Translate

Friday, September 14, 2012

ጋዜጠኛ አቤ ቶኪቻው እንግሊዝ አገር ሊገባ ነው


 አቤ ቶኪቻው (አበበ ቶላ) የአውራ አምባ ታይምስ እና የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ በመሆን፤ በስላቃዊ የጽሁፍ ስራዎቹ ይታወቃል። ባለፈው አመት በነዚህ ስራዎቹ ምክንያት በአገር ውስጥ የደህንነት አባላት

Abeክትትል ሲደረግበት ቆየ። ከዚያም በደህንነት አባላቱ አማካኝነት መንግስት አቋም እንደወሰደና ከዚህ በኋላ ቀጣቱ እርምጃ እስር እንደሚሆን ተነገረው። ወቅቱ የፍትህ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ ውብሸት ታዬ እና የፍትህ አምደኛ ርዕዮት አለሙ የታሰሩበት፤ የአውራምባው ዳዊት ከበደ አገር ጥሎ የወጣበት፤ አቤ ቶኪቻውም በፍትህ ጋዜጣ ላይ በሚያወጣቸው ስራዎቹ በመንግስት የክትትል ስር የወደቀበት ወቅት ነበር።
Abebe Tola
አቤ ቶኪቻው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ነበር ባለፈው አመት አገር ለቆ የወጣው። በመሆኑም ላለፉት አስር ወራት በናይሮቢ ኬንያ በስደት አለም ነበር የቆየው። አሁን ግን የእንግሊዝ መንግስት ጋዜጠኛውን ተቀብሎታል። አቤ ቶኪቻውም ወደ እንግሊዝ አገር ሄዷል። ይህንን ዘገባ ባቀረብንበት ወቅት አቤ ቶኪቻው ወደ ማንቸስተር ሲቲ በምትበረው አውሮፕላን ውስጥ ነው። በማንቸስተር ሲቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ይህን ውድ ኢትዮጵያዊ በሚገባ ተቀብለው ያስተናግዱታል ተብሎ ይጠበቃል።

አቤ ቶኪቻው ከኬንያ ከመነሳቱ በፊት የኢ.ኤም.ኤፍ. አዘጋጆች አነጋግረውት ነበር። ለጊዜው ማስተላለፍ የፈለገው፤ “እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ አመት አደረሳችሁ!” የሚለውን መልዕክት ነው። ቀሪውን እንግሊዝ አገር ከገባ በኋላ በተለመደው ብሎግ ወይም ጽሁፎቹ የራሱን መል ዕክት ያስተላልፋል። እስከዚያው በኛም በኩል፤ እንደ አቤ… “እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ አመት አደረሳችሁ!” የሚለውን መልዕክት እናስተላልፋለን።

No comments:

Post a Comment