Translate

Sunday, September 9, 2012

ዜማ እስኪታደስ ጀሮ ዳባ ልበስ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት ነበሩ አሁንም ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተናዊ ዕድገት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት (ፓትርያርክለቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙት አህጉረ ስብከት፣ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ከጳጉሜን 1ቀን 2004 .ም ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2005 .ም ድረስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል”  ይላል።
ወደ ደብዳቤው ይዘትና መንፈሱ ዘልቀን ከመግባታችን በፊት እንዲሁም ጸሐፊው ደብዳቤውን ተንተርሰው ለማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በቀላሉ ለማግኘትም ይረዳ ዘንድ ለመንደርደሪያ ያክል ስለ መዝሙረኛው አሳፍ ጥቂቱ ልበላችሁ። አሳፍ ማለት በዳዊትና በሰሎሞን ዘመን የነበረ የመዘምራን አለቃ ሲሆን ያን ዘመን ሲጠራም ከዘመኑ እኩል በዳዊትና በአሳፍ ዘመን” ተብሎ ስሙ የሚጠራ ብርቅ የእግዚ አብሔር ሰው ነበር:: አሳፍ በንጉሱ ፊት የሚቆምእጅግ የላቀ ክብርና ልዩ የዝማሪ እንዲሁም የድርሰት ተሰጥኦ ያለው የእግዚአብሔር ባሪያ ሲሆን ይህን ቅባቱም ዘሩ ጭምር የወረሰ ስጦታ ነበር:: በመዝሙረ ዳዊት ከተካተቱ ዝማሪዎች መካከልም ወደ አስራ ሁለት የሚደርሱ በዚህ ሰው የተደረሱ/የተጻፉ ናቸው::
እንግዲህ የእግዚአብሔር ሰዎች በቀላሉ የሚደርሱበት ቦታም ሆነ የሚያስመኝ ህይወት አያልፉምና ይህም ሰው በአንድ ወቅት “እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ … በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ … ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው … አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ1 ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና።” እስከ ማለት ደርሶ በተለይ አመጸኞች በቅንና ደጋግ ሰዎች የሚፈጹምትን በደል እያየና እየተመለከተ ምን ነው ፈጣሪሲል ራሱን ሲረብሽና  ስምታውንም ለእግዚአብሔር ሲያቀርብ የምናገኘው።

ሰው ከልብ በሆነ ሐዘንና የህይወት ስብራት የተነሳ ያመረረና ያለቀሰ እንደሆነ እግዚአብሔር ካልደረሰለት ቀጣይ እርምጃው ገመድ ነው የሚሆነውና እግዚአብሔር ወደ አሳፍ ህይወት መጣ። ታድያ አመጣጡ ለኤርምያስ በመጣበት መንገድ በመምጣት እንዲጸልይ አልተናገረውም። ይልቁንስ ባስጨነቀው ጉዳይ ላይ ብዙ ከማሰላሰል የተነሳ ራሱን ወደ ከፋ አደጋ እንዳይጨምር ጉዳዩን በሚገባ ያስብበት ዘንድ ነበር ያነቃቃው። በዚህ ቅጽበት ነበር እንግዲህ አሳፍ የጾም ጸሎት ጊዜ መድቦ በር ዘግቶ መጮህ ሳያስፈልገው ችግሩና የችግሩ መፍትሔ ዓኑን ከፍቶ ማየት የጀመረው። እንዲህም አለ የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው። እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው። ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።” ውድ አንባቢ እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባ ዋና ነጥብ ቢኖር ድሮም ችግሩ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የሚፈታ ጉዳይ አልነበረምና አሳፍ ወደዚህ እረፍትን ወደሚሰጥ ድምዳሜና ወሳኔ የደረሰበትን ምክንያት ሲገልጽ እንዲህ ብሎ ነበር “ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ (እይታዬን እስካስተካክል ድረስ)፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ” በማለት ከማስተዋል ጉድለት የተነሳ ራሱን ለአደጋ አጋልጦ እንደነበር እንመለከታለን።   
ጥበብ በዚህ አለችግር ሁሉ በጸሎት አይፈታም:: ይህ ማለት ግን ጸሐፊው በምንም ዓይነት ሁኔታ ጸሎት አያስፈልግም እያሉ እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል:: እየተባለ ያለው አንድ ሰው ካጋጠመው ከአቅሙ በላይ የሆነ ሁኔታ/ችግር የተነሳ ለጸሎት ከመነሳቱ በፊት ቢያንስ ቢያንስ ስለምን ርእሰ ጉዳይ እንደሚጸልይ ማወቅ ይጠበቅበታል:: ምን ነው ቢሉከላይ ከፍ ስንል ከአሳፍ ህይወት ለመማር እንደቻልነው እንደ የአሳፍ ዓይነቱ ችግር በጸሎት ሳይሆን ራስን በመመርመር በማስተዋል የሚፈታ ችግር አለና። በአሁን ሰዓት ከሃይማኖት መሪዎች የተነሳ በቤተክርስቲያናችን የተፈጠረው ሰጣ ገባም በተመሳሳይ በጸሎት የሚፈታ ጉዳይ ሳይሆን ራስህን ለጽድቅ ስራ በማስገዛት በማስተዋል የሚፈታ ችግር ነው:: የሃይማኖት መሪዎች የጸሎት መለከት የሚነፉበት ምንም ዓይነት ምክንያት የላቸውም::
እርስ በርስ ይቅር መባባል ካቃታቸው፣ እርስ በርስ መዋደድ ካልሆነላቸው፣ ልዩነቶቻቸውን በማጥበብና እርቅም በማውረድ አንድ መሆን ከተሳናቸው እንጸልይ/ጸልዩ ማለት ምን ማለት ነውሰላምእርቅፍቅርናአንድነት ካልተፈለገ ጸሎት ለምን  አስፈለገምን ለመሆን?ጸሎት ማለት ጥያቄ ማለት አይደለም ወይጸሎት ማለት እኮ ጥያቄ ነው::
  • አቅቶናል እርዳን:
  • ደክመናልና ብርታቱ ስጠን
  • ተንገዳግደንና ደግፈን:
  • ስተናልና መልሰን:
  • ተለያይተናልና አንድ አድርገን ማለት ነውኮ ነው:: ታድያኮ ለዓመታት የዘለቀው መደረቋቀስ ከድካም የተነሳ ሳይሆን ከጥጋብ የመነጨ ነው።
ጸሎት መልካም ነው። ጸሎት እንደሚቀበሉ አምነው ለሚጸልዩ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ያሰጣል ያስገኛልም። ጥያቄው ምን ተብሎ ነው የሚጸለየውየሚል ነው። አምላክ ሆይ ስማንተብሎ ፈጥሪ ለመማጸን እኮ ችግሩ ማወቅ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር አባት እንዲሰጠን እንጸልይ ከማለት ይልቅም እግዚአብሔር አባት መሆኑ ከታመነበት ጸላዩ እንደ ልጅ በእግዚአብሔር ፊት እንደ እግዚአብሔር ንብረት በእግዚአብሔር ፋቃድና ትእዛዝ መመላለስ ነው የሚቀድመው:: ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው!” በማለት ሲዘምርኮ አፉ ስላመጣለት አይደለም:: እረኛ በጉን ያሰማራል እንጂ በግ እረኛውን እንደማያሰማራ ሁሉ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ለማለት እግዚአብሔር በሚያሰማራህ ስፍራ ላይ ስትሰማራ ነው:: ሰው በሰይጣን (ጸብንትርክክፋትአመጸኝነትአድመኝነትእልከኝነትነውር ሁሉ በሞላበትመንግስት ተሰማርቶ ሲያበቃ ኡ ኡ ቢል ማን ይሰማዋል?    
ሌላው የጸሎት አዋጁ ገጽታ እስቀድማችሁ ምን ማድረግና ማንን መሾም እንዳለባችሁ ጨርሳችሁ ስታበቁ ያደረግነው ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ለማለት ከሆነ ጸሎቱ፤ ሰውን ብቻ ማታለል አይበቃም ወይእግዚሃሩ ላይ ምን አንጣራራችሁእንግዲህ ጠቢቡ “ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች” (መጽምሳሌ 11:3) እንዲል አያያዛችሁ በገዛ እጃችሁ መጥፊያችሁ ማበጃጀታችሁ ነው የሚመስለው። 
ኤልዛቤል ናቡቴን ለመግደል ባሰበችበት ጊዜ እርምጃዋ ሁሉ ተገቢና ሕጋዊ እንደሆነ ለማስመሰል አስቀድማ ያሰበችውና ያደረገችው ነገር ቢኖር በአይሁድ ባህልና ወግ መሰረት የጾም ጸሎት ጊዜ (ሱባዔነበር ያወጀችው።
በአክዓብም ስም ደብዳቤ ጻፈች፥ በማኅተሙም አተመችው በከተማው ወደ ነበሩትና ከናቡቴም ጋር ወደ ተቀመጡት ሽማግሌዎችና ከበርቴዎች ደብዳቤውን ላከች። በደብዳቤውም ስለ ጾም አዋጅ ንገሩ፥ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀምጡት ሁለትም ምናምንቴ ሰዎች በፊቱ አስቀምጡና። እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ ውገሩት ብላ ጻፈች። በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች ከበርቴዎችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈ እንዲሁ አደረጉ። የጾም አዋጅ ነገሩ፥ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀመጡት። ሁለቱም ምናምንቴ ሰዎች ገብተው በፊቱ ተቀመጡ ምናምንቴዎቹ ሰዎችም በሕዝቡ ፊት። ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው በናቡቴ ላይ መሰከሩ። የዚያን ጊዜም ከከተማ አውጥተው እስኪሞት ድረስ ወገሩት።”
በተነገረው አዋጅና በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ጸሎቱ ተጸለየሕዝብ በእንባ ተላቀሰ ተራጨ የናቡቴም ደም ፈሰሰ። የዚህ ንጹህ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ መሞትም በጾም ጸሎት የታጀበ ስለ ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ ተብሎ ሕዝብ መለከት እየነፋ ነጋሪትም እየጎሰመ ደስታውን ገለጠ። ጥያቄው የናቡቴን በግፍ መገደል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበረ ወይ ነውየጸሎት አዋጁስ  ቢሆን ናቡቴን ለማትረፍ ነበር ወይስ የዋሁን ሕዝብ ለማደናገር የተሸረበ ተንኮልመልሱ ቀጥሎ የሰፈረውን ቃል/አንቀጽ በማንበብ ያገኙታል።
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ። ተነሥተህ በሰማርያ የሚኖረውን የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ትገናኝ ዘንድ ውረድ እነሆ፥ ይወርሰው ዘንድ በወረደበት በናቡቴ የወይን ቦታ ውስጥ አለ። አንተም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ገድለህ ወረስኸውንብለህ ንገረው። ደግሞም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ የአንተን ደም ደግሞ ውሾች ይልሱታል ብለህ ንገረው።” ይላል
አሁንም ቢሆን የሚጸለየው ጸሎት ያለውን ለመድፋት፣ እውነቱን ለመቅበር፣ ብዙሐኑም ለማታለል ካልሆነ በስተቀር የትኛው ችግራችሁ ነው ለጸሎት የሚያበቃ/በጸሎት የሚፈታ ሆኖ የጸሎት ሱባኤ የሚታወጀውወይስ “ሊበልዋት የፈለጉ አሞራ ዝግራ ጅግራ ይሏታል” መሆኑ ነው::እውነት ነውነገራችሁ ከሰው ዘንድ ለመሰወር ተችሎአችኋል ቢሆንም እናንተ ራሳችሁም ሆነ እግዚአብሔር የሚያውቀው ችግር እንዳላችሁ ግን ሁለታችሁ በየፊናችሁ አሳምራችሁ ታውቃላችሁ። ታድያ ለእንዲህ አይነቱ አዙሪት ምን ጸሎት ያስፈልገዋልበማሰብና በማስተዋል የሚፈታ ችግር እንጅ በጸሎት የሚፈታ ችግር የላችሁ። በአጭር አገላለጽ ዘሩ ያለው በእጃችሁ ላይ ነው። እንክርዳድ ዘርቶ ስንዴ ያጨደ ማን ነውይቅርታ፣ ምህረት፣ ፍቅርን … ዝሩ ሰላም፣ አንድነትና ህብረትን ታጭዳልችሁ። በእንቢተኝነት ጸንታችሁ እልከኝነትም ነግሶባችሁ አሻፈረኝ ከሆነ ቋንቋ ግን አፋቹ በሰማይ አንደበታችሁም በምድር ውስጥ ባታመላልሱና ባታኖሩ ነው የሚመከረው። ይቅር ተባባሉእርቅ ሰላምም አውርዱይህን ለማድረግ ደግሞ ይቅርብኝ ማለት ብቻ እንጅ ምንም ዓይነት ጸሎት አያስፈልገውምይህን ስታደርጉ ደግሞ አይደለም አባት ሌላውንም ግዛት አሳልፎ ለክብሩ ይሰጣችኋል:: በተረፈ ግን ከነፈሰ ጋር የሚነፍሰውን እውነት እንደ ሰማይ ከዋክብት ለራቀችበት ሕዝብ ግን ከልብ አዝናለሁ::
አንድ ነገር ጨምሬ ልንገራችሁና ጽሑፌን ላጠቃልል። ማናችሁንም ብትሆኑ የሕዝቡ ባለባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ከሚያስብለት በላይ ለዚህ ሕዝብ/ለዚች ቤተ ክርስቲያን ልታስቡ አትችሉምውሸት ነው!ከመስዋእት ይልቅ መታዘዘን የሚማርከው እግዚአብሔር ደግሞ ከምንም በላይ አስቀድማችሁ እርስ በርሳችሁ ተስማሙተዋደዱተፋቀሩ ብሎ ካዘዘ እርቅ በሰማችሁ ቁጥር አንገቴ ለካራ የምትሉበት ምክንያት ምንድነውምናችሁ ቢነካ ነውይቅር ለማለት ምህረትንም ለመስጠት ያልተሰላቸ/መቼም የማይሰላች እግዚአብሔር በትልቁ እያለ የእናንተ መጨናበርና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ምን ያባላልማን ቤት ሆናችሁ ነውና እንዲህ ደጅ የሚጸናባችሁእግዚአብሔር ወርዶ እናንተን ይለምን?የቀራችሁ ይሄ ነው። እንግዲህ የለምቅድሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩት እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ጸሎት አይሰማም። ዜማ እስኪታደስ ጀሮ ዳባ ልበስበተጨማሪም እግዚአብሔር ሲያከብራችሁ ካልከበራችሁ ዓለም ቅዳሴ ታዜሙላት ዘንድ እንደማትፈልጋችሁ ልታውቁ ይገባል:: በዚያን ጊዜም የሰው ክንድ ደግፎ አያቆማችሁምአንገታችሁ ያንጠለጠላችሁትን በደግ ዘመን የሸመታችሁት ወርቅ ሸጣችሁ ትበሉ እንደሆነ እንጅ::
ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት!
  • ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”(የማቴዎስ ወንጌል 6:14, 15)
  • ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።(የማርቆስ ወንጌል 11:25)
ሰላም ከተፈለገ የጸሎት ሱባኤ አያስፈልግም!2
/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America
Sep. 07, 2012
1  “አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ” የሚለውን ቃል የእይታው ቅኝት የሚያመላክት ነው:: ኦይኖቼ በሰዎች ህይወት ላይ ተክዬ እንዲህ ያለ ሃጢአትና ነውር እያየሁ ለምን ራሴን እረብሻለሁ በማለት ራሱን ከማረጋጋት ይልቅ ከሚያልፍበት ህይወት በተጨማሪ ተደራቢ መከራ ያመጠበት የሃጢአተኞች ህይወት እያያ ይህንንም በማሰላሰል በራሱ መንገድ ለማጥናት በመወሰኑ ነበር::
2  ይቅር ተባባሉእርቅ ሰላምም አውርዱይህን ለማድረግ ደግሞ ይቅርብኝ ማለት ብቻ እንጅ ምንም ዓይነት ጸሎት አያስፈልገውምይህን ስታደርጉደግሞ አይደለም አባት ሌላውንም ግዛት አሳልፎ ለክብሩ ይሰጣችኋል:: በተረፈ ግን ከነፈሰ ጋር የሚነፍሰውን እውነት እንደ ሰማይ ከዋክብት ለራቀችበትሕዝብ ግን ከልብ አዝናለሁ::

No comments:

Post a Comment