሪት ማዘዣ!


በልኡል አለም 
በሕወሃት ኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር የወደቀው የሰሜኑ እዝ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር የላካቸው በወታደራዊ ደህንነት እና በወታደራዊ ምህንድስና የተሰማሩ አባላቶቹ መገደላቸውንና መሰወራቸውን ለኮማንድ ፓስቱ በላከው ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል። በሪፓርቱ መሰረት፣


 1. ወታደር መሀንዲስ ትህትና በለው 
2. ወታደራዊ የደህንነት አባል ቃሲም ይማም 
3. ወታደር መሀንዲስ ዝናቡ ሕንጻ 
4. ኮማንደር ማንያዝ ገብሬ
 5. ወታደር ማሀንዲስ ቃቄ 

የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑን መረጃዋች ሲጠቁሙ…

 1. የ10 አለቃ ስንሻቅ 
2. ጓድ መሪ ወ/ር መሀሪ ጎላ
 3. ወታደራዊ ደህንንት አባል ወ/ር ሶስና ፍስሀዬ
 4. ወ/ር ገላው ስንቄ
 5. ወ/ር ምጅዱ
 6. ወ/ር አለሞ አጋፋሪ
 7. ጋረድ ብሻፍለጋው 

የተባሉ የመረጃና የቅኝት ወታደሮች በህዝባዊ ሃይሉ መበላታቸው ተረጋግጧል።

 በተያያዘ መረጃ ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ውጊያ የገጥመው የምሥራቅ እዝ ከሶማሌያ የተወረወረ የኦነግ ሐይል አስግቶኛል በሚልመነሻ ወደ ሰሜን ዕዝ የተዛወረው ብረት ለበስ ሜካናይዝድ ይመለስልን ሲል ለመከላከያ ሚንስቴር ዘመቻ መምሪያ አመራርሮች ጥያቄ አቅርቦአል።

 መከላከያ ሚኒስቴሩ በኮማንድ ፓስቱ ወታደራዊ ስልት በሚዘወርበት በዚህ ሰዓት መአክላዊ ዕዝ ውስጥ የተካተቱ ወታደሮች የፌደራል ፖሊስን ደርበን አናግዝም በማለታቸው በአዲስ አበባ ዙሪያ ሊቀሰቀሱ የሚችሉ ነውጦችን መቆጣጠር የማይቻልበት አደጋ እንደሚያመጣ ምንጮች ገልፀዋል።

 ዽል ለኢትዮጵያ ህዝብ! 

No comments:

Post a Comment