Translate

Saturday, October 6, 2012

የዘረኛው መለስ ዜናዊ ራዕይ ሳይሸራረፍ እተገብራለሁ በማለት ቃል የገባው ሀይለማሪያም ደሳለኝ አወዛጋቢውን መሬት ለባዕዳን የመሸጥ ፖሊሲ እንደሚገፋበት አስታወቀ


ላለፉት አምስት አመታት የኢትዮጵያን ደሃ ገበሬ በጠመንጃ ኃይል እያፈናቀለ መሬቱን በርካሽ ለባዕዳን ሲቸበችብ የከረመዉ የወያኔ አገዛዝ አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የተቀሰቀሰበትን ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣና ተቃዉሞ ጆሮ ዳባ ልብስ በማለት አሁንም ደሃዉን ገበሬ እያባረረ መሬት መሸጡን የሚቀጥል መሆኑን አስታወቀ።
ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የራሱ የሆነ ራዕይ እንደሌለዉና ጥረቱ ሁሉ የጌታዉን የመለስ ዜናዊን ራዕይ ክግቡ ለማድረስ መሆኑን ደጋግሞ የተናገረ ቢሆንም መሬት ሽያጭን የመሰለ አጅግ አወዛጋቢ እርምጃ አንዲህ በአጭር ግዜ ይወስዳል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ አልነበረም። ሆኖም የኃ/ማሪያም ደሳለኝ አገዛዝ መሬት የመሸጡን ፖሊሲ አሁንም እንገፋበታልን በማለት አገዛዙ የሚጨነቀዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን አሁንም የህወሀት ባለስልጣኖችንና የደጋፊዎቻቸዉን ኪስ ለመሙላት መሆኑን በተግባር እያሳየ ነዉ ሲሉ ብዙዎች ትችት በመሰንዘር ላይ ናቸዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን የመሬት ንጥቂያ በቅርብ የሚከታተሉ ምሁራንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ባለፉት አመታት የተካሄደዉን የመሬት ሽያጭ አጥብቀዉ ሲቃወሙ የቆዩ ቢሆንም የወያኔ አገዛዝ ግን በያዝነዉ አመት አንድ መቶ ሺ ሄክታር መሬት ለባዕዳን ለመሸጥ ማቀዱን አስታዉቋል። የመሬት ሽያጩ የሚካሄደዉ በኦሮሚያ፤ በአማራ፤ በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ሲሆን ከዚህ ቀደም በእነዚህ ክልሎች የተካሄደዉ የመሬት ሽያጭ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱና በተለይ ጋምቤላ ዉስጥ ህዝቡ ጫካ ገብቶ የትጥቅ ትግል እንዲጀምር ማድረጉ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ “የብሔር ብሄረሰቦች” እኩልነት ተከብሯል የሚለዉንና መለስ ዜናዊ ያስተማረዉን መዝሙር እንደ ዳዊት ከመድገም ዉጭ “መብት” ማለት ምን እንደሆነ የማያዉቀዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የኢትዮጵያን ደሃ ገበሬ ከመሬቱ እያፈናቀለ መሬቱን ለመሸጥ መወሰኑ የሚያሳየን ነገር ቢሆን እሱም እንደ ጌታዉ እንደ መለስ ዜናዊ ለዜጎች የአገር ባለቤትነት መብት ምንም ደንታ የሌለው መሆኑን ገና ሥልጣን ላይ ሳይደላደል መግለጹ ለውጥ ሊኖር ይችላል ብለው የሚያስቡትን  ወገኖች ቅስም የሰበረ መሆኑ ይገመታል።
ሃይለማሪያም ደሳለኝ “ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለአምላካችን ይሁን” የሚለውን አምልኮአዊ አነጋገር ገልብጦ “ ክብርና ሞገስ ለዘላለሙ ለታላቁ መሪያችን ይሁን ሲል መደመጡ መለስ ዜናዊ አሳርፎበት ከሄደው የበታቸኝነት ስሜት ገና ባለማገገም አምልኮ መለስ ጀምሮአል የሚል ትችት አስከትሎበታል።

No comments:

Post a Comment