Translate

Saturday, September 8, 2012

በኢህአዴግ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ቀጥሏል


(Sept. 9) አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት፤ በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል የተፈጠረው ሽኩቻ እንደቀጠለ ሲሆን፤ በመጪው የኢትዮጲያ አዲስ አመት የመጀመሪያ ሳምንት፤ 180 የኢህአዴግ ማእከላዊ ምክር ቤት አባላት፤ ጉዳዩን እልባት ለመስጠት እንደሚሰበሰቡ ለማወቅ ተችሏል።
የ4 ፓርቲዎች ግንባር የሆነው ኢህአዴግ፤ ከያንዳንዱ ፓርቲ የተውጣጡ 45 የማእከላዊ ም/ቤት ዓባላት፤ በድምሩ 180 የምክር ቤት አባላት ተሰብስበው ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያከራክር የቆየውን፤ የኢህአዴግ ሊ/መንበርና፤ የጠ/ሚ/ርነት ቦታን ጉዳይ እንደሚቋጩት ይጠበቃል።
የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በነበሩት ሁለት ቀናት የሚንስትሮች ምክር ቤት፤ የአቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝን ተጠባባቂ ጠ/ሚ/ርነት ቢያፀድቅም፤ በተለይም በሕውሃት በኩል በቀረበው ተቃውሞ ምክንያት፤ የአቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትርነት ለግዜው እንዲዘገይ ተደርጎ፤ ባለፈው ማክሰኞ የተሠበሰቡት 36 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ጉዳዩን በምክር ቤቱ እንዲወሰን ወደ ም/ቤቱ መርቶታል።
በመጪው ሳምንት 180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ማዕከላዊ ም/ቤት ተሠብስቦ፤ የኢህአዴግን ሊ/መንበርና ም/ሊ እንደሚመርጥ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የህውሃት ስራአስፈጻሚ አባላትና የቀድሞ የህወሀት ታጋዮች፤ የምክትል ሊ/መንበርነቱን ቦታ ለመያዝ እየተሯሯጡ ነው ሲሉ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment