Translate

Thursday, September 27, 2012

በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው


ኢሳት ዜና:-በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል  ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው ሲሉ የግንባሩ ቃል አቀባይ ገለጡ
የኦብነግ ቃል አቀባይ  አቶ ሀሰን አብዱላሂ  በኬንያ አደራዳሪነት ተከታታይ የሆኑ ድርድሮችን ለማካሄድ ስምምነት ላይ ቢደረስም ፣ ጦርነቱ ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
“እናንተ ከመንግስት ጋር ድርድር ውስጥ የገባችሁት ሀይላችሁ እየተዳከመ በመምጣቱ ነውን?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሀሰን ሲመልሱ ፣ ድርጅታቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ በድርድር እንደሚያምን ገልጠው ፣  ከመቼውም ጊዜ በላይ በጠንካራ ሁኔታ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል
ድርጅታችሁ ብቻውን ወደ ድርድር ከመቅረብ ይልቅ ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ብትደራደሩ ይበልጥ ሀይል አይኖራችሁም ነበር ወይ? ተብለው የተጠየቁት ቍል አቀባዩ  ፣ ከተወሰኑ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር አብረው እየሰሩ መሆናቸውን፤ ከቁሪዎቹ ድርጅቶች ጋር ግን አብሮ ለመስራት እየቸገራቸው መምጣቱን ገልጠዋል
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር የሚያደርገውን ድርድር በሚቀጥሉት 2 ወራት ውስጥ በሶስተኛ አገር እንደሚያካሂድ የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ የድርድሩን ነጥቦች ከመናገር ተቆጥበዋል።
ከአቶ ሀሰን አብዲላሂ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለምልልስ በድረገጻችን ላይ መከታተል ትችላላችሁ።

No comments:

Post a Comment