Translate

Saturday, September 29, 2012

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ሃይሎች እና በዩኒቨርሲቲ መምህራን መካከል የተካሄደው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው ። “ግንቦት ሰባት እና ግንቦት ሃያ እኩል ሊታዩ ይገባል” ተባለ




university-of-gondar-stadiumየሃይማኖት አክራሪነት እና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች በሚል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ሃይሎች የተከናወነው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው ።

በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ከሰኞ እስከ ረቡእ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምናና ጤና ኮሌጅ  ካምፓስ  ሳይንስ አምባ አዳራሽ ውስጥ የተከናወነው አጠቃላይ የአክራሪነትን እና የልማታዊ እንቅስቃሴ ስብሰባን አስመልክቶ ስብሰባውን ይመሩት የነበሩት የወያኔ አባላት በሙሉ ተቃውሞ  የገጠማቸው ሲሆን የስብሰባው ዋነኛ አቀንቃኝ እና የቀድሞው የትምህርት ሚንስትር ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካዔል ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ፤በፕሮፌሰር ይግዛው ከበደ የተባሉት የዩኒቨርሲቲው መምህር ማለትም የቀድሞው ዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት “ግንቦት ሃያ እና ግንቦት ሰባት እኩል ሊታዩ ይገባል”  ሲሉ ገልጸዋል 
በስብሰባው ወቅት በተነሳው አምባጓሮ የስልጣን ማን አለብኝነታቸውን 
                                                                                                           
                                                                                                           
                                                                                                                                   university-of-gondar-stadium   
 
ለማሳየት የሞከሩት ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካዔል አይናቸውን ወደ    መምህራኑ በማፍጠጥ የማስፈራሪያ ዛቻ እስከመስጠት ድረስ ደርሰዋል።በሌላም በኩል ከተሰብሳቢዎች በተነሱ ጥያቄዎች እና መልሶች በመነሳት መንግስት አሸባሪ የሚለዉን ተራ ቃል እየተጠቀመበት እሱ እራሱ ዜጎቹን እያሸበረ እንደሆነም ተናግረዋል ለምሳሌም ያህልም የእስቴ ህዝቦች ተትቅሰዋል።ፕሮፌሰር ይግዛው ከበደ  ከስልጣናቸው ዝቅ እንዲደረጉ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት የወያኔ አባል ሁን በሚለው የወያኔ ካድሬዎች ግብዣ ባለመቀበላቸው ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ማህበር እና ከአመራር አካልነታቸው እንዲነሱ አድርገዋቸዋል ።

በዚህ ውይይት ላይ ፕሮፌሰሩ ለተናገሩት ቃል “ግንቦት ሰባት እና ግንቦት ሃያ እኩል ሊታዩ ይገባል” የሚለው ሃሳብ ያበሳጫቸው  ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካዔል ላነሱት ሃሳብ የተቃውሞ ድምጽ ሲቀርብባቸው የተቃውሞ ድምጽ ላሰሙት መምህራ በሙሉ አጠቃላይ ተሰብሳቢው በእጅ ጭብጨባ ድጋፉን አሳይቷቸዋል። ምክንያት ዶ/ር ስንታየሁ የተሰብሳቢዉን ጭብጨባቸውን እስከማስቆም ድረስ የደረሱ ሲሆን ንዴታቸውን የሚወጡበት መንገድ እስከሚፈልጉበት ደረጃ መድረሳቸው  ከፊት ለፊታቸው ሲነበብ ይበልጥ ተሰብሳቢውን አስደስቷቸዋል።በተለይም የወያኔ ካድሬ እየተባሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚታወቁት ድ/ር ስንታየሁ የስብሰባውን አጀንዳ እስኪለቅ ድረስ በከፍተኛ ደረጃ ክርክር ውስጥ መግባታቸውን  ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ለማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ገልጸዋል።

ሌላኛው ተናጋሪ ደግሞ ህዝቡ ዝም ሲል የደገፋችሁ እንዳይመስላችሁ ይልቁኑስ ከአሁኑ እረፍት ብትወስዱ ይሻላችኋል በማለት ሃሳቡን ገልጾአል ።ይህም ሆኖ ሳለ በአሁን ሰአት ላይ በልዩነት መንፈስ ላለው ህዝብ እርቀ ሰላም ያስፈልገዋል ሁሉም ወደ አንድነት የሚመጣበት መንፈስ እንዲኖረው ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል። ሃይማኖቶችን በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበሩት መንግስታቶች በኩል ምንም ጣልቃ በመግባት የፈጠሩት ችግር እንዳልነበር የጠቆሙ ሲሆን አሁን ግን ይህ ገዢው መንግስት በህዝብ እና በሃይማኖቶች ላይ እንዲሁም ብሄሮችን በመከፋፈል ያደረገው ስራ ጥሩ እንዳልሆነ ጠቁመው ለራሱ ፓርቲ ለመግዛት እንዲያመቸው ያደረገው መሆኑን እና ከአሁን በኋላ ግን ከዚህ አስቀያሚ እና አስከፊ ስራው እንዲታገድ አሳስበዋል  ።

በተያያዘ ዜና  ሌሎች ተሰብሳቢዎች ደግሞ ወያኔ በህይወታችን ላይ ጣልቃ በመግባት በጣም አብግኖናል ህይወታችን ምስቅልቅል ብሎብናል ስለዚህ የዶ/ር ስንታየሁ መናደድ ለኛም ምን ያህል ደስታ እንደሚሰጠን እንዲረዱልን እንፈልጋለን ሲሉ ለማለዳ ታይምስ አዘጋጆች ገልጸዋል።

በዛሬው እለትም በአስተዳደር እና ሰራተኞች ላይ የሚያተኩር ስብሰባ ከአመራርአ አባላቶች እና ሰራተኞች ጋርም እንደተጀመረ ተገልጦአል።ዶ/ር ስንታየሁ የብአዴን (ANDM) አባል ሲሆኑ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው እና ከትምህርት ሚንስቴር የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር የነበሩ ሲሆን በአቅም ማነስ ምክንያት የመተማን መሬት በሸጠው ደመቀ መኮንን ቦታ ላይ እንዲተኩ ተደርገው የሚሰሩ የወያኔ ታማኝ አገልጋይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment