Translate

Friday, July 15, 2016

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ – ከቅስቀሳና አደራጅ አካላት የተሰራጨ አስቸኳይ ባለ 8 ነጥብ መልእክት

Gonder
ሃምሌ 8 2008
1. ወያኔ የሚንበረከከው በሃይል ብቻ ስለሆነ የተጀመረው አኩሪ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል። ያ ካልሆነ የታሰሩ ወገኖችን ማስፈታት አይቻልም።


2. ህዝባዊ ተቃውሞው ካልቀጠለ የአማራ ክልል አስተዳደር በወያኔ ጫና ተንበርክኮ ሰዎቻችንን አሳልፎ እንዳይሰጥ የተጀመረው ትግል ጋብ ሳይል ተጠናክሮ ይቀጥል። እስካሁን ባለው መረጃ በወያኔና በአማራ መስተዳድር መካከል መሻከሩ ተካሮ ለአንባጓሮ እየደረሰ ነው። ለዚህም ማሳያው የክልሉ ሚሊሻያ እና የፀጥታ ሃይል በህዝቡ ላይ አንተኩስም ማለታቸው በብዛት ይታወቃል።

3. የአማራ ወጣትና የገበሬ ሚሊሽያ ጥይት ቆጥባችሁ ለማይቀረው ትንቅንቅ ብሎም ድል ቀበቶ አጥብቁ።

4. በወረዳዎች የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥል። ጠላትን በጣም አሸብሮታል። ከአጎራባች ክፍለ ሃገራትም ሆነ ከሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተቀናጀ ትግል ይደረግ።

5. ለጀግናው ኮሎኔል ደመቀ በህዝብ ጥበቃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል። አመራሩንም ህዝብ ይከተል። የወልቃይት ኮሚቴ መሰረቱ ሰፍቶ በሰው ሃይል ይጠናከር። በተዋረድም ተጠባባቂ አመራር በህቡእ ይደራጅ።

6. ወያኔ ከላይ በኤርትራ ካሉ የነፃነት ታጋዮች ከታች በጎንደር በተቃጣበት ጥቃት እጅግ አጣብቂኝ ውስጥ ስለገባ በከባድ ጭንቀት ላይ ነው። መውደቂያውም አሁን ግልፅ እየሆነ ነው።

7. የጎንደር ሕዝብ በአንድ ልብ በአጭር ጊዜ ቆርጦ ስለተነሳ የስርአቱ ማብቂያ ሰአቱ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወያኔ መውደቂያውን አይቷል። እግዚአብሔር የቆረጣት ቀን እንደደረሰ ምንም አትጠራጠሩ! ይሰመርበት!

8. በአለም አቀፍ ደረጃ በጎንደር ሕብረት አማካኝነት የሚደረጉት የድጋፍ ስራዎች በጣም በተጠናከረና በተቀናጀ መልኩ እየተካሄዱ ናቸው። በገንዝብ በዲፕሎማሲ በእውቀት በመረጃ ልውውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይደረጋል። ድሉ ተጀምሯል! ይፈፀማልም!

ድል ለጀግናው የጎንደር ኢትዮጵያዊ ሕዝብ!
ይህን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተውጣትቶ የተሰራጨ መልእክት ለሁሉም በአስቸኳይ እንዲደርስ አድርጉ።

No comments:

Post a Comment