Translate

Saturday, October 20, 2012

መሬት ዘረፋ ኢትዮጵያዊያኖችን በ‹‹ዓለም የረሃብ ቀን›› ወቅት ለችጋር እያጋለጠ ነው፡፡


ልጁ በታችኛው ኦሞ ወንዝ ጠርዝ ላይ
በኢትዮጵያ በታችኛው ኦሞ ሸለቆ በውጭ አገር ባለሃብቶች የሚካሄደው የመሬት ዘረፋና ሽሚያ ተወላጆቹን እያፈናቀለ እና መሬታቸውን እንዳያርሱ እንቅፋት እየሆነ በርካታዎችንምSuvival International PR Release Translationበችጋር እያመሰ ‹‹ሞታቸውን እንዲጠብቁ›› እያደረገ ነው፡፡
በኦክቶበር 16 የ “ዓለም የምግብ ቀን”ን  በማክበርና ከድህነት በስተጀርባ ያለውን ችጋር በሕዝብ ሕሊና ውስጥ ለማስረጽ ደፋ ቀና በሚባልበት ወቅት፤ኢትዮጵያን በሚገዙት ኢሰብአዊዎች፤ 200 000 በራሳቸው የሚተማመኑትን ዜጎች የምግብ ዋስትና ለማሳጣት ደንቃራ እየሆኑ ነው፡፡

የሱሪ፤ ሙርሲ፤ ቦዲ እና ክዌጉ ነገዶች በታችኛው ኦሞ ላይ ገዢው መንግስት አትራፊ የሚለውን ልማት አካሄዳለሁ በሚል፤ከቀያቸውና ሃብት ንብረታቸው፤ በማፈናቀል ሊያሰድዳቸው እያስገደዳቸው ነው፡፡ የደህንነት አባላት ከብቶቹን በጉልበት እየነጠቁና እየዘረፉ የታችኛው ኦሞን ነዋሪዎችን በጉልበት ከመኖሪያቸው እያስወጡ እያባበረሯቸው ነው፡፡
አንድ የሙርሲ ሰው ለሰርቫይቫለ ኢንተርናሽናል እንደተናገረው፤የሰፈራው ሂደት እንዴት አድርጎ ነዋሪውን ቤተሰቡን እንደጎዳ ገልጧል፡፡ ገዢው መንግሥት በጭካኔ በቆሏችንን ወደ ወንዙ እየጣለብን ነው፡፡ እርሻዎቻችንን  ነቃቅሎ ምርቶቻችንን መንጥሮ ወደ ወንዝ ጨምሮታል፡፡ አሁን የቀረኝ ጥቂት ጥሬ ነውና… ቀጥለን የምንጠብቀው ሞትን ነው ብሎል፡፡ በምሬት እያለቀስን ነው፡፡ መንግስት ሁላችንንም በአንድ መንደር ሲያግተን፤ለእርሻ ቦታ ስለማይኖረን፤ ልጆቻችን መኖርያም ምግብም  አይኖራቸውም፡፡
ሌላው የሱሪ ተወላጅም ‹‹አሁን ቦታውን አጥርተው እኛንም አባረው ጨርሰዋል፡፡ ለመሆኑ የናንተ መንግሥት ነኝ የሚለን መንግስት ለምንድን ነው የኛን መሬት የሚሸጥብን? ለከብቶቻችን ሣር የለም፤ ስፈር የተባልነው እየተራብን ነው፡፡ ለችጋር ተጋልጠናል፡፡ ስለምግብ በጣም ሃሳብ ገብቶናል፡፡ አሁንም ቁጡ እና ተስፋ ቢሶች ሆነናል፡፡››
ከኦሞ ሸለቆ
አንዲት የሙርሲ ተወላጅ ስለደረሰው እልቂትና ስለተወላጆቹ አስከሬን ትናገራለች፡፡ለደህንነቷ ተብሎ ስሟ አይጠቀስም፡፡ ቁልፉ ሰበብ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢው መንግስት የጀመረው አወዛጋቢው ጊቤ 3 ግድብ ነው፡፡ ግድቡ ተሰርቶ ሲያልቅ የኦሞን ፍሳሽ ጨርሶ ያጠፋውና ነዋሪው በፍሰቱ በመጠቀም በወንዙ ዳርቻ ላይ የሚገኘውን ለም ቦታ እንዳይጠቀምበት ያደርገዋል ከብቶቹም ግጦሽ አያገኙም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ጉዳዩ ማንንም የአካባቢውን ነዋሪ በጊቤ 3 ገድብም ላይ ሆነ ወይም በቦታው ላይ ስለታቀደው አዲስ የተክል ሁኔታ አላነጋገረም ከማንም ጋር  አልተመካከረም፡፡ ቦታው እኮ የዩ ኔ ስ ኮ የዓለም ንብረት ክልል ነው::
የሰርቫይቫል ዲረክተር የሆነው ስቲቭን ኮሪ ‹‹በዓለም የምግብ ቀን ወቅት የዓለም ሕዝብ ሊገነዘበውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ራሳቸውን ችለው ለመኖር የሚችሉትና በራስ ተማማኝ የሆኑትን የኦሞ ሸለቆን ነገዶች ለማፈናቀልና ለማጥፋት መነሳሳቱንና እንቅስቃሴውም ተጀምሮ ለብዙዎች ምግብ የለሽነት እያጋለጠ መሆኑን ነው›› ብሏል፡፡ እነዚህ ነገዶች ለዘመናት መሬቶቻቸውን ለምግብ ማፍሪያና ለከብቶቻቸው ግጦሽ ማብቀያ በማድረግ ሂደቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ነው፡፡አሁን  መሠረታዊ መብታቸው በጭካኔ መንገድ እየተገፈፈና ለፍርሃትና ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡›› ብሏል::
እነዚህ ሁለት የዳሰነች ተወላጆች ከብዙዎቹ ለመከራው ከተዳረጉ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ሰላባዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በጣም የተለጠጠ ራዕይ ይዞ ይህን አንቀበለም ያሉትን ደግሞ ከማወያየት በማዘዝና በማስገደድ፤ ከመመካከር ይልቅ በማን አለብኝነት በሠፈራ ስም በማፈናቀል  በታችኛው ኦሞ ቫሊን ነገዶች እያሰቃየና ለክፉ መከራ እየዳረጋቸው ነው፡፡ካርታው በሃገሪቱ ስላለው የእንስሳት ሁኔታ የቀረበውን ዘገባ ለማጠናከር ነው፡፡ ይህ ካርታ በስውር ለ ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል የተሰረገ ነው፡፡ይህም ኢትዮጵያ ተፈናቃይ የታችኛው ኦሞን ነገዶች ውሳኔውን ለመቀበል እምቢታ የሚያሳዩትን ለማስፈር የታቀደበትን ክልል ያመላክታል፡፡ በድብቅ የተሰረገው ካርታ፡፡ ሰርቫይቫል ሶስቱን የሰፈራ ቦታዎች አጉልቶ ምልክት አድርጎበታል፡፡ ጎሳዎቹ ከመጠን በላይ የሆነ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ የሰርቫይቫል ዲረክተር ስቲቭን ኮረ፤ ሲናገሩ: ‹‹የተሰረገው የድብቅ ካርታ የሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግሥት  በታችኛው ኦሞ ያሉትን ነዋሪ ነገዶች በግዴታ ለማፈናቀልና ለማስፈር ያለውን ደባ ነው፡፡በግዴታ የማፈናቀሉን ጉዳይ በሰፊው በሚነገርበት ሁኔታ መገንዘብ የሚቻለው መንግስት ይህን የግዴታ ሂደት እምቢ የሚሉትን በጉልበት አፈናቅሎና ከብቶቹን ነጥቆ መሬታቸውን ቀምቶ ባዷቸውን ለማስቀረት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡››
ሂደቱ የሙርሲን፤የቦዲን፤ እና የጉዌጉን ጎሳዎች እያጠፋ ያለውን ከመጠን በላይ የተንዛዛውን አደገኛ  የነዋሪዎቹን መሬትና ኑሮ ቤተሰብና ከብት በማጥፋት ላይ ያለውን እቅድ ያሳያል፡፡ (የሙርሲ መንደር፡፡)
እነዚህ ጎሳዎች ለዘመናት አያት ቅድመአያቶቻቸው ኖረውበት ካስረከቧቸውና ንብረት መስርተው ቤተሰብ አፍርተው፤ ካሉበት ቅድመ ርስታቸው መፈናቀል ማለት  ጉዳቱ መጠነ ሰፊ ነው፡፡ በቅድሚያ አሁን እንዲሰፍሩ የሚባልበት ቦታ ተወልደው ካደጉበት አካባቢ በብዙ መልኩ የተለየ በመሆኑ፤ ዘርተው ለማብቀልና ለመቋቋም አዲስ መጦች በመሆናቸው ለመሬቱ ባህል ጋር ባለመተዋወቃቸው፤ ከብቶቻቸውም የኖሩበትን ለቀው ወደ አዲስ ቦታ ሲሰማሩ ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለመታወቁ ድንጋጤና ፍርሃታቸው ከዚህ የመነጨ፤ የሞትም አደጋውን ማሰባቸው ከዚሁ በመነሳትና ሲያስቡት ተስፋ ስለሚያስቆርጣቸው ነው፡፡ ለምንም ይሁን ለምን የዜጎችን ጥቅም ማስቀደም የሚገባው ገዢ መንግሥት፤ ለነዚህ እርቃናቸውን እየኖሩ ዳር ድንበራቸውን ግን ከጠላት ለዘመናት የጠበቁትንና ደምወዝ ስጡን ቀለብ ቁረጡልንን ጨርሰው የማያውቁትን ዜጎች ጠብ ያለሽ ዳቦ ብሎ ካሉበት ድረስ ሄዶ ነገር ፍለጋ ለማን እንደሚጠቅም ማንን እንደሚጎዳ ማሰብ እንዴት ይሳነዋል::
እነዚህ ከተስፋ መቁረጥ አልፈው ረጂሙንና አድካሚውን መጪ ወቅት ሲያስቡት ባሉበት በኖሩበት፤ ወልደው በከበዱበት  ቀያቸው ሞትን መርጠው በፍራሹ ቤታቸው ሜዳ ላይ የሞትን መምጣት የሚጠጉ ዜጎች ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment