Translate

Sunday, July 31, 2016

ከአዲስ አበባ ሀረርና ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ ተዘጋ | አጋዚ በአወዳይ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት አቆሰለ

oromia
(ዘ-ሐበሻ) ጎንደር በሰላማዊ ሰልፍ በተቀወጠበት በዛሬው ዕለት ምስራቅ ሐረርጌ አወዳይ ከተማም እንዲሁ ሕዝባዊው ተቃውሞ ገንፍሎ መውጣቱ ተሰማ::
ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ ተቃውሞን ባሰማበት በዛሬው የአወዳይ ከተማ ተቃውሞ በስፍራው የነበረው የአጋዚ ሰራዊት 4 ሰዎችን ክፉኛ ማቁሰሉ ተሰምቷል::
የሕዝባዊ ተቃውሞው እጅግ በመጠንከሩ ሕዝቡ ከአዲስ አበባ ሃረርና ጅጅጋ የሚያገናኘውን መንገድ በድንጋይ; በ እንጨትና በተለያዩ ቁሳቁሶች እንደዘጋጋቸው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ:: በዛሬው ተቃውሞ በአጋዚ ጥይት ከቆሰሉት መካከል አህመድ የሱፍ; ሙአዝ አብዱልሃሚድ ኡመር; ባርክሌና በየነ ደሜሾ የሚባሉ ወጣቶች እንዳሉበት ታውቋል::

No comments:

Post a Comment