Translate

Saturday, March 30, 2013

እንገፋበታለን እየተባለ ከበሮ የሚደለቅለት እዉነተኛዉ የመልሰ ዜናዊ ራእይ ተልእኮ፣ ግብና የአፈጻጸም መሳሪያዎቹ


ከአየነዉ ብርሃኑ

እንደ መንደርደሪያ
መለስ ዜናዊ ላይመለስ ሄዷል። አገርን የማፈራረስ እቅዱና ዘርን የማጥፋት አላማዉ ግን ዛሬም አለ።ወደፊትም እንደሚቀጥል የመለስ ምልምሎች ደግመዉ ደጋግመው እስኪገለማን ድረስ እየነገሩን ነው።
ባለ ራእዩ መሪ፣ ሊቁ መሪ፣አርቆ አሳቢዉ መሪ፣ የአፍሪካ ጠበቃ እንዲያዉ በአጠቃላይ ስለ መለስ ምን ያልተባለ አለ !! ሀይማኖቴን ቀይሬ በመለስ ማመን ጀምሬአለሁ ያለም አለ። ይባስ ብለዉም ፖሊስ ሲያባርረዉ የተወረወረዉን ወጣት በመለስ ሞት ምክንያት ከአስረኛ ፎቅ ላይ በመዉደቅ ራሱን አጠፋ ይሉናል። ምን ይህ ብቻ መለስ ዜናዊ አሁንም በመንፈስ እየገዛ ነዉ በሚል የሰበካ ስራ የተሰማራዉ የአዳዲስ ካድሬ ብዛት የትየለሌ መሆኑም ይነገራል።
ሁሉንም ማለት መብት ነው።ይመኑበትም ይስገዱለትም ይሙቱለትም ምንም ይሁን ምን መለስ አሁን የለም።ወደፊትም አይኖርም። ይቅበሩትም ያቃጥሉትም ለጊዜው ባይታወቅም እሱና እርኩስ ተግባሩ አሁን የሉም።

ከመለስ ህልፈት በኋላ በወያኔ ጎራ ትልቁ ስራና ይህ ነዉ የማይባል የገንዘብ መጠን የፈሰሰበት የመለስን ስብእና ከፍ ማድረግ እና ስራዎቹን ማወደስ ሆኖ ቆይቶአል። ለምን ይህን ማድረግ አስፈለገ?
የመለስ ድንገተኛ ሞት ወያኔን አስጨንቆት እንደነበር ይታወቃል ። የተደረገዉ በመለስ በድን የመነገድ ድራማም ሆነ የግዢ ልቅሶ ድራማ ከጭንቀት የመጣና በደመነፍ የተከናዎነ ትእይንት ሲሆን ድራማዉም ሁለት የመለስን ምልምሎች በጭምብል መሪነት በማስቀመጥ ተጠናቋል።የመለስን ራእይ የማስቀጠሉና የሱን ፈለግ የመከተሉ የፕሮፓጋንዳ ግሳንግስ ተጠናክሮ ቀጥⶀል ። ምልምሎቹም ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ ሆነዋል። ከመልስ ዜናዊ ባልተናነሰ መልኩ ከመለስ ዜናዊ የወረሷቸዉን ያልተገሩና አስጸያፊ የካድሬ ዝባዝንኬዎች ሲተፉ ትስተዉለዋል።
ይህን እየሰሙ እነዚህን የዎያኔ ሮቦቶች ማንነት ማሳወቅ፣ እንዴት ለመለስ ዜናዊ ደቀ መዝሙርነት እንደበቁ ማወቅና ወደፊት ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥፋት ለመገመት የሚያስችል ግንዛቤ መስጠት የሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታ መሆኑን በማመን ነው ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀዉ። የበዛዉን ቀንሰዉ ያነሰዉንም ጨምረዉ የራስዎን ግንዛቤ መዉሰድ የርስዎ የአንባቢዉ ድርሻ ነዉ። ይቀጥላል…

No comments:

Post a Comment