Translate

Tuesday, July 5, 2016

የአቶ ሀብታሙ አያሌው ባለቤት አራሷን ስታ በመውደቋ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች የአቶ ሀብታሙ አያሌው ባለቤት አራሷን ስታ በመውደቋ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች

Habtamu Ayalew and his wife
ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንዲጓዝና ፍርድቤት የጣለበትን ከሀገር ውጭ የመጓዝ እገዳ ያነሳል ተብሎ የተጠበቀው ችሎት “ዳኛው ቀርተዋል” በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ መተላለፉን ያደመጠችው የአቶ ሀብታሙ ባለቤት እራሷን ስታ ወድቃለች።

አቶ ሀብታሙ አያሌው በሕወሃት የታገደው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ታስሮ በቅርቡ በዋስ የተፈታ ቢሆንም በእስር ላይ በቆየባቸው ጊዚያት ጤናው በመታወኩ በአስጊ ሁኔታ ላይ ሆስፒታል ተኝቶ ይገኛል።
አቶ ሀብታሙ አያሌውን እያከሙት ያሉት ዶክተሮች “ከአቅማችን በላይ ነው ህመምተኛው በውጭ ሀገር ከፍተኛ ህክምና ሊያደርግ ይገባል” በማለት የጻፉትን ደብዳቤ ይዘው ነበር የአቶ ሀብታሙ ባለቤት እና ወዳጅ ዘመዶች ፍርድቤት የተገኙት። ይሁንና ፍርድቤቱ “ጉዳዩን የያዙት ዳኛ አልተገኙም” በሚል ተልካሻ ምክንያት ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።

No comments:

Post a Comment