Translate

Saturday, October 27, 2012

ወያኔ/ኢህአደግ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል ግንባሩን ከማዳከም አልፎ ወደ መግደል እያመራ መሆኑን የወያኔ ልሳን የሆነው ሪፖርተር አስጠነቀቀ


የህወሃት የቀድሞ ታጋይና በመጀመሪያዎቹ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴለቪዥንን መሥሪያቤትን ለረጅም ጊዜ በሃላፊነት ሲመራ የቆየው አማረ አረጋዊ ንብረት የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ረቡዕ ር ዕሰ አንንቀጹ እንዳሰፈረው ህዝብ በሃዘን ወቅት ስላዘነና በደስታም ጊዜ በጋራ ስለ ጨፈረ ከወያኔ / ኢህአዴግ ጋር ያለውን ግንኙነት በአወንታዊ መልኩ አንጸባረቀ ማለት አለመሆኑንና ይልቁኑም በበርካታ ችግሮች ምክንያት ልቡ ከድርጅቱ መራቁን በመግለጽ የቀድሞ ጓዶቹ ሳይመሽባቸው መልሰው የሚጠናከሩበትን ዜዴ አጥብቀው እንዲሹ አሳስቦአል።
ወያኔ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንካራ ነኝ እያለ ራሱንና አንዳንድ የዋሆችን ለማታለል ቢሞክርም እውነታው ግን ፍጹም የተለየና በሌላ ጽንፍ ያለ መሆኑ ያሳሰበው ሪፖርተር ወያኔ / ኢህአዴግ ደፋርና ቆራጥ የውስጥ ትግል አካሂዶ ካልተስተካከለ በስተቀር በስብሶ መደርመሱና የነበረው እንዳልነበረ መሆኑ አይቀርም በማለት አስጠንቅቆአል።
ሪፖርተር የቀድሞ የትግል ጓዶቹንና እስከ ደርግ መውደቅ የታገለለትን ፓርቲውን ከውድቀት ለማዳን ተጨንቆ በጻፈው በዚህ ርዕሰ አንቀጽ በእርግጥ ከተቃዋሚዎች አንጻር ሲታይ ግንባሩ የተሻለ አንድነት ቢኖረውም ወቅቱ ከሚጠይቀው አኳያ ግን የውስጥ አንድነቱ ደካማ  ስለሆነ ይህንን  እውነታ ከግንዛቤ በማስገባት እራስን ከማታለል ተቆጥቦ የቀድሞ አንድነትን በቶሎ መመለስ የተገባ ነው ብሎአል።

ሪፖርተር አንድነቱን በመጠበቅ ከተቃዋሚው ይሻላል በማለት ለማወደስ የሞከረውን ፓርቲ ዞር ብሎ ደግሞ አራቱም የኢህአዴግ ድርጅቶች ማለትም ህወሃት፣ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን በየውስጣቸውም  ሆነ እርስ በእርሳቸው ባላቸው ግንኙነት አንድነት የላቸውም፤ የተሻለ አንድነት የነበረው ህወሃት እንኳን ያ አንድነቱ  ዛሬ በውስጡ የለም በማለት የመለስን ሞት ተከትሎ ወያኔ ኢህአደግ ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል መደበቅ ከማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን አረጋግጦአል።
ወያኔ / ኢህአዴግ ዛሬ ከላይ እስከ ታች በሙስና ተጨማለቋል፤ ይህ  ድርጅቱን አበስብሶ የሚገድለው ነው ያለው ጋዜጣው፣ ሙሰኞቹ ባለስልጣናት ደግሞ አቅመ ቢስና ምላሰ ብዙ ናቸው፤ ምክንያቱም በወያኔ መንግስት ውስጥ በብቃት መመደብ እየቀረና አቅም ባይኖረውም ደጋፊ እስከ ሆነ ድረስ ችግር የለም በሚል የሚመደብ መሆኑ ነው።እናም ሁኔታው ህዝብ በወያኔ መንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው አድርጓል ሲል አስረድቷል።
እንደ ጋዜጣው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚባለውም ከእቅድ አልፎ በይዘት እየተተገበረ አይደለም፤እንዳውም በብዙ ቦታዎች በእቅዱ ስም ገንዘብና ንብረት እየተዘረፈ ነው በማለት የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ስለ ትራንስፎርመሽኑ ስኬታማነት የሚለፍፉትን ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ባዶ መሆኑን አጋልጦአል።
ወያኔ ላለፉት 21 አመታት በአገሪቱ ፍትህና እኩልነት አስፍኛለሁ በማለት የሚነዛውን ውሼት ዋጋ ብስነት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያጋለጠው ሪፖርተር “በፍትህ ረገድም ምንም ተስፋ የለም። ፍትህ ጨርሶ ጠፍቷል።ህዝብ አቤት የሚልበት ቦታ የለውም። የሚያነጋግረው ሹምም የለም “በማለት ድርጅቱ በአስተዳደር በደልና በንቅዜት ወደ መጨረሻው ግባተ መሬቱ እያመራ መሆኑን  በማስጠንቀቂያነት መልክ ይፋ አድርጎአል።

    No comments:

    Post a Comment