የኢትዮጵያ የስልምና ጉዳዮች ተብሎ እየተጠራ ያለው እና በአሁን ሰአት በመንግስት ተተክቶ የሚሰራው የኡለማዎች ዋና የተሰኘው ጽ/ቤት በፈትዋና እና ዳእዋ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በየአምስት አመቱ የሚያደርገውን ምርጫ አስመልክቶ በአሁን ሰአት አዲስ አመራሮችን መምረጥ እንደምኢፈልግ ይጠቁማል ። ይህ ከፍተኛ ነቀፌታ የገጠመው መጅሊስ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በመለየት የመንግስትን የአመራር እርምጃ ተከትሎ የሚሰራ እና መንግስትን እንደ ጣኦት የሚያመልክ የውጭ የተልእኮ ድርጅት ነው ሲሉ ሙስሊማን ህብረተሰቦች ይኮንኑታል።
በሃገሪቱ በስፋት ተቃውሞ የገጠመው ይሄው የመጅሊስ አሠራር ዛሬም ተቃውሞአቸው ቢቀጥልም ህብረተሰቡን ከማወክ እና አሰራራቸውን ቀርፈው ከመንግስት እጅ ለመውጣት እንዳይችሉ የተሳሰረ ቁልፍ ውስጥ መግባታቸውን የሚጠቁም ሪፖርት ደርሶናል።ለዚህም መንግስት አውቆ የከፋፈለው የእስልምና እምነት ተከታዮቹን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል እንደሆነ የሚገልጹት ብዙሃኑ ሙስሊሞች ይህንን መስተካከል የማይችል ከሆነ ግን ከሰላማዊ ጥያቄ ወደ መብት ማስከበር ሊጓዙ የሚችሉበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሆኑ ተገልጾአል። የታሰሩት አባሎቻቸውን ለማስፈታት ያቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ያላገኙት እነዚሁ ወገኖች በአሁን ሰአት ካለው የመጅሊሱ ጋር ያላቸውን ሰፊ ልዩነት ማስወገድ የሚችሉት ህዝበ ሙስሊሙ የፈለገውን በራሱ ስልጣን መምረጥ እና የራሱን ሰው ሲያስቀምጥ ብቻ እንደሆነ የሚጠቁመውን አንደኛውን አንቀጻቸውን መንግስት አልቀበልም በማለት አባሎቻቸውን በማሰቃየት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በዚህ አቋማቸው የሃይማኖት መብታቸውን ማራመድ እንዳይችሉ የተነፈጉት አጠቃላይ ሙስሊሞች በየሃገሩ የድምጽ ማሰማት ዘመቻቸውንም አሁንም ቀጥለው መዋላቸውን የደረሰን ዜና ዘገባ ያመለክታል ::
No comments:
Post a Comment