Translate

Monday, September 10, 2012

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለ17 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለዩኒቨርስቲ መምህራን ይሰጣል


ኢሳት ዜና:-የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የመንግስት ሰራተኞችን በመጋበዝ፣ ለግንባሩ ያላቸውን ተአማኒነት በይፋ እንዲያረጋገጡ የነደፈው ስትራቴጂ በዩኒቨርስቲ መምህራን ይጀመራል።
የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በቀጥር 259/2311/04 በቀን 10/12/2004ዓም በላኩት ደብዳቤ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 20 /2005 ዓም የሚቆይ አገር አቀፍ ስልጣን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደሚሰጥ ገልጠዋል።
በዚህም መሰረት የነባርም ሆነ የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ከመስከረም 20 ቀን 2005 ዓም በፊት እንዳይደረግ፣ ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመሆን ተስማሚ የስብሰባ ቦታ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች እንዲያመቻቹና ለትምህርት ውጭ አገር ከሚገኙት መምህራን በስተቀር ሁሉም በስልጣነው ላይ መገኘት ግዴታ መሆኑን ሚኒሰትር ዲኤታው አሳስበዋል።

ለዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጣና እንዳለቀ፣ የሁለተኛ እና የአንደኛ ደረጃ መምህራን ስልጠና እንደሚቀጥል ታውቋል።
ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን በአመቱ መጨረሻ ላይ ለስብሰባ በመጥራት የግንባሩን ፕሮግራም እንዲቀበሉና  የድርጅቱን የአባልነት ቅጽ እንዲሞሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
የኢህአዴግ አባል አንሆንም በማለት ያንገራገሩትን መምህራን ከስራ ከመባረር ጀምሮ የተለያዩ የደረጃ እድገቶች እንዳይሰጣቸው ሲያደርግ መ ቆየቱም ኧይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት ላይ በቂ ትብብርና በቂ ሀዘን አላዘኑም የተባሉ መምህራን እየተወከቡ ነው።
በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ መምህራን በክልል የወረዳ ባለስልጣናት እየተጠሩ_ በአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት ላይ ስለነበራቸው አቋም መጠየቃቸውን የአማራ ክልል ዘጋቢያችን ገልጧል።
በመንግስት እና በመምህራን መካከል ያለው ፍጥጫ ባለፈው የካቲት ወር ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ነበር ።
ፍጥጫውን ተከትሎ መምህርት ረድኤት አሰፋ ፣ መምህርት ትዕግስት አየለ ፣ መምህር ኩራባቸው በለጠ፣  መምህር በለው አክሊሉ እና መምህር ዮናታን ፈለቀ በፖሊስ ሲታደኑ መቆየታቸውና እስካሁንም አድራሻቸው አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
ኢህአዴግ ተቀባይነቱን ለማረጋጋጥ ከመምህራን ሌላ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞችንም እየጠራ እንደሚያነጋገር ታውቋል።

No comments:

Post a Comment