ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ቆይተው የተለቀቁት የስዊዲን ጋዜጠኞች የታሰሩበት እስር ቤት በእስረኛ ብዛት ከ200 በመቶ በላይ የተጨናነቀና በሽታ የበዛበት መሆኑን ጋዜጠኞቹ አስታወቁ::
በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩበት እስር ቤት ከ200 በመቶ በላይ መያዝ ከሚችለው በላይ የተጨናነቀና ፍጽም ቆሻሳ መሆኑ ተገለጸ::
በእስር ቤቶቹ አይጦችና ዝንቦች ለታሳሪዎች መከራ መሆናቸውንም ቢቢሲ ጋዜጠኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል::
በኢትዮጵያ እስር ቤቶች 400 ቀናት አሳልፈው የተፈቱትን ስዊዲናዊ ጋዜጠኞችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩባቸው እስር ቤቶች፤ ውሀ የሌለባቸው፣ በከፍተኛ ወበቅ የነደዱና ተባይ የበዛባቸው በመሆናቸው፤ ብዙ ሰዎች ይታመማሉ የሳምባ ነቀርሳም ሌላው ችግር ነው ብለዋል::
በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት 11 አመት የተፈረደባቸውና ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ ጠይቀዋል በመባል ከ400 ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በሆላ የተለቀቁት ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬና ጆሀን ፒርሰን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ እስራት የፈረባቸው ፍርድ ቤት የችሎት ሂደት ቀልድ ነበር ብለዋል።
የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፍርዱ ከመሰጠቱ 20 ቀን በፊት በብሄራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው፤ ፍርድ ቤቱ ወንጀለኛ ሳይለን ወንጀለኛ ስለመሆናችን መግለጫ ሰጥተው ነበር ብለዋል::
ማርቲን ሽብዬና ዮሀን ፒርሰን በኦጋዴን በኢትዮጵያ ሰራዊት መሳደዳቸውንና፤ በመጨረሻ በእሩምታ ተኩስ ብዛት ማርቲን ትከሻዉ ላይ ጆሀን ደግሞ እጁ ላይ ተመተው መያዛቸውን ተናግረዋል::
አሸባሪና ወንጀለኛ መሆናቸውን አምነው እንዲናገሩ ተለማምደው ለቀረጻ መዘጋጀታቸውን የገለጹት ሁለቱ ጋዜጠኞች የኦጋዴ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት የሀሰተኛው ፌልም ዳይሬክተር ነበሩ ካሉ በኋላ፤ በመጀመሪያ በተቀረጹት ፊልሞች አለመርካታቸውን ገልጠው በድጋሜ ተለማምደው እንዲቀረጹና ለቴሌቭዥን እንዲውል አደርገዋል ብለዋል::
እንደ እስቲቨን ስፒልበርግ ፌልም በተለያዩ ሁለት ቦታዎች እያመላለሱ እንደቀረጿቸው በምጸት የተናገረው ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ በስራው አልተደሰትንም ነገ እንደገና አሸባሪ መሆናችሁን እየገለጻችሁ ሀጥያታችሁን ትናዘዛላችሁ መባላቸውን አስረድቶል::
No comments:
Post a Comment