Translate

Saturday, September 15, 2012

ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ


ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰበር ዜና - ዛሬ እየተደረገ በነበረው የኢህ
ኃይለማርያም ደሳለኝ
አዴግ ስብሰባ ከደቡብ ህዝቦች የተወከለው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ የኢህ አዴግ ሊቀመንበር ሆኖ መመረጡን በተለይ ኢ.ኤም.ኤፍ. የደረሰው ዘገባ ያመለክታል። ይህን ዜና ባቀረብንበት ወቅት ዜናው ገና ለህዝብ ይፋ አልሆነም። የኢህአዴግ አመራር አካላትም በስብሰባ ላይ ናቸው። በመቀጠል የሚደረገው በቀድሞው የኢህአዴግን ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አዲሱ ለገሰ ምትክ ሌላ ሰው መምረጥ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ በቅርቡ ሲከፈት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የድርጅቱ ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን፤ ለጠቅላይ ሚንስትርነትም ይታጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፓርላማው ካጸደቀው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል ማለት ነው። ዝርዝር ዘገባዎችን ወደፊት እናቀርባለን። ዛሬ በነበረው ስብሰባ ግን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር ሆኖ መመረጡን በሰበር ዜና መልክ እነሆን ብለናል።

No comments:

Post a Comment