Translate

Saturday, October 6, 2012

ከመስከረም 20 ጀምሮ ለአራት ቀናት በዝግ የተካሄደው የኦህዴድ ስብሰባ ከፍተኛ ፍጭት የተካሄደበትና በርካታ ነባር አባላት ከድርጅቱ ሊባረሩ የሚችሉበት ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ገለጹ


ዘረኛው መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ወዲህ በህወሃትና ህወሃት በአምሳሉ በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ጥርጣሬና አለመተማመን መስፈኑን በዚህም ምክንያት በተለይ ህወሃትና ኦህዴድ በስብሰባ መወጠራቸውን ከታማኝ ምንጮች የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ።
ከመስከረም 20 ጀምሮ በዝግ ስብሰባ የተካሄደውን የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር ስብሰባ የመራው ኩማ ደመቅሳ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች ግለሰቡ በአብዛኛው የድርጅቱ አባል ዘንድ የማይወደድ እንደሆነና ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የግምገማ  ተቀናቃኞቹን ለማስመታት ትልቅ ተጋድሎ ሲያደርግ እንደሰነበተ ይናገራሉ።
አብዛኛው የኦህዴድ አመራር በበረከት ስሞን አንጋሽነት ለጠቅላይ ምንስትርነትና ምክትል ጠቅላይ ምንስትርነት በተሰየሙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው ይታወቃል። በዚህም ምክንያት የሰሞኑ ስብሰባ በረከት ስሞን ጥርስ የነከሰባቸውንና እንደተለመደው አንገታቸውን ደፍተው ታዛዥ በመሆን ላለመቀጠል እያቅማሙ ያሉትን የኦህዴድ አባላት ነጥሎ ለመምታት የታለመ ነው ተብሎአል።

በህትመት ሥራው ላይ የበረከት ስሞን እጅ እንዳለበት የሚነገርለት ሰንደቅ ጋዜጣ የሰሞኑን የኦህዴድ ስብሰባ ሲዘግብ ስብሰባው የኦህዴድን መስመር በርዘው በሚንቀሳቀሱ አመራሮች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመወሰድ የሰላ የመደብ ትግል የተካሄደበት እንደነበር ገልጾአል።
ሰንደቅ ላይ የወጣውን ዘገባ የተመለከቱና ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት አብዛኞቹ የኦህዴድ አባላት በሙስና የተጨማለቁ ናቸው በሚል ውንጀላና  የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን ደግሞ  በሃይማኖት አክራሪነት ፍረጆ ለመምታት የተቀረውን በኦነግ ሰርጎ ገብነት ለማስወገድ ዝግጅት መጠናቀቁን ይገልጻሉ።
ከመለስ ዜናዊ ሞት ቦኋላ የኦህዴድን አመራር ልብ ያሸፈተው ለጠቅላይ ምንስትርነት በተደረገው ምርጫ ከኦህዴድ ብቁ ሰዎች እዳሉና ቦታው እንደሚገባቸው የህወሀት ተላላኪ ለሆነው ኩማ ደመቅሳና ቡችሎቹ ተነግሮአቸው ወደ ኢህአደግ አመራር ስብሰባ ከሄዱ ቦኋላ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን ትተው መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ያድርጉ እንደነበረው በረከት ስሞን አጭቶ ላቀረባቸው ዕጩዎች  አጨብጭበው መመለሳቸው የፈጠረው ብሶት ነው ተብላኦል።

No comments:

Post a Comment