Translate

Friday, July 22, 2016

ሰበር መረጃ – በሕወሃት የመከላከያ ሰራዊት ዉስጥ የነበረዉ ጉምጉምታ ወደ ተግባራዊ ተቃውሞና ፍጥጫ ተሸጋገረ

በልኡል አለም
የወታደራዊ ፖለቲካ መምሪያ እና የፕሮፓጋንዳ ክፍሎች ምንጭ እንደሚያመለክተዉ በሰሞኑ ጎንደር ላይ የተገደሉትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ትዉልድ ቦታቸዉ ተወስደዉ በክብር መቀበራቸዉ ተንተርሶ በሰራዊቱ ዉስጥ ቅራኔ ተፈጥሯል!TPLF security members killed in Gondar
ይህዉም፣

1. ከሟቾች ዉስጥ ትግሬ የሆኑ አባላት ስላሉበት ነዉ የቀብሩ ስነ ስረአት በክብር የተከናወነዉ።
2. ዉስጥ ዉስጡን የሚሰራ የብሔር ማናከሱ ደባ በአማራ የተገደሉ ትግሬዎች ናቸዉና ትግሬ የሆንክ ሁሉ ለዘላቂ የመኖርህ ሕልዉናህ ስትል ከህወሃት ጋር እስከ ሞት ድረስ ቁም የሚል የጽንፍ መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነዉ።
የሚሉ ሲሆን ሰራዊቱ በሶማሌያ፣ በኤርትራ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በጋንቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በተለያዩ የቦርደር አካባቢዎች ሲገደል ወይም ሲሰዋ የመከላከያ አባላቶቱ ከነመፈጠራቸዉም ስማቸዉ ተነስቶ አይታወቅም።
ይህ ለምንና እንዴት እንደሆነ ባለስልጣናት የሆኑ የሕወሃት አመራሮች ሲጠየቁ “ሕወሃት ከጅምሩ ወታደሮችን በሞቱበት ስፍራ የመቅበር ባሕል አላት” ብለዉ ይቀልዳሉ በማለት ማጉረምረሙ ወደ ቅራኔ እየተቀየረ መምጣቱን ምንጮች ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት በጎንደር የተከሰተዉን የህዝብ የመከላከል እርምጃ ተንተርሶ ሕወሃት ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀ ሲሆን በተጨማሪ በዚህ ሁለት ቀናት ዉስጥ በጎረቤት ሀገር ቦርደር አካባቢ የህወሃት 24ተኛ ክ/ጦር ድንገተኛ ጥቃት ደርሶበታል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment