Translate

Wednesday, October 24, 2012

ወ/ሮ አዜብ ቤተ-መንግስቱን ለቀቁ


ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በ አቶ መለስ ምትክ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመረጠች ወራት ቢቆጠሩም ፤ ተሿሚው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለረዥም ቤተ-መንግስት መግባት ሳይችሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ከ አቶ መለስ ሞት ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ዘግይቶ የተሾሙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር  ወደ ቤተ-መንግስቱ መግባት ያልቻሉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደነበርም ይታወቃል።
በዚህም ምክንያት አቶ  ሀይለማርያም ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ ለመሥራት በመገደዳቸው ወደ ሥራ ሲወጡና ሲገቡ በሚደረግላቸው አጀባ መንገዶች እየተዘጉ፤ ህብረተሰቡ ለእንግልት ሲዳረግ መቆየቱ በ ኢሳትና አገር ቤት በሚታተሙ ጋዜጣዎች የተዘገበው ከሳምንት በፊት ነበር።
የወይዘሮ አዜብ፡የቅርብ ጓደኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው  የዛሚ ኤፍ ኤም ባለቤት ወይዘሮ ሚሚ ስብሀቱም  የአቶ መለስ 40 ሳያልፍ የዚህ ዐይነት ነገር መነሳቱ  አግባብ እንዳልሆነ በመጥቀስና በጋዜጦቹ ዘገባ በመቆጣት፦<<መረጃውን ለጋዜጣ የሰጡት እርሳቸው ከሆኑ የሚያሳዝን ነገር ነው>> በማለት አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ወቅሰዋል።
የ ኢዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ መንግስት አለመግባት ከኢትዮጵያውያን አልፎ የውጪ ሚዲያዎችን ሁሉ ትኩረት ስቧል።

በኮሜዲ ፕሮግራሞቿ  የምትታወቀው ናይጀሪያዊቱ ጋዜጠኛ  አዶላ ባሳለፍነው ሳምንት ካቀረበቻቸው ስላቃዊ ፕሮግራሞቿ መካከል አንዱ ይኸው የወይዘሮ አዜብ መስፍን ቤተ መንግስትን ለመልቀቅ እምቢተኛ መሆንና- የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር  የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ቤት አልባ ሆኖ መንከራተትን የሚያመለክት ነበር።
ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ነው ወይዘሮ አዜብ ሰሞኑን ከቤ መንግስት መልቀቃቸው የተሰማው።
ሳምንታዊው ሰንደቅ እንደዘገበው  በ አሁኑ ጊዜ ቤተ መንግስቱ በመለቀቁ ፤ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ቤተሰቦቻቸው መኖሪያቸውን በቅርብ ቀናት ወደቤተመንግሥት ያዛውራሉ።
ኢሳት ለወ/ሮ አዜብ መስፍን በስድስት ኪሎ የስብሰባ ማእከል ጎን ባለ ሰፊ መሬት ላተለዋጭ ቤተመንግስት ሊገነባላቸው እንደሆነ መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment