Translate

Thursday, March 21, 2013

የባህር ዳሩ ጊዮን ሆቴል ህወሀትንና ብአዴንን ዱላ ቀረሽ ፍጥጫ ዉስጥ መክተቱ ተሰማ



በደርግ ዘመነ መንግስት የአገር ሀብት የነበረዉና ባለፉት ሃያ አንድ አመታት የትግራይ ተወላጅ በሆነ ግለሰብ አላግባብ ተይዞ የነበረዉ የባህርዳሩ ጊዮን ሆቴል ባለቤትነት ለአማራ ክልል የመንግስት ቤቶች ኤጄንሲ እንዲዘዋወር መወሰኑ የህወሀትንና የብአዴንን ከፍተኛ ባለስልጣኖች ግጭት ዉስጥ እንዳስገባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። በ1983 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በመንግስት ይዞታ ስር የነበረዉን የባህርዳሩን ጊዮን ሆቴል ለመለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመደ ለሆነዉ ወልዱ ለሚባል ግለሰብ በ5000 ብር በኪራይ ስም መሸለሙ ይታወሳል። የአድዋ ተወላጅ የሆነዉ ወልዱ የሚባለዉ ግለሰብ ወያኔ የትጥቅ ትግል ያካሄድ በነበረባቸዉ 17 አመታት ባህርዳር ዉስጥ የህወሀት ሰላይ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን መለስ ዜናዊ ያንን የመሰለ ዘመናዊ ሆቴል በ5000 ብር የሸለመዉ ለዚሁ የስለላ  አገልግሎቱ እንደሆነ ብዙ የባህር ዳር ነዋሪዎች በግልጽ ይናገራሉ።
ባለፉት ሃያ አንድ አመታት ጊዮን ሆቴል ለወልዱና ለልጁ ለብስራት ወልዱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ትርፍ ሲያስገኝ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በሆነባቸዉ አመታት ሁሉ የባህርዳር ከተማ ህዝብ አንድ ኪዎስክ በ5 ሺ ብር እየተከራየ እንዴት ጊዮን ሆቴልን የሚያክል ትልቅና ዘመናዊ ሆቴል በ5 ሺ ብር ብቻ ይከራያል እያለ ተቃዉሞዉን ቢያሰማም የሚሰማዉ ጠፍቶ ሃያ አመታት አልፈዋል። ሆኖም በቅርቡ መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ የፌደራል የኪራይ ቤቶች ድርጅት የአማራ ክልል መንግስት ሆቴሉን እንዲረከብ ለአማራ ክልል የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ደብዲቤ በመጻፉ ጉዲዩ ከክልል አልፎ ገዢዉ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረስ ችሏል። ሆቴሉን ለከልል መንግስት እንዲያስረክቡ ደብዲቤ የደረሳቸዉ ወሌደና ሌጁ ብስራት ጉዳዩን በቀጥታ ለበረከት ስምኦን፤ ለፌዳሩሽን ምክር ቤት ሰብሳቢው ካሳ ተክለብርሀንና ለአዲሱ ለገሰ የመለስ ዜናዊን ሞት ተክትል ሆቴሉን እንዱያስረክቡ መጠየቃቸውን በመናገራቸው፣ ባለስልጣኖቹ የክልሉ መንግስት የጻፈውን ደብዳቤ እንዱያነሳ ጠይቀዋል።

የክልሉ የመንግሰት ቤቶች ኤጀንሲ ጉዲዩ ከፍተኛ ዝርፊያ መሆኑን ገልጾ ዉሳኔዉን ለመለወጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን ቢገልጽም የሆቴለ አስተዳዳሪ የሆነዉ ብስራት ወልዱ የክልሉን ባለስልጣናት በማስፈራራት እርምጃ እንደሚወስድ በመዛት ሆቴሉን ለማስረከብ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልጿል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የዝግጅት ክፍላችን በስልክ ያናገረዉ አንድ የኪራይ ቤቶች ድርጅት ሰራተኛ የሆቴሉ አስተዳዳሪ ብስራት ወልዱ ሆቴሉን እንዲያስረክብ ደብዳቤ ሲጻፍለት “ዋጋህን ታገኛለህ” የሚል መልስ መስጠቱን ተናግሯል። የባህርዳር ከተማ ህዝብ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በአንድ ተራ የህወሀት አባል መደፈረቸዉን አስመልክቶ እያሾፈ ሲሆን እንደ ብዙ ታዛቢዎች እምነት የክልሉ መንግስት ከዚህ አይነቱ ህዝባዊ ትችት ነጻ መሆን የሚችለው ግለሰቡ ሆቴሉን እንዱያስረክቡ ሲያደርግና እንደማንኛውም ሰው ተጫርቶና ለጨረታዉ ተገቢውን ክፍያ ማስከፈል ሲችል ብቻ መሆኑ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment