Translate

Tuesday, September 4, 2012

የኪነጥበብ ሰዎች ቤተ-ጥበብን አፍርሰው መንገድ ተዳዳሪመሆን አይኖርባቸውም!


ዘነበ በቀለ
Ethiopian man (cadre) singing for dictator Meles Zenawiኪነጥበብ በብዙ መልኩ በእውነት ላይ መሰረት ያደረገ እንጂ! ህዝብን የአንድ አቅጣጫ ተከታይ ለማድረግ የሚሞክር አይደለም። ምንም ጊዜ ቢሆን እውነትን በእውነትነቱ ከማቅረብ
ፎቶ (ሀና መታሰቢያ፣ ከፌስ ቡክ፣ የተወሰደ)
ባሻገር አስመሳይነት በኪነጥበብ ውስጥ ስፍራ የለውም። ማህበረሰባዊ አስተሳሰብን ለማንፀባረቅ በባህል እንደታየው የመንግስት ሰላዮች ማምሻቸውን በየመጠጥ ቤቱ የሚያደርጉት የአዝማሪን ትችትና ወቀሳ ለማወቅና ህዝብና መንግስት የሚቀራረቡበትን ዘዴ ለመቀየስ ነው። አዝማሪ የህዝቡን ስሜት በማንፀባረቅ በኩል ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑ ግልፅ ነው። ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት የቆየ ታሪክ አላት ሲባል በርካታ ሁኔታዎችን ለመግለፅ የሚያስችል ህዝቡ የሚጠቀምባቸው ከህፃን መዝሙር አንስቶ እስከ ሰርግ ዘፈን ድረስ አልፎም ለሀዘን የሚደረግ፣ ሙሾም ሆነ ለቅሶ ያላት መሆኑን ለመጠቆም ነው።  ያንድ ህዝብ የበለፀገ ባህል መገለጫውም ይህን የመሰለ ትውፊት መኖር ነው።

ግለሰቦች በሞቱ ቁጥር አዳዲስ ዜማ አይደረስላቸውም። ይህም ንጉስ ሆነ ፕሬዚዳንት አሰሪ ሆነ ሰራተኛ በባህል ውስጥ እኩል ናቸው። በተለያዩ ቋንቋዎች የሚቀርበው የሙሾም ሆነ የለቅሶ ሙዚቃ በመድልዎ ላይ የተመሰረተ አይደለም። የጉራጊኛ ተናጋሪው “አለም ገፈረነ በዋሻ…” የሚለው ሙሾ፣ ከአማርኛ ተናጋሪው “ኢላላ ደነቦ” ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑ ያለምንም አድልዎ ለሁሉም ሀዘንተኛ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በግለሰቦች የሚደረግ ለቅሶም በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን ስሜቱ ተቀራራቢና አንድ አይነት ነው። ስሜቱን በኦሮምኛ ተናጋሪው ክፍል በሚቀርበው ምሳሌያዊ ለቅሶ ላይ መመልከት ይቻላል። ልጇ የሞተባት እናት እንዲህ ትላለች።
ያ ሙጫኮ
ዋንጫን ጨብዴ፣
ዳዲን ነገላቴ፣            
ያ ሙጫኮ የሰቲ ረገቴን ደምቴ!
ትርጉሙ/ የኔ ልጅ! ዋንጫው ተሰበረ
ወይኑ ፈሰሰ
አንተ የኔ ወይን ነህ!
ለምን ብቻዬን ተውከኝ!
የኔ ልጅ!
እያለች እናት ታለቅሳለች።
የሞተው አባት ከሆነ ደግሞ
“ኢሳን ዴክቱ አባባ!
ኤሳን ጣሊያኒን ከሌ!
ኢንተዉ! ኢሳን“ ዴክቱ!
ትርጉሙ:
የት ትወስዱታላችሁ?
መልሱት!
ሀገሩን ከጣልያን ፋሽስት የተከላከለ ነው።
አርበኛ ነው፣ እሱ አይሞትም!
ተዉት! አትቅበሩት! እያለ ወዳጅ ዘመድ ይላቀሳል።
ይህ እንግዲህ በባህል ውስጥ ያለ በሀዘን ጊዜ እንደሁኔታው ግጥሙን እየለዋወጡ ዜማውንም እንደ አስፈላጊነቱ እያሻሻሉና ለድምፃቸው እንዲስማማ እያደረጉ የሚያዜሙት ነው።
ለመሪዎች ሞት የተደረገ ልዩ የዜማ ድርሰት በኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶም አይታወቅ። ለምሳሌ የንጉሰ ነገሥቱ የዐፄ ሀይለ ስላሴ ባለቤት እቴጌ መነንም ሆኑ፣ ልጃቸው ልዑል መኮንን በሞቱበት ወቅት ሙዚቀኞች አዲስ የዜማ ድርሰት አላቀረቡም። ሙዚቀኞች ተገደውም ሆነ ወደው ሙያቸውን አሳልፈው እጅ መንሻ አላደረጉትም። በዘመናችን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት አስመልክቶ በርካታ ዘፈን እየተደረሰ መሆኑ እየተሰማ ነው። የሙዚቃ ጥበብ ህዝብን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ባህልን ታኮ ስሜትን እየኮረኮረ የሚያሰልፍ መሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በ እነ ናፖሊዮንና በነ ሂትለር መንግስት ነው። ይህ አይነቱም ድርጊት በርካታ የኪነ ጥበብ ሰዎች ሙያውን የፖለቲካ መጠቀሚያ አናስደርግም ብለው ለስደት ተዳርገዋል።  ወቅቱ ሙዚቃ ለናዚ ፓርቲ መቀስቀሻ እንዲውል መደረጉ በሪቻርድ ሰትራውስ ታላቅ የሙዚቃ ስብዕና ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያለፈ ነው። ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች ምስጋናቸውንም ሆነ ነቀፌታቸውን በቅኔ ግጥማቸው ሲገልፁ የኖሩ ናቸው። ለምሳሌም ያህል
ወንድሜ ብቻውን ሲሄድ አለት ላለት፣
እሰይ የምስራች ደመና ሆነለት።
እንጨቱ ተጓሮ ቋሚ እየኮራ፣
አለማገር ቀረች ቤቴ ተዠምራ።
አልተከልኩ እንኳ ከጓሮዬ፣
ዱባ ለመከራዬ። ወዘተ…
 እያለ የሚፈልገውን ነገር በሰምና ወርቅ ግጥም የሚገልፀው አዝማሪ፣ ተሸማቆ ሳይሆን ደረቱን ነፍቶ ያመነበትን ነገር ጎላ ባለ ድምፁ በመዘመር ነው። ይህ ባህላዊ ጥበብ ተንቆና  ተረስቶ ማንም የሙያው ሰው ነኝ ባይ እየቀነጣጠበ እራሱ የሚሰማውን ለመግለፅ ቢጥር ብራቮ አበጀህ የሚባልበት ጉዳይ አይደለም። አቶ መለስን በሙሾ በለቅሶ መቅበር ይቻላል ከእውነትና ከሀቅ ከተጋጩ። አዳዲስ ዜማዎች እያወጡ የኢትዮጵያን ህልውና በሚፃረር ፍልስፍና ዙሪያ ሲሽከረከር የኖረ ግለሰብ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዐላማ ላይ “ባፎሜት” በሚል የሚታወቀውን ባለ አምስት ጉጥ ያለው የሰይጣንና የጥንቆላ ምልክት እንዲለጠፍ ያደረጉ ቡድኖች መሪ ግለሰብ
መሆኑ እየታወቀ፣ ድንበሯን ማስደፈሩ። መሬቷን ለባዕዳን መሸጡ፣ እንደ ፀጋ ተቆጥሮ የኢትዮጵያ ህዝብ አዳኝ መስሎ እንዲታይ ለማድረግ መሞከር ከእውነት ጋር መጋጨት ነው። አቶ መለስ እንደሰው መቀበር ቢችልም እንደ ኢትዮጵያዊ በእንባ ለመሸኘት ሀቁ አይፈቅድለትም:።  የኪነ ጥበብ ሰዎችም ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ብለው እውነትን በሀሰት ለመለወጥ መሞከር ሙያውን ማዋረድ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ከመለስ በፊትም ነበረች ከሱ በሁዋላም ትኖራለች!!

No comments:

Post a Comment