Translate

Tuesday, July 12, 2016

ሰበር መረጃ — የትምህርት ሚኒስተር፣ የፈተናዎች ኤጀንሲ ኮምፒውተሮች ሃክ ተደረጉ

በልኡል አለም
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አፈትልኮ መዉጣትን ተንተርሶ ብዙዎች የራሳቸዉን አስተያየት ሰጥተዋል ነገር ግን ፈተናዉ ትክክለኛ መሰረቁን የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር። ኢሳት ጉዳዩን ለማጣራት ብዙ ጥረት አድርጎአል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ መግለጫ የሰጡጠም ግለሰቦች አለጠፉም።የትምህርት ሚኒስተር፣ የፈተናዎች ኤጀንሲ ኮምፒውተሮች ሃክ ተደረጉ
እዉነቱ ከሕወሃት መንደር ሲነገር መስማቱ ብዙም ባያስደነቅ የሐገራችንን ብሐራዊ ደህንነት አደጋ ላይ የጣለዉ እራሱ የብሐራዊ ደህንነት ፈተናዉ የተሰረቀበትን መንገድ አገኘሁ እያለ ባለበት ሁኔታ የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች እና መምህራን ያፈተለከዉ ፈተና ትክክለኛ መሆኑን እያረጋገጡ ይገኛሉ።

የብሔራዊ መረጃ ቻይናዎች ባጣሩት መሰረት በመጀመሪያ ግዜ የተሰራጨዉ ፈተናና ዉጤት የተበተነዉ የትምህርት ሚኒስተሩ የነሽፈራዉ ሽጉጤ የፈተናዎች ኤጀንሲ ኮምፒዉተሮች ሃክ በመደረጋቸዉ ነዉ የሚል ፍንጭ ይዞ የተከሰተ ሲሆን በተመሳሳዩ ለሁለተኛ ግዜም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተደረገባቸዉ ኮምፒዉተሮች መጠለፋቸዉ ተረጋግጧል።
ወያኔ ከሚጠቀምባቸዉ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌዚዥን፣ የናዝሬት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሄራዊ መረጃ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ የተልኮሚኒኬሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮምፒዉተሮች ባልታወቁ ሃከሮች ቁጥጥር ስር ወድቀዉ ነበር አሁንም እየወደቁ ይገኛሉ ይላል የሄራዊ መረጃዉ፤
በመሆኑም መረጃዉ እንደሚያትተዉ ከተጠላለፉ የሶፍትዌር ወረራዎች የሐገሪቱን ሚስጥር መጠበቅ ካለመቻሉ በተጨማሪ የባለቁልፍ ኮምፒዉተሮችን የኮድ ሚስጥር ከወያኔ ጓዳ የሚያቀብሉም ግለሰቦች መኖራቸዉን ነገር ግን እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ኣጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መወደቁን የዉስጥ ምንጮች አክለዉ ገልጸዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

No comments:

Post a Comment