Translate

Thursday, March 28, 2013

መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!


በታምሩ ገዳ

በየትኛውም የእድገት  ደረጃ  ይሁን የፖለቲካ  አመለካከት ወይም የሃይማኖት  ስርአት  ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው  ቢባል ማጋነንPope Francis breaks with tradition and refuses to move into a palatial apartment  አያስብልም፡፡
ለዚህ ይመስላል የሮማ  ካቶሊክ ቤ\ክርስቲያን   በቀርቡ 266ኛዋን  መሪ (ፓፓ ) ለመምረጥ የሃይማኖቱ አባቶች  በቫቲካን ከተማ  በተሰባሰቡበት  ወቅት በ 150,000ዎች  የሚቆጠሩ ምእመናን ቀጣዩ የሃይማኖታችን አባት  ማን ይሆኑ? በማለት  የምርጫው ውጤቱን ለማወቅ  በታላቁ  የቅዱስ  ጴጥሮስ  አደባባይ ተሰባስበው የነበረው፡፡ በዚህ የምንፈስ  ቅዱስ መሪነት  በተካሄደው  የመጪው  የቤተክርስቲያኒቱ  መንፈሳዊ አባት መረጣ    ላይ  የብዙዎቹ ምርጫ ሆነው  የቀረቡት  ከ120 ሚሊዮን  በላይ የእምነቱ ተከታዮች  ያሏት አገር  ብራዚል  ከሳኦ ፖሎ ከተማ  የመጡት  አርክቢሾፕ ኦዲሎ ሺረር ነበሩ፡፡
ለምን? ቢባል አርክ ቢሾፕ ኦዲሎ  በቫቲካን ውስጥ  በሚገኙ  ታላላቅ መነኮሳት  ዘንድ ቀረቤታ ያላቸው አባት በመሆናቸው ነበር ፡፡ይሁንና የምርጫው ስነስርአት ሲጠናቀቅ  አባ ጆርጁ ቤርጎባሌዮ የ1.2 ቢሊዮን ህዝብ(በአለማችን ላይ ያለው የካቶሊክ አማኞች ቁጥር  መሆኑ ነው) አባት ናቸው  የሚለው  ዜና  ሲሰራጭ በዙዎች  አባ ጆርጁ  ቤርጎባሌዮ ወይም አባ ፍራንሲስ ማናቸው?  የሚለው ጥያቄን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ የብጹነታችውን ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት  በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ አዲስ አባት  አገኘን (we have a Pope!)ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ለወትሮው ፓፓው  ለህዝቡ የሚጸልዩት ወይም  ህዝቡን የሚባርኩት እርሳቸው ሲሆኑ በአሁኑ ግን እርሳችው ለተስብሳቢው ህዝብ  !እባካችሁ  ጸልዩልኝ!” ሲሉተማጽነዋል፡፡
ላለፉት ስምንት አመታት  በፓፓነት ማእረጋቸው ሲያገለግሉ ቆይተው በህመም  ምክንያት  በቅርቡ ስልጣናቸውን በፍቃደኝነት  የለቀቁት  አቡነ ቤኔዲክት  16ኛውን በመተካት  ሰልጣኑን የተረከቡት  አቡነ ፍራንሲስ አባታቸው ጣሊያናዊ የባቡር  ላይ ሰራተኛ   ሲሆኑ የፋሺስቱን  አገዛዝ  በመሸሽ በእርጀንቲና  ቦነስ አይረስ  ከተማ  ፍሎረነስ  በተባለች  አንስተኛ አካባቤ  መኖር ጀመሩ ፡፡ ልጃቸው  አቡነ ፍራንሲስ በ1936 እኤአ  እዚያው አርጀንቲና ውስጥ ተወለዱ፡፡  ለደሆች እና ለተፈጥሮ ሃብት ተቆርቋሪ ከነበሩት  ከቅዱስ ፍራንሲስ  (ከሃብታም  ቤተሰብ ተወልደው ስለደሃዎች እና ጭቁኖች መብት መከበር ሲሉ በሮም  ጎስቋላ ስፍርዎች  ከመጻጉዎች እና ከደሃዎች ጋር ይኖሩት ከነበሩት የኦሲሱ  ቅዱስ ፍራንሲስ ናቸው ) መጠሪያ ሰያሜ ያገኙት አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን  አባት  የሆኑት ብጹነታቸው ለደሃዎች   ደህንነት እና  እኩልነት  የሚሟገቱ ታላቅ  አባት እንደሆኑ ብዙዎች ይመስክሩላቸዋል፡፡አባ ፍራንሲስ  በብዙ መልኩ ከቅንጦት እና ምቾት ካለው  አለማዊ  ኑሮ  ይልቅ ዝቅተኛ የሆነ (ሎው ፕሮፋይል) የሚመርጡ ሲሆኑ እነዚህ ምልካም ተግባሮቻቸው  መካከል  በቅዳሴ ጊዜ  በአለማዊ ሰዎች  ዘንድ  ከተዋረዱት  በእግዚአብሄር  ፊት ግን  እኩል ከሆኑት  በቦይነስ አይረስ  ከተማ  ከሚገኙ የቀድሞ ሴትኛ አዳሪዎች  ጋር አብረው  በመጸለይ የሃይማኖታዊ   አባትነታቸውን  እና አርያነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከዚያም አልፎ ለስልጣነ ክህነታቸው  ሲባል ለግላቸው የተመደበላቸውን ዘመናዊ ሌሞዚን  መኪና  ከእነ ሹፌሩ  እርግፍ አድርገው በመተው (ሹፌሩን በማሰናበት)  እራሳቸው  በህዝብ የማመላለሻ አውቶቡስ  በመገልገል  የደሃው ህዝብ አካል መሆናቸውን   አስመስክረዋል፡፡
(ወደእኔ ይመጡ ዘንድ ህጻናትን አትከልክሏቸው፡-አባ ፈራንሲዮስ ህጻን  ልጅታቅፈው)
በአጠቃላይ አኗኗሯቸው  ቀለል ያለ ኑሮን የሚመርጡት ብጹነታቸው የላቲን አሜሪካ  ካፈራቻቸው  የመጀመሪያው  የሮማ  ካቶሊክ ፓፓ ሲሆኑ እርሳችው መመረጥም  በቤተክርስቲያኒቱ  ውስጥ  ላላፉት 1300 አመታት ከአንድ አካባቢ (ከአውሮፓ ብቻ ) ይመጣ የነበረው የፓፓነት  ስርአትን   በመለወጥ  ፋኖ ወጊ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ይመስላል በአሜሪካ:  በአፍሪካ  በደቡብ አሜሪካ እና በእሲያ  የሚገኙ  በቢሊዮኖች  የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዩች   እንዲሁም በርካታ የአገር መሪዎች  የብጹነታቸው ምመረጥን (viva il papa !!) በማለት  እንደ ታላቅ ድል የቆጠሩት ፡፡ብዙዎችም ፓፓው ድህነትን በማስወገድ  ዘመቻ እንዲሳተፉ ተማጽነዋቸዋል፡፡ ምንም እንኳን በጹነታቸው  በግላቸው ለምእመናኑ እና  ለደሃው ህዝብ ቅርብ የሆኑ  መንፈሳዊ አባት  ቢሆኑም  የትውልድ አገራቸው  አረጀንቲና በ1970ዎቹ  እኤአ  በነበረው ወታደራዊ  ጁንታ ሳቢያ  አገዛዙን  በመቃወማቸው ብቻ ህይወታቸውን  ላጡ ከ30,000 በላይ  ሰላማዊ
ዜጎች  ቤተክርስቲያኒቱ ተቃውሞዋን አላሰማችም  የሚል ብርቱ  ወቅሳ ቀርቦባታል፡፡ይህንንም ወቀሳ በተመለከተ አቡነ ፍራንሲስ  በ2010 እኤአ በአርጀንቲና ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ አስተያየት  አርሳቸው ሰዎች እንዳይታሰሩ  ሙያቸውን  በመቀየር እንዲደበቁ ወይም አገራቸውን ጥለው  እንዲሄዱ በማደረግ የታሰሩትም እንዲፈቱ በመሟገት የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸውን በመግለጽ ውንጅላውን አስተባብለዋል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት   በአንዳንዳንድ ምግባረ በልሹ ካህናት  የተነሳ ከሙስና  እንስቶ ጨቅላ ህጻናትን  የመድፈር  እና መሰል  ክሶች የቀረቡባት  የሮማ ካቶሊክ  ቤተክርስቲያን  በቤቷ  ውስጥ የተጋረጡት  ችግሮችን  ለመቅረፍ የአቡነ ፍራንሲስ  ወደ ቤተክርስቲያኒቱ በአባትነት  መምጣት  መልካም አጋጣሚ ቢሆንም  አባጣ ጎባጣ የሆኑ መንገዶችን ለምጥረግ  በርቱ  ፈተናዎች ከፊታቸው  የጠብቋቸውል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የብጹነታቸው  የግል ታሪክ ጸሃፊ የሆኑት  ሴርጆ ሩቤን  ሰለአዲሱ ፓፓ  ባህሪ ሲገልጹ  “በእሁኑ ወቅት  በለውጥ ጎዳና ላይ ያለን ይመስለኛል ፡፡ይህ ሁኔታ  ግን ቀላል  አይደለም፡፡ብጹነታቸው ቤተክርስቲያኔቱ  ወደ አደባባዮች(ጎዳናዎች) መውጣት  ስትችል  ብቻ ነው የህዝቡን ችግር መረዳት የምትችልው ብለው ያምናሉ( poor Church for the poor )፡፡” ሲሉ ተናግርዋል፡፡ በደግነታቸው  እና በእውነተኛ ርህራሄያቸው  በበርካታ የካቶሊክ  ማህበረሰብ ዝንድ  እውቅና ያገኙት አቡነ ፍራንሲስ  የፓፓነቱን ስልጣን ከያዙ  በሁዋላ እንኳን  ያ ደግነት የተላበሰ ባህሪያቸውን ባለመለወጥ ሰሞኑን ከእርሳቸው ጋር ለሚኖሩ  ካህናት  እራሳቸው  ምግብ  አብስለው በማዘጋጀት እራት እንዲቋደሱ አድርገዋል፡፡ አርፈውበት በነበረ አንድ ሆቴል ውስጥም ለተስተናገዱበት ወጪ  ከገዛ ኪሳቸው ገንዘብ በማውጣት  ከዚህ ቀደም የነበረውን የቀይ ምንጣፍ እና ልዩ መስተንግዶ ባህልን  ወደጎን አድርገውታል፡፡
ብጹነታቸው  ባለፈው አርብ ጠዋት ላይ  በቫቲካን ከተማ  ከሚገኙ  የዝቅተኛው  ማህበረሰብ ክፍል ከሆኑት  (ብሉ  ኮላርስ )  እየተባሉ ከሚጠሩት  የቤተመንግስታቸው  አትክልተኞች እና  የጽዳት  ሰራተኞች  ጋር  በጋራ  በመሆን  የህብረት ጸሎት ያደረሱ  ሲሆን በስተመጨረሻም አያንዳንዱን ሰራተኛ  በግል አነጋግረዋል፡፡ለወትሮው  ለጳጳስ  ወደ ተዘጋጀው  የክብር መቀመጫ ከመሄድ  ከምእምናን  በስተሁዋላ  በመቀምጥ  እንደተራው ምእመናን  ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ  የጋራ ጸሎት  አድርገዋል፡፡ ሰሞኑን ምእራባዊያኖች ባከበሩት የ40 ቀናት እና 40 ሌሊት  ጾም(የሁዳዴ ጾም)  ክፍል አንዱ የሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከሃዋራቱ ጋር የመጨረሻውን እራት(Lord’s Supper) የበላበት እና  የሃዋሪያቶቹን እግር በማጠብ  እነርሱም የእርሱን እርያነት እንዲከተሉ ትህትናውን ዝቅ ብሎ  ያሳየበትን  ምእራፍ በማሰታውስ  ብጹነታቸው ካሳል ዴል ማርሞ (Casal del Marmo) በተባለ የወጣት አጥፊዎች እስር ቤት በመሄድ ከህግ ታራሚዎቹ ጋር  አብረው እንደሚያሳልፉ  ከቫቲካን የወጣው መግለጫ  ያመለክታል፡፡
የቤተመንግስት  ነገር ከተነሳ  ከላይ እንደተገለጸው  ቀላላ ኑሮን ዘወትር የሚመርጡት  ብጹነታቸው አሁንም ወደ ቫቲካን  ተዛውረው  “በቤሊዮን የሚቆጠረው  ምእመናን አባት በመሆኖት ለክብሮት ሲባል የቀድሞው የአቡነ ቤኔዲክት 16ኝውን  ሆነ የቀደምት አባቶች ቤተመንግስትን ይረከቡ” ቢባሉም አሻፈረኝ በማለት  በፓፓው ምርጫ ሰሞን እዚያው ቫቲካን ውስጥ አርፈውበት በነበረው ባለ ሁለት ክፍል ሆቴል ውስጥ  ለጊዜው መቀመጥን  መምረጣቸው ተነግሯል፡፡ይህ ማለት ቤተመንግስቱን ሙሉ በሙሉ አይጠቀሙሙበትም ማለት ሳይሆን  ከመደበኛ ስራዎቻቸው መካከል አንዱ የሆኑት እንግዶችን ለምቀበል ስብስባዎችን ለማካሄድ  ወደ ጽፈት ቤታቸው ጎራ ማለታቸው አልቀረም፡፡  አብዛኞቹ ባለስላጣናት ስልጣን በያዙ ማግስት ዘመድ አዝማዶቻችውን  ለመጥቀም ሲሯሯጡ  ወይም ቀደም ሲል አስቀይመዋቸው የነበሩ ወገኖችን ለማባረር አሌያም ከእነአካቴው ለማጥፋት ላይ ታች በሚሉበት   አሁን ባለንበት በ21ኛው  ክ\ዘመን  በየትኛውም ጎራ ይሁኑ በየትኛውም ስፍራ አንደ አቡን ፍራንሲስ  የመሰለ መንፈሳዊ አባት ማግኘት  ለሃይማኖቱ ተከታዩች ብቻ ሳይሆን እምነት ለሌላቸውም(አለማዊያን) ቢሆን  ጥሩ አርእያ መሆኑ የሚቀር አይመስልም፡፡  (tamgeda@gmail.com)

No comments:

Post a Comment