Translate

Wednesday, October 3, 2012

ኃይለማርያም ደሳለኝ አዲሱን ካቢኔያቸውን የፊታችን ሰኞ ያሳውቃሉ፤ ሹም ሽር ይጠበቃል




Ambassador_berhane_gebrekristos የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የፊታችን ሰኞ (መስከረም 28 ቀን 2005 ዓ.ም) በፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ንግግር በይፋ ይከፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ም/ቤቶቹ ሰኞ ዕለት በይፋ ከተከፈቱ በኋላ ማክሰኞ ዕለት መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ማክሰኞ ዕለት መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ.ም በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ
ኃይለማርያም ደሳለኝ አዲሱ ካቤኔያቸውን ም/ቤቱ እንዲያፀድቅላቸው ይዘው ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምንጮቻችን እንደገለፁት ወደ 22 የሚጠጉ ሚኒስቴር መ/ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮች መካከል በአቶ ኃይለማርያም ሹመት የሚቀጥሉም፣ የሚሰናበቱም ይኖራሉ። ይህም ሂደት ይከናወናል ተብሎ የሚጠበቀው የኢህአዴግ አራት አባል ፓርቲዎች ተመጣጣኝ የኢህአዴግ አራት አባል ፓርቲዎች ተመጣጣኝ ዕድል ለመስጠት እንዲሁም አጋር ፓርቲዎችን በካቢኔ ቦታ ውስጥ ለማሳተፍ ሲባል ነው።


ሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም ባዋቀሩትና በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ባለው ካቢኔ ውስጥ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) – ስድስት፣ ብአዴን – አምስት፣ኦህዴድ – አምስት፣ ህወሓት – ሁለት፣ ሶህዴፓ – ሁለት፣ ከአፋር – አንድ፣ ከየትኛው ፓርቲ አባል ያልሆኑ አንድ ሚኒስትር በማካተት ለፓርላማው አቅርበው ማስፀደቃቸው ይታወሳል።

ቀደም ሲል አቶ ኃይለማርያም ደርበው ይዘውት የነበረውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ በአሁኑ ወቅት በመ/ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ይይዙታል የሚል መረጃ እንዳለው
ምንጫችን ጠቁሟል። ሆኖም ይህን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment