Translate

Thursday, December 6, 2012

በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸውህዳር


በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸውህዳር


Add caption

ኢሳት ዜና:- 

መንግስት የችግሩን ምንጭ ፈልጎ እንደማግኘትና መፍትሄ እንደመፈለግ  በመምህራን ላይ ማሳበብን መርጧል።  የመንግስት አቋም መምህራን ወደ አረብ አገራት ስለሚደረገው ስደት በቂ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለተማሪዎች አልሰጡም የሚል ሲሆን፣ የመምህራን አቋም ደግሞ  ” ተማሪዎች የሚሰደዱት  ተስፋ በማጣታቸው ነው” የሚል ነው ።

በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር  ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።  መንግስት መምህራንን በመሰብሰብ ለማወያየት ሙከራ አድርጓል።

እድሉ ቢገኝ ከአገሪቱ ህዝብ 40 በመቶው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ፍላጎት እንዳለው በውጭ አገር የተደረገ አንድ ጥናት ከአመት በፊት ማመላከቱ ይታወሳል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ሰላጤ እንዲሁም በሰሀራ በረሀ የውሀ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment