Translate

Monday, March 25, 2013

“እኔ ግን አልሞትኩም” – አላሙዲ


‹‹ጠ/ሚ/ር መለስን በማጣቱ ሰው ተደናግጦ ነበር፤ … እኔንም ገለውኝ ነበር፤ ግን አልሞትኩም እስከአሁን ከእናንተው ጋር ነኝ›› ሲሉ መናገራቸውን ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ መናገራቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ኢትዮቻናል ጋዜጣ ዘገበ። ዘገባው ለግንዛቤ ይጠቅማል በሚል ሳንጨምር ሳንቀንስ አቅርበነዋል – ያንብቡት። በአሁኑ ወቅት በሥሩ 20 ግዙፍ ኩባኒያዎችን የሚያስተዳድረው የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ባለፈው እሁድ 10ኛውን የደምበኞች፣ የሠራተኞችና የቤተሰቦች ቀን በዓል አከበረ፡፡ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ቺፍ ኤግዚክዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ ላይ እንደገለፁት ‹‹የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ውስጥ መሪዎችም ሆንን ተመሪዎች ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ሠራተኞች ነን፤ አሠሪ ቢኖር አንድ ሰው ብቻ ነው›› ነበር ያሉት፡ ፡ ዶ/ር አረጋ ‹‹ አንድ አሠሪ ብቻ ነው ያለን›› ያሏቸው ክቡር ዶ/ር ሼክ አል- አሙዲ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግርም ‹‹ለአንድ ሀገር መመስረቻው ቤተሰብ ነው፡ ፡ ከዚያ ቀጥሎ ቤተሰብ ወልዶ ተዋልዶ ሠራተኛ ይፈጥራል፤ ሠራተኛውም ለሚያመርተውም ደምበኛ ያመጣል፡፡ ከምወዳቸው ነገሮችና መገኘት የምፈልገው ይህንን ቀን ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹የሜድሮክ ዕድገት አይገታም››
ክቡር ዶ/ር ሼክ አል-አሙዲ ሀገሪቱ እያደገች መሆኑን ነው በዕለቱ የገለፁት፡፡ በተለይ፤ ከኩባኒያዎቻቸው ጋር ተያይዞ ‹‹ይሄ ቤተሰብ ጥሩና ጠንካራ ሠራተኛ ፈጥሮልናል፤ ይህም ሠራተኛ ጥሩ ደንበኞችን ማትረፍ ይዟል፡ ፡ በዚህ ከቀጠላችሁ የሀገሪቱ ዕድገት የት እንደሚደርስና ምን እንደሚመስል ባለፈው 10 ዓመታት አይታችሁታል›› ሲሉ ነው የገለፁት፡፡ ይሁንና፤ ባለፈው ዓመት ከጠ/ሚ/ር መለስ ህልፈትን ተከትሎ ለጥቂት ሰዓታት ሰው ተደናግጦ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ‹‹አስቀድሞ መሠረት ያለው አመራር ስለነበር፤ ነገሮች ሳይናጉ በተቀመጡለት መስፈርት ሁላችንም እየሄድን ነው፤ … ፈጣሪ ካመጣ ሞት አይቀርም፣ ሁላችንም ሟች ነን፡፡ እኔንም ገለውኝ ነበር፤ ግን አልሞትኩም፡ ፡ እስከአሁንም ከእናንተው ጋር ነኝ›› ብለዋል፡፡ እናም ‹‹በሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ያሉ ድርጅቶች እያደጉ ነው እንጂ እየመነመኑ እንደማይሄዱ አረጋግጥላችኋለሁ›› ብለዋል፡፡
ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባኒያዎች እያደጉና ቁጥራቸው እየጨመረ ካፒታላቸውም ከፍ እያለ መምጣቱን ነው የገለፁት፡፡ ‹‹እስከ አሁን ድረስ ቀንቶናል፤ ወደፊት ግን ከበድ ያለ ሥራ ያጋጥመናል፡፡ ሀገራችን እያደገች ነውና ብዙ ተወዳዳሪዎች ይኖራሉ›› ሲሉም፤ ለመጪው ግዜ ኩባኒያዎች ለሚገጥማቸው ውድድር ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡
*መተካካት በሜድሮክ*
አሁንም ቢሆን ሜድሮክ እያደገ እየሰፋ ቢመጣም፣ ዕድገቱን ለማስጠበቅ ክቡር ዶ/ር ሼክ አል-አሙዲ ‹‹በተለይ እንደእኔ ያለው ዕድሜ ገፋ ያለ ሳይሆን ወጣቱን ትውልድ ይዘን የኢትዮጵያን ዕድገት ለዓለም እናሳያለን›› ሲሉ ‹‹አዳዲስ ወጣቶችን እያሰለጠንን መተካት ጥሩ ደረጃ ላይ ነው ያለነው›› ያሉት ደግሞ ዶ/ር አረጋ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው፡፡ በጠቅላላ ኩባኒያዎቹ ሰው ተኰር የማኔጅመንት አካሄድና ፍልስፍና ተግባራዊ በማድረግ እየተጠናከረ መምጣቱን አፅንኦት የሰጡት ዶ/ር አረጋ ሥራውንና አለቆቹን የሚያከብር፣ ሀገሩን የሚወድና ሥነ-ሥርዓት ያለው እንዲሁም በሀገሪቱ መጥፎ ፀባዮች እንዲጠፉ ለማድረግ አቋም እንዳለው ነው የገለፁት፡፡ ለዚህ ደግም ‹‹ከመጠን በላይ ጥንቁቅ ከመሆናችን የተነሳ በአሁኑ ግዜ ሰው እንኳን ስንቀጥር አረንጓዴ ጥርስ ያላቸውና የሌላቸው መሆናቸውን እየተመለከትን ነው›› ብለዋል፡፡
‹‹እንደዚህ ዓይነት ባህል እኛ ጋ አይኖርም፡፡ ወደፊትም አይኖርም፡ ፡ ጥርት ያልን መሆን አለብን፡፡ ለፍተን ያገኘነውን ገንዘብ ጫት የምንበላበት ከሆነ ሌላ ነገር ነው›› ያሉት ዶ/ር አረጋ ‹‹ሀገሪቷ ጫት መሸጥ ከፈለች ግን እሱ ሌላ ነገር ነው›› ይላሉ፡፡ ‹‹የእኔ ኃላፊነት ሠራተኞቼ ጤነኛ ሆነው የሚያገኙትን ገንዘብ ለጤና እንዳያውሉትና ለልጆቻቸው እንዲያስተዳድሩበት ማድረግ ነው›› የሚሉት ዶ/ር አረጋ ‹‹ቅጠል መብላት ለፍየሎች ብቻ የተፈቀደ ነው›› ብለዋል፡፡
*ምን ተከናወነ?*
በበዓሉ ላይ ኩባኒያዎቹ ባለፉት ዓመታት በሥራዎቻቸው አብረዋቸው ለተጓዙት ደምበኞቻቸውና የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ ለሆኑት ሁሉ እንደከዚህ ቀደሙ በላቀ ደረጃ አገልግሎት ለማበርከት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡ በ2004 ዓ.ም ለኩባንያዎቹ ለስራ ማስኬጃ፣ ለማምረቻ፣ ለቋሚ ንብረት ግዢና ለፕሮጀክት ማስፈፀሚያ 2.2 / ሁለት ነጥብ ሁለት/ ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ በበጀት ዓመቱ ካስገኙት 1.6 /አንድ ነጥብ ስድስት/ ቢሊዮን ከታክስ በፊት ትርፍ ለመንግስት ካዝና ከ690 ሚሊዮን ብር በላይ በታክስና በሮያሊቲ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡ በዚሁ ዓመት ለፕሮጀክትና ለማስፋፋት ስራ ከተያዘው በጀት ውስጥ ብር 262,488,746 /ሁለት መቶ ስድሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺ ሰባት መቶ አርባ ስድስት/ በተግባር ላይ ውሏል፡፡
በቅርቡ የቴክኖሎጂ ግሩፑን የተቀላቀለው ሰሚት ፓርትነርስ ኃላ/ የተ/የግ/ማህር በ20ኛው የቴክኖሎጂ ግሩፑ አባል ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ ግሩፑ ውስጥ 5,186 ቋሚና 1,797 የኮንትራት ሠራተኞች ሲኖሩ በድምሩ ለ6,983 ሠራተኞች የስራ ዕድል የተመቻቸላቸው ሲሆን፣ በ2004 በጀት ዓመት በተለያየ መልኩ የ183 / መቶ ሰማኒያ ሶስት ሚሊዮን ብር/ ክፍያ ተፈፅሟል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለኩባንያ ሠራተኞች ለትምህርት በተሰጠው ዕድል በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ፣ በቴክኒክና ሙያ፣ በአንደኛና በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ 105 ሠራተኞች ሲሆኑ፣ የ2004 ዓ.ም የትምህርት ወጪው ብር 661,000 ነበር፡፡
ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች መካከል የግብርና ውጤቶችን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በሻሎ እርሻ ልማት የጠብታ መስኖ ፕሮጀክት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡ ፡
በነትሌ በመስኖ የተጀመረው የገበታ የወይን እርሻ ልማት ውጤታማ ሆኖ ምርቱ ለውጭ ገበያ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡ በክቡር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የተጎበኘው የአልፋ አልፋ የከብቶች መኖር የሙከራ ፕሮጀክትም ውጤት በማስገኘቱ ምርቱን በስፋት ለማምረት በጀት ተመድቦለት ስራ ጀምሯል፡፡
በነትሌ በመስኖ የተጀመረው የገበታ የወይን እርሻ ልማት ውጤታማ ሆኖ ምርቱ ለውጭ ገበያ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡ በክቡር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የተጎበኘው የአልፋ አልፋ የከብቶች መኖ የሙከራ ፕሮጀክትም ውጤት በማስገኘቱ ምርቱን በስፋት ለማምረት በጀት ተመድቦለት ስራ ጀምሯል፡፡
በተያዘው የ2005 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በመተከልና በመንታ ውሃ የሚያካሂደውን ማዕድን ፍለጋ በማጠናቀቅ ወርቅ ማምረት የሚያስችለውን ጥናት ጀምሯል፡፡ የወርቅ ማምረቻ የፋብሪካ ተከላ ለማካሄድ አስፈላጊው ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ.ማህበር አዲስ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ማምረቻ፣ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃላ/የተ/የት/ ማህበር ደግሞ በሀገሪቱ በግል ድርጅት የመጀመሪያ የሆነውን የግል ቆርኪ ማምረቻ ዘመናዊ መሳሪያ ተከላ እያከናወነ ሲሆን፣ ዩናይትድ የአውቶሞቢል ጥገና አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ዘመናዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ መመርመሪያ መሳሪያ በመትከል ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሁዳ ሪል እስቴት በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስም የተሰየመውን የወልድያ ስታዲየም በ261 ሚሊዮን ብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በመቂ /ነትሌ/ እና በሻሎ /ሐዋሳ አጠገብ/ በከፍተኛ ደረጃ የጠረጴዛ ወይንና የአልፋአልፋ ምርት በዘመናዊ መስኖ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ከ4500 በላይ ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች፣ የየኩባንያዎቹ ደምበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ከየኩባንያዎቹ ለተመረጡ ምርጥ የኩባንያ ደምበኞች፣ ምርጥ ሰራተኞች፣ የዓመቱ ምርጥ ስራ አስኪያጅ፣ ምርጥ ኩባንያና ምርጥ የሠራተኛ ማህበር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment