Translate

Friday, October 26, 2012

አጫጭር ወሬዎች


አቤ ቶኪቻው

አንድአጫጭር ወሬዎች
በመጀመሪያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ እንኳን ለኢድ አልድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ነገ የአረፋ በዓል በሚደረግባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች በሙሉ ለኢህአዴግ ሁለተኛው ቢጫ ሊሰጠው መሆኑን ሰምቻለሁ።
አዲሳባ ስታድየምን ጨምሮ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “መንግስት ከሀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ” ብለው ለብዙኛ ጊዜ ደግመው ሊነግሩት ተነስተዋል። ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በመዋላቸው “ሊለቀቁ ይሆን” የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ አጭሮ ነበር። ነገር ግን ክሱ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መዛወሩን ዛሬ ሰምተናል።

ሁለት ቢጫ እንደ ቀይ ይቆጠራልና መንግስት አጨዋወቱን ቢያሳምር ጥሩ ነው ብለን እንመክራለን! (መምከር አይደክመን!)
ሁለት
ብሄራዊ ቡድናችን ደቡብ አፍሪካ ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ከናይጄሪያ፣ ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ ጋር ተመደበ።
እንደ ስያሜው “ዋሊያ” ከሀገር ወጥቶ የመታየት እጥረት ሲፈታተነው የነበረው ቡድናችን ባለፈው ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ሲያረጋግጥ የመንግስት ሰዎች ውጤቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታሰቢያ ሲያደርጉት የፌስ ቡክ ሰፈር ልጆች ደግሞ “መለስ ሲሞቱ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፍን ኢህአዴግ ቢወርድማ ለአለም ዋንጫ እናልፋለን ማለት ነው!” ሲሉ ማሽሟጠጣቸው ይታወሳል (የማይታወስ ከሆነ ይታወስ!)
እዝችው ላይ አንድ ወዳጄ ባደረሰኝ ወሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሱዳንን ከአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጪ ባደረገበት ወቅት በሱዳን፤ ሱዳንያውያንን አግብተው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርቶች ትዳራቸው አደጋ ላይ ወድቆ ነበር ብሎኛል። እንደ ወዳጄ ገለፃ በዚህ የተነሳ የተፋቱ ሁሉ አሉ ብሎ ምሎ ነግሮኛል። በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ወሬ ከተገኘ አመጣዋለሁ!
ሶስት
ምንድነው የምሰማው? በአዲሳባ አንድ ባለ ክላሽንኮቭ ሰውዬ ከዚህ በፊት አግብቷት ከዛም “በቃ ይቅርብን ይቅርብን” ተበብለው የተፋቱትን የሁለት ልጆቹን እናት በጥይት ደብድቦ ገደላት የሚባል ወሬ ሰማሁ!
እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ተገዳይ ፍሬህይወት ታደሰ ህይወቷን ያጣችው ፖሊሶች አጠገብ ነው። ከሪፖርተር ልቀንጭብላችሁ…
…ከኋላቸው ከፍተኛ የሆነ የተሽከርካሪ ጥሩንባ በመስማታቸው፣ ሟች ‹‹ምንድነው?›› ብላበመኪናዋ ስፖኪዮ ስትመለከት ተጠርጣሪው መሆኑን ማወቋን የገለጹት እናቷ፣ ‹‹እሱ ነው››በማለት ወደፊት እየፈጠነች ነድታ ደንበል ሲቲ ሴንተርን እንዳቋረጠች ፖሊሶች በማየቷስታቆም፣ ገዳይ እንደበረረ መጥቶ በመውረጃዋ በር በኩል መኪናውን በማስጠጋት የእሷ በርእንዳይከፈት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
እናቷ ባሉበት በር በኩል እንድትወጣ ቢስቧትም አሥራው የነበረው የአደጋ መከላከያ ቀበቶከነበረው ድንጋጤ ጋር ተዳምሮ አልፈታ በማለቱ፣ ተጠርጣሪው ክላንሽኮቭ ጠመንጃበማውጣት ውስጡ ያሉ ጥይቶችን እንዳርከፈከፈባት አስታውቀዋል፡፡     
ይሄ ሁሉ ሲሆን ተማምናቸው መኪና አጠገባቸው ያቆመችው ፖሊሶች ምን እየሰሩ ነበር? እግዜር ይወቀው!
ለማንኛውም ለፍሬህይወት ቤተሰቦች መፅናናትን፣ ለገዳይ መፀፀት እና ጥሩ ቅጣትን፣ ለፖሊስ ቅልጥፍና እና ነቃ ማለትን እመኛለሁ!

No comments:

Post a Comment