Translate
Monday, October 29, 2012
አቃቢ ህግ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ክስ መሰረተ
ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛር ከጧቱ 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችናኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ተምልክቷል።
ብርሀኑ ወንድማገኘሁ ፣ ዘረሰናይ ምስግናው እና ቴዎድሮስ ባህሩ አቃቢ ህጎች ሆነው የቀረቡ ሲሆን ለተከሳሾች ማለትም ለ29 ግለሰቦችና ሁለት ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠበቃ ሆነው የቀረቡት ደግሞ አቶ ተማም አባቡልጋ፣ አቶ ብርሀኑ ፣ አቶ ሞሀመድ አብደላና ናቸው።
የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከቀኑ 4፤30 ላይ ዘግይቶ የጀመረ ሲሆን የ31 ሙስሊም ተከሳሾችን ማየት ሲጀምር አቃቢ ህግ የክስ ፋይሉ ማህተም ይቀረዋል በማለቱ ችሎቱ ለ40 ዲቂቃ ተቋርጦ የክስ ፋይሉ ከመጣ በሁዋላ እንደገና ተሰይሟል።
አቃቢ ህግ 26 ጥራዝ የክስ ፋይል እና አባሪ ሰነዶችን በፌደራል ፖሊስ አሸክሞ ያቀረበ ሲሆን ፣ ክብደቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተከሳሾቹ ይዘውት ሊቆሙ አልቻሉም። ተከሳሾች ሰነዶችን ከአጠገባቸው አስቀምጠውም ግራ በመጋባት ጠበቆቻቸውን ይመለከቱ ነበር።
የችሎቱ ሶስት ዳኞች የተከሳሾችን ስም እየጠሩ መኖራቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ የክስ ቻርጁን መቀበላቸውን ጠይቀው ክሱን ትቀበላላላችሁ ወይስ ትቃወማላችሁ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የተከሳሽ ዋና ጠበቃ አቶ ተማም፣ አቃቢ ህግ ይህን የክስ ቻርጅ ለማዘጋጀት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ለ4 ወራት ጊዜ የ28 ቀናት ቀጠሮ እየጠየቀ 4 ወር ሙሉ ያዘጋጀውን ከባድ እና የተወሳሰበ ብዙ ዶክመንት ያሉትን ክስ ገና የመጀመሪያውን ክስ እንካን አንብበን ባልጨረስንበት ሁኔታ ተከላከሉ ማለት ስለሚከብድ ቢያንስ የአንድ ወር ጊዜ ያስፈልገናል ከደንበኞቻችን ጋር ለመመካከር እና የክስ ፋይሉን ለመመርመር ጊዜ ያስፈልገናል። ደንበኞችም የዋስትና መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል ብለዋል።
አቃቢ ህግ በበኩሉ የተከሳሽ ጠበቃ የጠየቁት ጊዜ እጅግ የተጋነነ እና ህጉ የሚለው ክሱ በቀቀረበበት ጊዜ እንዲከላከሉ ወይም እንዲቃወሙ በመሆኑ የጠበቆችን አስተያየት አንቀበልም ብሎአል።
ዳኞችም ተከሳሾች በሽብርተኝነት በመከሰሳቸው የዋስትና መብት እንደማይኖራቸው ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ማረሚያ ቤት ተዛውረው እዛ ሆነው ክሱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ እንዲከራከሩ መወሰኑንና የተከሳሽ ጠበቆችም ክሱን መርምረው መልስ እንዲያዘጋጁ የ20 ቀናት ጊዜ በመስጠት ለህዳር 13፣ 2005 ኣም ቀጠሮ ሰጥተዋል።
እስረኞች በጥብቅ ቁጥጥር ስር እንደነበሩ ለማወቅ ተችሎአል። በአካባቢው በርካታ የደህንነት አባላት ተበትነው ታይተዋል።
እስረኞቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊገቡ ሲሉ ድምጻቸውን ቀርጸዋል፣ ፎቶ ግራፍ አንስተዋቸዋል የተባሉ ሙስሊሞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment