Translate

Friday, September 14, 2012

የከፋፈሉንን መሪ አንድ ሆነን ቀበርናቸው!

Meles Zenawi with Chines president
ከተወልደ በየነ (ተቦርነ) ነሃሴ 2004
በቅርቡ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሀገራችን የተፈጠረውን ሁኔታ ሳይ አንድ የቆየ የስለላ ታሪክ ትዝ አለኝ::
ባንድ ወቅት አንድ አሜሪካዊ የስለላ ድርጅት አባል ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እንዲሄድ ይታዘዛል በዚህም መሰረት በሶቭየት ህብረት በሚኖረው ቆይታ ምስጢራዊ መረጃወችንለመላክ ቀይና ሰማያዊ ቀለም ያላቸው ብዕሮችን እንዲጠቀም በጥብቅ ይታዘዛል ይህም የሆነበት ምክንያት በወቅቱ የነበረው የሩሲያ ስለላ ድርጅት ከሀገሩ ይወጡ ለነበሩ ማናቸውም ጽሁፎች መነበብ አለባችው የሚል ህግ ስለነበረው ነው በዚህም መሰረት ቀዩ ብዕር ትክክለኛ መረጃን ለመላክ የሚጠቀምበት ሲሆን መረጃው ሀሰተኛ መሆኑን ለመጠቆም ሰሚያዊውን ብዕር እንዲጠቀም በጥብቅ ተነግሮት ወደ ሩሲያ ያቀናል::
የሶቭየት ህብረት ቆይታውን በተመለከተም ሪፖርት ሲያደርግ ታላቋ ሩሲያ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲ፣ የዕኩልነት ሁሉም ነገር ተሟልቶ ያለባት ምቹ ሀገር እንደሆነች ገልጾ በሩሲያ ፈልጌ ያጣሁት ነገር ቢኖር ቀይ ብዕር ብቻ ነው ብሎ ረፖርቱን አጠቃለለ::
ወደ እኛ ሀገር ስንመለስ እውነት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአ
መራር ብቃት፣ ጀግንነት፣ ብልህነት፣ አርቆ አሳቢነት ሰሞኑን እየተባለ ያለው ብቻ ነው ከተበለ ትክክል አይመስለኝም ምክንያቱም እውነቱን ለመፃፍ እንደ አሜሪካዊው ሰላይ ቀይ ብዕር ካላጣን በስተቀር ወይም በነበረው ፕሮገራም መጣበብ ምክንያት ተዘሎ ካልሆነ በቀር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ 21 ዓመት ያመራር ዘመናቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነውን የኢትዩጵያን ሠራዊት የበተኑ፣ ኤርትራን ያስገነጠሉ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የወደብ አላስፈላጊነትን በልበሙሉነትና በብልህ ያመራር ብስለት ያስረዱ ታላቅ የማይተኩ መሪ ናቸው::
በተሳሳተ የትምርት ፖሊሲ ዓንድ ትውልድ ያመከኑ ባለ ራዕይ መሪ ነበሩ::
በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት 80ሺህ ኢትዩጲያዊያን ወታደሮችን ያስፈጁ እና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እደራደራለሁ ያሉ መለኪያም መተኪያም የማይገኝላቸው ታላቅ የሀገር ሀብትም ነበሩ::
በ1997 ምርጫ በሰላማዊ መንገድ በካርዱ ያሸነፋቸው ህዝብ ላይ አነጣጥሮ ገዳይ ያዘመቱ ልበ-ሙሉ ጀግናም ነበሩ:: ታድያ ይሄ ሁሉ ታላላቅ የጀግንነት የብልህነት ያስተዋይነት ብቃታቸው ታሪክ ተዘሎ መታለፍ አግባብ አይደለም ምክንያቱም በነዚህ ምክንያቶች የፈሰሰው እንባና ደም ለቀብራቸው ከፈሰሰው እንባ በተሻለ የሳቸውን ብቃት ያሳያል የሚል እምነት ነበረኝ::
ለማንኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የከፋፈሉት ህዝብ አንድ ሆኖ በናቁት ሰንደቅ ዓላማ ጠቅልሎ ባዋረዱአት ቤተከርስቴያን ቀብሯቸዋል:: ወርቅ ከሆነው የትግራይ ህዘብ የተፈጠሩት ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ አሁን የሉም በዘር በሀይማኖት እንዲከፋፈል የደከሙለት ህዝብም አንድ ሆኖ እሳቸውን ቀበረ ስለዚህ ሟች በከንቱ ደከሙ:: ነፍስ ይማር!

No comments:

Post a Comment