Translate

Sunday, October 7, 2012

ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ የኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶች ታስረዋል ተባለ


ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን ዓመታዊው የኢሬቻ በዓል በደብረ ዘይት በሚከበርበት ጊዜ በደህንነት ሀይሎች የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ደህንነት ጉዳይ እጅግ እንዳሣሰበው  የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል።
የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከወኪሎቹ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ባለፈው መስከረም 29 የኢሬቻ በዓል ማጠናቀቂያ ላይ በደህንነቶች ተወስደው  የታሰሩት ከ200 በላይ ሲሆኑ፤ሁሉም ወጣቶች ናቸው።
ወጣቶቹ በማግስቱ ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን የጠቀሰው የሰብዓዊ መብት ሊጉ፤የታሰሩትም በበዓሉ ላይ ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸው መፈክሮችን አሰምታችሁዋል ተብለው  እንደሆነ አመልክቷል።

እንዲሁም መስከረም 19 ቀን  ከምዕራብና ከደቡብ ሸዋ   በአውቶቡሶች ሞልተው ወደ በዓሉ ስፍራ ሲመጡ የነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች በደህንነት ሀይሎች ታግተው ወደ ጉደር፣አምቦ፣ጊንጪ፣ሻሸመኔ ሰበታ፣ዱከም እና ሌሎች ከተሞች ውስጥ ወደሚገኙ ያልታወቁ ሥፍራዎች መወሰዳቸውን ሊጉ ገልጿል።
የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች ባለፉት 20 ዓመታትና አሁንም የከፍተኛ አመራር ለውጥ በተደረገበት ጊዜ ፤ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ለማየት አለመታደላቸውን ሊጉ ጠቁሟል።
በመቶዎች ከሚቆጠሩት እስረኞች መካከል ብዙዎቹ የትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አለመታወቁን የጠቀሰው የሰብዓዊ መብት ሊጉ፤ በወኪሎቹ አማካይነት ባደረገው ጥረት ያሰባሰበውን የ 50 እስረኞችን ስም ዝርዝርና ፎቶ በመግለጫው ይፋ አድርጓል።
በሉጉ መግለጫ የተዘረዘሩት 50 ወጣቶች ስም፣ዕድሜ፣የትምህርት ደረጃና የትውልድ ቦታ የሚከተለውን ይመስላል፦


ተራ ቁጥርስምዕድሜየት/ት ደረጃ ወይም ሥራ
የትውልድ ቦታ
1አለሚቱ ለሚ ጀቤሳ1910ቢሾፍቱ
2ጃፋሮ ሻላማ ፊዳ25Studentፊንፊኔ/ልደታ
3ማሞ ለሚ ተረፈ2010+3ግንደ በረት
4ተስፋዬ ዱጉማ ዲዳ2210+3አምቦ
5ያደሳ ነገሮ ዋጋሪ27-ያልታወቀባኮ-ቲቤ
6ቦጃ ሽብሩ ደሬሳ2510+3ባኮ-ቲቤ
7አያንቱ መሀመድ ሙሜ2210+3ሀሮማያ
8ቂጤሳ አለማየሁ አያና198ነቀምት
9አብዲ አብራሂም ሰይድ25BAሀሮማያ
10ዳዲ ጉዳ ባልቻ25ያልታወቀዱከም
11ኤልያስ ባጫ አመኑ2410ሻሸመኔ
12ጋዲሳ ቃባ ዋጋሪ26BAጌዶ
13ሞቱማ ለሚ ጀቤሳ2210+3ቢሾፍቲ
14አሸናፊ አንገሳ ኩታ22ገበሬጦሌ
15ድሪባ ቱምሳ ጭብሳ2210+2አምቦ
16ሽመልስ አቦዩ2510+3ሆሮ ጉድሩ
17ሳኒ ጃቤሳ ዱቤ2212ጦሌ
18ሌሊሳ ላጨ ቴሬሳ25ያልታወቀአልፋታ
19ሳሙኤል ፈቃዱ ቀልቤሳ22የመንግስት ሠራተኛነቀምት
20አብዲ ቀጀላ ሰቦቃ21የመንግስት ወራተኛጃርሶ
21በዳሳ ታደሰ አባወሪ27BAጅማ
22ገመቹ ሀብታሙ ታፈሰ2012ጃርሶ
22ፊሮምሳ ራቢራ ጂራታ24BAጃርቴ ጃርደጋ
23ገመቺ ግርማ ጋራሳ2210ጦቄ ኩታዬ
24ዳሜ ቱፋ ሮባ198ሎሚ-ኢንጉሚ
25ቡልቲ ጌታሁን ባርቄሳ1810አለልቱ
26ቶማስ አማንቴ ጃሮ25BAኩዩ
27በዳሳ ተሾመ ኦልጅራ35ሠራተኛነጆ
28ኦሉማ ሱፊ ቀጀላ23ያልታወቀዝዋይ
29ሽመልስ አበበ ጠሶ2612ኩዩ
30ፈያራ አበበ ያደሳ2312አምቦ
31ግርማ ጭምዴሳ ኦሉማ2510+3ሻምቡ
32ዘላለም ባይሳ ልሬቲ2410ጎቼ-አዋሽ
33ጫላ ቶሎሳ በዳዳ2312ኢንጭኒ
34ገረመው ዳባ ባይሳ25BAየቄ
35በዳሳ ገመዳ ጩቃላ27-ያልታወቀሊምባን
36ገመቺስ ለሜሳ26-ያልታወቀያልታወቀ
37ቡልኪ ጌታሁን27-ያልታወቀነጆ
38ዳና ቱፋ ሮባ25-ያልታወቀሉሜ
39ደቻሳ ከበደ28-‘አቢቹ
40ዲቦ ሹሚ30-ቢሾፍቱ
41ባዶ መልካ--አቡ ሴራ
42ንጋቱ ለገሰ--ሰበታ
43አየለ ባዪ--ሜታ
44ጃፉራ ሸለማ--ኢንጪኒ
45ሰንበቱ ረጋሳ--ገርባ ጉራቻ
46ኢብራሂም ቃሌ--አሰላ
47ተክሉ ፉርሞሳ--ነቀምት
48አባይ ጎሳ ባልቻ--ቢሾፍቱ
49ኦላና ጫላ ሂርጳ--አምቦ
50ሌሊሳ ሉቼ ተሊላ--አልፋታ

No comments:

Post a Comment