Translate

Friday, November 17, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ፣ በወታደሮች ታጅቦ ይጓዝ በነበረ መኪና ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገለጹ


ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሚትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

ከአሁን ቀደም እንደሚታወቀው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአወጀበት ወቅት “ቀይ ዞን” በማለት በአደገኛ ቀጠናነት ከፈረጃቸው ቦታዎች አንዱ ከጎንደር መተማ እስከ ሱዳን ያለውን መስመር ነው፣ በመሆኑም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት አሰከ ቀኑ 11:00 ብቻ ተሽከርካሪዎች እንደሚያልፉ እና ከዚህ ሰዓት በኃላ አይደለም ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ይቅርና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም በመንገዱ አያልፉም፡፡
በመሆኑም የህወሓት ወታደሮች አጅበውት ከሱዳን በኩል የመጣው ይሄ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ከነጋዴ ባህር ማደር ሲገባው ከዚያ እደማያድር ቢመሽም ጎንደር መግባት እዳለበት ነዳጅ ለአስቸኳይ ግዳጅ ስለተፈለገ ታጅቦ እደሚሄድ መረጃው የደረሳቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች ከጓንግ ወንዝ ባለው አቅጣጫ ደፈጣ በመጣል ይሄን በአጀብ ሊያልፍ የነበረን ወያኔ ለልዩ ግዳጅ ሊያውለው የነበረውን ነዳጅ እስከነ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በማውደም በሹፌሩና በአጃቢ ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። አርበኞቹም የተሰጣቸውን ግዳጅ በአግባቡ ፈፅመው ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡
እንደሚታወቀው የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ከህዳር 2-3 ቀን 2010 ዓ/ም በተመረጡ ታርጌቶች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ገልፆ የነበረ ሲሆን ጥቃቱም ቀጣይነት እደሚኖረው ማስታወቁ ይታወሳል ይሄም ጥቃት የዚያ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ውጥረት ነግሷል ፍተሻም በእጅጉ ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡
ይህ በእንዲህ እዳለ ወያኔ ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጎንደር ከተማ በሚያስገቡ 3 መግቢያዎች ላይ ኬላዎችን ማለትም ከሁመራና ከደባርቅ በኩል ወደ ጎንደር መግቢያ ከባህርዳር በኩል ባለው መግቢያ እና ከመተማ በኩል ባለው መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነበትም ወያኔ በህዝብ ስም የህወሓት ካድሪዎችን እና የእሱ ተላላኪ የሆነው የብአዴን ካድሬዎችን ያካተተ “የሰላም ኮንፈረንስ” ብሎ የጠራውን ስብሰባ በጎንደር እያካሄደ ስለሆነ አርበኞች ወደ ከተማዋ ገብተው ጥቃት ይፈፅሙብኛል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች እንዲሁም በደሴ ከተማ ውጥረት ነግሶ ይገኛል በአካበቢው ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ለህዝባችን የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ!

No comments:

Post a Comment