Translate

Sunday, July 31, 2016

በገደብ አሳሳ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደሙ | ሰልፈኞች የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ደኤታ መኖሪያ ቤትን አቃጠሉ

gedeb asasa2
Gadab asasa
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ እንደቀጠለ ነው:: ሕዝብ በመንግስት እና በመንግስት ደጋፊዎች ንብረት ላይ የበቀል እርምጃውን እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል::
ምዕራብ አርሲ በገደብ አሳሳ ቲጆ ዋቄንተራ ከተማ ዛሬ በተደረገ ተቃውሞ በአጋዚ ጥይት ወገኖቹ የተቆሉበት ሕዝብ ቁጣውን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሰባብሮ በመግባት ሰነዶችን በመበታተንና በማቃጠል የበቀል እርምጃዎችን ወስዷል::
በዛሬው የገደብ አሰሳ ቲጂ ዋቄንተራ ከተማ ቤታቸው ከተቃጠለባቸው የ ስር ዓቱ ባለስልጣናት መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ደኤታው አቶ ዳዋኖ ከድር መኖሪያ ቤት እንደሚገኝበት ታውቋል:: እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ተቃሟቸውን ሊገልጡ የወጡ ሰልፈኞች የምታስፈጀን አንተ ነህ በሚል የአቶ ዳዋኖ ከድርን መኖሪያ ቤት በ እሳት አንድደውታል::
Gadab asasa 2

No comments:

Post a Comment