Translate

Saturday, September 29, 2012

በአቶ መለሰ የተያዘውን የአምባገነንነት ክብረወሰን አቶ ኃይለማሪያም የማይሰብሩበት ምን ምክንያት አለ?


Hailemariam Desalegn
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በአካልም በመንፈስም ከሞተ ወራቶች መቆጠር ተጀምረዋል ነገር ግን ሙዋቹ መለስ ዜናዊ የዘረጋቸው የአፈና መዋቅሮች የደነገጋቸው አፋኝ ሕጎች የዘረፋ ሰንሰለቶች አብረው ወደ መቃብፍር አልወረዱም።በዘርና በጥቅም ተሰባስበው ሀገርንና ህዝብን የሚግጡና የሚበዘብዙ የጥቂት ግለስቦች ቡድን ዛሬም በስልጣን ላይ ይገኛሉ ።አቶ መለስ የዘረጋቸውን የተለያዩ ህዝብን በጠብመንጃ አስፈራርቶ አፍኖና እረግጦ እየበዘበዙ የመኖር እስትራቴጂ ጭፍሮቹ እያፋፋሙትና እያጠናከሩት ይገኛሉ።

እነዚህን ጭንቅላታቸው ሆድ የሆነባቸውና አርቆ አስተዋይነት አይምሮ ያጡ የወያኔ አሽከሮችና የአንድ ብሄር የበላይነት ናፋቂዎችና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸው ጠባብ ትምክህተኞችን ሳይወገዱ መይም ሳይገደዱ ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን ለመመስረት መሞከር የባሰ ወያኔን ከማጠንከር ውጭ ሌላ ምንም ለውጠ አያመጣም::

በኢትዮጵያን ወገኖች አሁንም ድህነት ስደት የመብት ረገጣው ተጠናክሮ ይገኛል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍውን የኑሮ ሸክም እየተሸከመ ይገኛል።
ባሳለፍነው አመት የተጀመረው በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል አዲስ የእስልምና እምነት ከውጭ እንዳስመጣ በጉልበትም ካልተቀበላቹ እያለ እያስፈራራ አያሰረ እየገደለ እንደሆነ እያየን ነው:: አንቀበልም ያሉት ደግሞ አሸባሪ እየተባሉ ነው:: 


የኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ መንግስት እጁን ከእምነቶቻቸው እንዲያወጣ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ቢቆይም ይባስ ብሎ በሙዋቹ የወያኔ አለቃ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ እምንት ነፃነት ጥያቄ የሚያነሱትን ህዝቦች ፅረ ሰላም ፅረ ልማት ፅረ ዲሞክራሲና ፖለቲካ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የፖለቲካ አጀንዳ ያላችው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው በማለት የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በትእቢትና በንቀት ሲያጣጥሉት አይተናል:: ። ባለፈው ሳምንት በ ESAT TV የተመለከትኩት ፌደራል ፓሊስ በሙስሊም ወጣቶች ላይ ያደረሰው እጅግ ዘግናኝ አስከፊ ድርጊት የ 97 ቱን የወገኖቼን ሞትና እንግልት ያስታውሰኛል።
መቼ ይሆን እኛ ኢትዮጵያን ከዚህ አፋኝና ዘረኛ የማፊያ መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አስወግደን ወይም አስገድደን ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን የምንመሰርተው ? የማይሞቱ የሚምስላቸው አቶ መለስ የኢትዮጵያ አምላክ ሆነው ሲፈርዱና ሲያስፈርዱ ኖሩ። ዛሬስ? አፅምሮዋቸው ጠቦ የሚያስነክሳችው የወያኔ ካድሬዎች መለስ ቢሞትም ራዕያቸው ለዘላለም ይኖራል አሉ መለስን ዘላለማዊ በማድረግ የግል ጥቅማቸውንና የስልጣን ጥማታቸውን ለማርካት እየሮጡ ይገኛሉ ። አዎ መለስ መቼ ሞተና ራዕያቸውም ሕልማቸው ቅዘታቸው ውሸታቸው እራስ ወዳድነታችው እብሪታቸው የቅናትና የበታችነት መንፈሳቸው በአገራችን ተንሰራፍቶ ሕይወት ዘርቶ እስካለ ድረስ የሞተም የተለወጠም ነገር የለም።

ምንም አገራዊ ስሜት የሌላቸው ትልቅ እድል ተሰጥቶዋችው እራሳቸውን በጥሩ መንገድ ማሻሻል ያልቻሉ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸው የሚበልጥባቸው አሸማቃቂና አሳፋሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ ሕዝብ ቁማር የሚጫወቱ እንደጋሪ ፈረስ ህዝብን መምራት የሚመኙ ከየጉሬዎቻችው ተጥራርተው እንመራለን ብለዋል። እነዚህ ግለሰቦች ሕዝባችን ላይ ከፍተኛና አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምስቅልቅሎች በደል ፈፅመዋል በተለይ የትግራይ ነፃ አውጭዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜያቸውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል :: ይህ የማፊያ ቡድን ዛሬም መሪያቸው የዘራውን ዘረኝነት ማን አለብኝንትና በጠብመንጃ ለመቀጠል በ አቦይ ስብሃት አማካኝነት እየተሰባሰቡ ይገኛሉ ።

ወያኔ ከሠላሳ አመታት በላይ የተለማመዳቸው የውሸት ተክህኖት ዛሬም አልበቃም ብሎት አጠናክሮ ይገኛሉ።እውነት ተናግረው በማያቁበት ሚዲያቸው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት እየገለፁበት ይገኛሉ ።ከአውስትራሊያ በሚሰራጭ SBS ከተባለ ራዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ በረከት አቶ መለስ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ለአዲስ አመት ዋዜማ መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ከዚያም ሕልፈታቸው ከተነገረ በኃላ ነሐሴ 15 2004 ዓ.ም አቶ ኃይለማሪያም ተጠባባቂ ጠ/ሚ እንደሆኑ ተገለፀ ። በማግስቱ ነሐሴ 17 የተወካዮች ምክር ቤት ጠ/ሚ ለመሰየም አስቸኮይ ሰብሰባ እንደሚጠራ አውሩልን ሆኖም ባልታወቀ ምክኒያት ተሰረዘ። ይህ በእንዲ እንዳለ አቶ በረከት ለ ጠ/ሚ ሹመት በመስከረም ወር መጨረሻ መደበኛ ስብሰባ እንደሚጠሩ ነገሩን ፓርላማውን በአሰቸኮይ የምንጠራበት ምንም ምክኒያት የለም ብለውንም ነበር። ሆኖም በማይታወቅ ሁኔታ አስቸኮይ ስብሰባ ተጠርቶ ቅኝቱን ያልሳተው ምደባ ተካሄደ። ይህ የሚያሳየን የኢትዮጵያን ህዝብ የዋህነት ፣ ታጋሽነት ፣ ጨዋነትና ታዛዝነት ልክ እንደ ፈሪነት፣ ሞኝነትና መሃይምነት ቆጥረውት በጠራራ ዐሃይ በሬ ወለደ ውሸት እየዋሹ ምንም እውነተኛ መረጃ እንዳያገኝ እያፈኑ በጠብመንጃና ኢትዮጵያውያንን እንደፈለጉ እስርቤት በሚያጉሩበት በአራዊት ህጋቸው እያስፈራሩ የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለማረጋገጥ አቅማቸው የቻለውን ሁሉ እያደረጉ ነው ::

የአቶ ኃይለማሪያም ወደ ስልጣን መምጣት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ የሕልም እንጀራ ነው አቶ ኃይለማሪያም 18 ደቂቃ በፈጀው ንግግራቸው ውስጥ የአቶ መለስን ቅዘት ሳይመረዝ ሳይበርዝ ለመቀጠል በቁርጠኝነት መነሳታቸውን ገልፀውልናል። አቶ መለሰ ለሁለት አስረት አመታት ሲሮጡት የነበረውን ሩጭ አቶ ኃይለማሪያም ሪከርዱን የማይሰብሩበት ምን ምክኒያት አለ። የተለያዩ በትግራይ ተወላጆች የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃኖች ድህረ ገፆች የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች በተለይ ታግለን ነፃነት አመጣን የሚሉት አባይ ወልዱ እና ስብአት ነጋም ይህንኑ ሁኔታ በተለያየ ግዜ በሚሰጡት መግለጫና ቃለ ምልልስ ህወሃት ዛሬም የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪ መሆኑንና ወደፊትም መሆን እንዳለበት አይን ባወጣ መልኩና የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አጥተው እየተናገሩ ይገኛሉ።

ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) የዛሬ ሀያ አመት በወያኔ ፋብሪካ ሲመሰረቱም ሆነ ካድሬዎቻችው ሲሰበሰቡ ዋነኛ አላማው ህዝባዊ መሰረት እንዳለው በማስመሰል ብዙ መስዋትነት የተከፈለበትን የኢትዮጵያውያንን ትግል የተጠበቀውንና የታለመለትን ውጤት እንዳያመጣ አድርጎ የህዝብን ስልጣን ለመቆናጠጥ ሲባል ነበር:: ለዚህም አላማችው ብዙ ህዝብ የብዛት ያላቸውን ብሄሮች አቅም በማይፈጥሩበት አካሁዋን በወያኔ ስር እንዲደራጁ ማድረግ ነበር ይህንን አድርገውም ይኸው ስልጣናችውን ለሁለት አስርት አመታት እየተንገዳገዱም ቢሆን ቆይተዋል:: ወያኔ ይህንን የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ከሞላ ጎደል በሙሉ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የስልጣን ክፍፍሎቹን በራሱ በህወሃት ሰዎች እጅ ውስጥ አስገብቶዋል:: እጅግ በጣም ጥቂት የስልጣን መደቦችን ከሌሎች ብሄረሰቦች ለተሰባሰቡ በርቀት መቆጣጠሪያ ለሚጠበቁ የኢሀአዴግ ተብዬ ካድሬዎች ለይምሰል ሰጠ:: ነገር ግን እነዚሁ ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎች (ኦህዴድ ደህዴን ብአዴን) በሀገር ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ውሳኔ ሰጭነት ጉልበት የላቸውም:: ኢህአዴግ ለይስሙላና ለማጭብርበር ቀጥቅጦ የሰራቸው ኦህዴድ ደህዴን ብአዴን ክልላችውን ይቅርና አነስተኛ ቀበሌ እንኩዋን በክልላቸው የማስተዳደር ስልጣን እስካሁን አልተሰጣችውም::

እነዚህ ያየናቸው ተጨባጭ እውነታወች አቶ ኃይለማሪያም በህወሃት ጠባብ የፖለቲካ ርዮተአለም ተቀጥቅጠው የተሰሩ የቤተ ሙከራ ጠቅላይ ሚንስትር እንጂ በራሳቸው ስብዕና መራመድ የማይችሉ ስለመሆናቸውን አልጠራጠርም።

No comments:

Post a Comment