Translate

Friday, March 15, 2013

የመለስ ዜናዊ የመጨረሻ ስብሰባ ሰነድ ይፋ ወጣ!


Meles Zenawi UN Climate Change Summit Enters Final Week
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በአዲስ አበባ አድርገውት የነበረው የመጨረሻ ለሊት ስብሰባ፤ እንዲሁም የስብሰባውን ቃለ ጉባዔ ሙሉ ቃል እነሆ ይፋ አድርገናል። ስብሰባው የተደረገው ጠቅላይ ሚንስትሩ በአሜሪካ ቆይታቸው ወቅት አበበ ገላው በተቃውሞ ካስደነገጣቸው አንድ ወር በኋላ፤ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሃምሌ 15 ቀን፣ 2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ነው። የመነጋገሪያ አጀንዳው በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ የተነሳውን ተቃውሞ አስመልክቶ ሲሆን፤ በዝርዝሩ ውስጥ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የተሰጠውን ማብራሪያ ተካቷል። ስብሰባው ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ላይ ሲጠናቀቅ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለአስቸኳይ ህክምና ወደ ውጭ አገር እንደሚሄዱ እና ከህክምናቸው በኋላ ውሳኔውን ለመተግበር እንደሚሰሩ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ነገር ግን የታሰበው ሳይሳካ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደወጡ ቀሩ፤ በዚያው ሞቱ።

3 comments:

  1. ወንድም ተስፋዬ ለወትሮው መረጃዎችህ ላይ ጥንቃቄዎችን እናስተውል ነበር፡፡ ምነው ታዲያ በዚህኛው ላይ ያ ጥንቃቄ ተለየህ ወይስ ብሎግህ ካንተ ቁጥጥር ውጭ ሆነ ፡፡ እስቲ አንድ ጥያቄ ልወርው በተባለው "የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የስብሰባ ቃለ ጉባዔ" ላይ የመጨረሻው መስመር ያዘለው ስቴትመንት የሚለው ሚንስትሩ ህክምናቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የውሳኔዎቹን አተገባበር እንደሚገመግሙ ያትታል፡፡ ባንተው ማንደርደሪያ ላይ ግን ከህክምናቸው በኋላ ውሳኔውን ለመተግበር እንደሚሰሩ ቀጠሮ ተይዞ ነበር ትለናለህ::በእነዚህ ሁለት ሃሳቦቸ መካከል ደግሞ የትርጉም ልዩነቱ የምስራቅና የምዕራብን ያህል ነው፡፡ ሁለት የተለያዩ ጫፎች፡፡ ባንተው ፅሁፍ መሰረት ውሳኔው የሚተገበረው ያለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሲመለሱ ሲሆን በተባለው ቃለ ጉባዔ ላይ ግን ቀሪዎቹ ተሰብሳቢዎች በዋናነት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር እየፈፀሙ ይቆዩና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመለሱ ውሳኔዎቹ ምን ያህል እንደተተገበሩ ይገመግማሉ፡፡ይህ ያንተው ስህተት ነው፡፡ ሕዝቡን ለማወናበድ በማለም ይህን ሰነድ ፈብርከው ለለቀቁት የምንለው አለን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የአህባሽን ፍልስፍና በሙስሊሙ ላይ ለመጫን በዋናነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ለመሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስም በዚሁ አቋማቸው የፀኑ እንደነበሩ ከአንተም ከእኛም የተሰወረ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጨረሻ ጊዜ በታዩበት የፓርላማ ውሎአቸውም ያስተዋልነው ይህንኑ ነበር ታዲያ እንኳንስ ለህክምና ሄደውና ይሄው ሞተው እንኳ በሙት መንፈሳቸው የሚሸበሩት ተተኪዎቻቸው እንደምን የተባሉትን ውሳኔዎች ሳይፈፅሙና ሳያስፈፅሙ ይቆያሉ ብለህ ታስባለህ አትድከም እነበረከተ እርግማን የሙስሊሙ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት ለኢህአዴግ/ህወሐት ያለውን አመለካከት ለማለዘብ የተመኙበት ፊክሽናል ስብሰባና የስብሰባ ውሳኔ ነው፡፡ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከዓመት በላይ በዘለቀው ሰላማዊ ትግሉ ብልጦች አይደለንም ብልጣብልጦች ግን አያታልሉንም ሲል ዘልቋል እናም እንላለን የሙስሊሙን ቅሬታ ለመፋቅ የሃሰት ሰነዶች ፋይዳ የላቸውም፡፡ ይልቁንስ አሁንም ያቀረብናቸውን 3 ግልፅና የእምነት መብት ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች መመለስ፥ እኒህን ጥያቄዎቻችንን ይዘው ከሚመለከተው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር እንዲያስፈፅሙልን መርጠን የወከልናቸው የሰላም አምባሳደሮቻችን የሆኑት ኮሚቴዎቻችንንና ድምፃችን ይሰማ ለማለት ወጥተው ከእምነት ቦታዎቻቸውና ከሰላማዊ ቤታቸው እየተለቀሙ የአገሪቱን እስር ቤቶች ያጣበቡ ወንድሞችና እህቶቻችንን መፍታት ብቻና ብቻ መፍትሔ መሆናቸውን መረዳት ይበጃል፡፡ የተባለው ሰነድ ልብ ወለድ ለመሆኑ ግን ነቄ ነን ፡፡እንደግመዋለን "ብልጦች አይደለንም ብልጣብልጦች ግን አያታልሉንም"

    ReplyDelete
  2. ሰላም ላንተ ይሁን ! ወንድሜ ሰይፍ ስለሰኸኝ አስተይየት ምስጋናዬ ከልብ ነው፡፡ በመቀጠል አንተ ወንድሜ ከምትለው በላይ ይህ እኩይ ስርዓትና የስርዓቱ ቁንጮዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፅሙትን ገደብ ያጣ በደልና እንግልት በሚገባ የማውቅና ይህም በኢትዮጲያችን የሚታየው ግፍ እንዲያበቃ አቅም በፈቀደና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የምታገል ወንድምህ እንደሆንኩ ልትስተው አይገባም፡፡ ሆኖም ይህንን አስተያየት የሰጠህበት ፅሁፍ የኔ ፈጠራ ሳይሆን ምንጩን ጠቅሼ በብሎጌ ማስቀመጤን መዘንጋት የለብህም፡፡ ምንም ይሁን ምን እየተባለ ያለውን ታሪክ ለአንባቢያን ማቅረቤ ስህተት ነው ብዬ አላስብም የሚገርመው እኔ እራሴ መጀመሪያ ሳነበው አሁን አንተ የተሰማህንና ያስተላለፍከውን አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ አሁንም ሃሳብህን እጋራለሁ በምንም አይነት መልኩ የሙስሊም ወገኖቼ ሰላማዊ የመብት ትግል እንዲቀለበስ አልፍልግም እንዲሁም በሰላማዊ ትግል ተምሳሌትነቱ የምኮራበትና የዚህ እኩይ ስርዓት የግፍ ቀንበር ከብዶት የሚሰቃይ ኢትዮጲያዊ ሁሉ በቁርጠኝነት በአርያነት ሊከተለው የሚገባ የትግል ስልት ነው ብዬ ከልብ አምናለሁ ለተግባራዊነቱም የበኩሌን አረጋለሁ፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ትረዳኛለሁ ብዬ አስባለሁ ስለሰጠኸኝ አስተያየት በድጋሚ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

    ReplyDelete
  3. ሰውዬው (ለገሰ ዜናዊ) የሞተው ሐምሌ 7-2004 አይደለም እንዴ ምንድነው የምታወራው? ነው ወይስ አንተም አንደ ኢቲቪ መቀባጠር ጀመርክ?

    ReplyDelete