Translate

Tuesday, June 28, 2016

“የትግራይ ሰዎች ተፈናቀሉ” አጉል የወያኔ ጩኸት በሽንፋ – ጎንደር

ሊቁ  እጅጉ እና አዳነ አጣናው
ላለፉት 40 ዓመታት አገርን  በማፈራረስ አባዜ  የተጠመደው  ወያኔ  በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ምክንያቶችን  በመፍጠር  ሲፈልግ  የትግራይ  ሕዝብ  ልጆቹን  ስለሰዋ  የትግራይ  ግዛት መስፋት አለበት፣ በሌላ  ጊዜ ደግሞ አባላቶቹን  አደራጅቶ  በተለያዩ   የሀገሪቱ  ክፍሎች በማስፈር፣ ብሎም  ከባንክ ብድር  በገፍ እንዲያገኙ በማድረግ  በሰፈሩባችቸው  አካባቢዎች ሁሉ  የንግድና  የእርሻ ሥራዎችን  በበላይነት እንዲይዙ አድርጓል። ስለሆነም  ወያኔዎች ተደራጂተው በሰፈሩባችው አካባቢዎች  ሁሉ  የአካባቢው ተወላጅ  በራሱ ቀዬ የበይ  ተመልካች  እንዲሆን  ተደርጓል ። በአጭሩ  ወያኔዎች ለ25 ዓመታት በመላ  ሀገሪቱ  የሚያካሂዱት  ዘረፋና የማያባራ የግዛት ተስፋፊነት ሌላው ቀርቶ በራሳቸው አምሳል የፈጠሯቸው  አጫፋሪ  የጎሣ  ድርጅቶች  እንኳ  ገደብ  የለሹን የወያኔ  ሁሉም  የኔ ይሁን በሽታ  ሥራ ላይ ለመትግበር ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መጥቷል።
“<በጅብ  ጅማት  የተሰራ ክራር  ዜማው ሁልጊዜም  እንብላው> እንደሚባለው  ወያኔ ዛሬም እንዳመሰራረቱ ታላቋን  ትግራይ  የመፍጠር  በሽታው በተጠናከረ  መልኩ  ቀጥሏል። ወያኔ በጠባብነት ታዉሮ  አትዮጵያን  በስፋትና በአኩልነት ሊመራ  ቀርቶ እወክለዉ አለሁ የሚለውን  ትግራይን  እንኳ በአግባቡ በእኩልነት መወከል የተሳነው  የአንድ  አካባቢ ስብስብ  ነው፡፡. ለይስሙላ የትግራይ  ሕዝብ  ወኪል  ነኝ  ቢልም  እውነቱ  ግን በበላይነት እና በዋናነት የሚመራው  ከአርባ ዓመት በፊት አሽአ ማለትም አድዋ፣ ሽሬ፣ አክሱም ብሎ የመገንጠል ዓላማ አንግቦ  በሕቡእ  የተደራጀው ከሦስት አውራጃዎች በመጡ እጅግ በጣም ጠባብ  ግለሰቦች ሲሆን  ከኢትዮጵያ ጎሳዎች ያልተቀላቀልን  ‘ንጹሕ ትግሬ  እኛ  ነን የሚሉ በዝምድና  እና በጋብቻ የተሣሰሩ የአውራጃ አንጀኞች ናቸው።

ይህ የአሽአ  ቡድን  ምንም እንኳ  በታሪክ ስህተት የኢትዮጵያን  በትረ ሥልጣን  ቢይዝም  ሌት ከቀን ከተነሣበት ጠባብ  የአውራጃና የጎሣ ዓላማውን  አዉን ከማድረግ  ወደኋላ አላለም። ስለሆነም  እድገቱን  እና ሥልጣኑን  የሚገመግመው  የግል  ቴ  በሚለው  በትግራይ  የግዛት መስፋፋትና  ወያኔዎች ከሌላው ኢትዮጵያዊ  በላቀ  በሚያከማቹት  የሀብት መጠን  ነው።
አንገብጋቢዉና በማንም ኃይል ሊገታ የማይችለው  የወልቃይት  ሕዝብ  ጥያቄ  እየገፋ ከመጣ ወዲህ ደግሞ ወያኔ የብአዴንን  ባለመዋልነት  ጥያቄ  ውስጥ  አስገብቷል። ለዚህም  ነው  ሰሞኑን የወያኔ የስለላ ድርጅት ብዙ ከመከረ  በኋላ አዲስ ዐይን ያወጣ በጎንደር ሕዝብና  እንዲሁም በራሱ የበክር ልጅ ብአዴን ላይ ያነጣጠረ  ዘመቻ ከፍቷል።  ይህ ያልተጠበቀ  የወያኔ የትግራይ ሰዎች በጎንደር ተፈናቀሉ አዲስ ክስ አንዳንድ ጌቶች ለአሽከሮቻችው አመቺ እንዳልሆኑ  ሁሉ  ወያኔም  እንዲሁ ለብአዴን እና ለሚገዛው ሕዝብ  ያልተመቸ  ጌታ ሁኗል። ስለሆነም  የወያኔን  ገደብ የለሽ  ፍላጎት ማርካት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ወያኔ ወልቃይትን ስጡኝ አለ፣ ወሰደም። ከዚያም ጠገዴን አምጡ አለ፣ ዝም ተባለ። ብሎም ዳንሻን፣ ሁመራን እስከ  ሱዳን ጠረፍ  ወሰደ፡፡ በወሎና እዲሁም  በአፋር ግዛቱን አስፍፍ።
“ወያኔ የትግራይ ሰዎች በጎንደር ሽንፋ  አካባቢ>  ተፈናቅለዋል  እናም  የበኩር ልጄ ብአዴን  የሰጠሁትን  የወያኔዎችን  የበላይነት  የማስጠበቅ  ኃላፊነት  አጓድሏል፣ ስለሆነም ብአዴንም  ሆነ የአካባቢውን  ሕዝብ እንቀጣለን  እያለ ነው። በውጭ ሀገርም ያሰማራቸው የታላቋ  ትግራይ  አቀንቃኞች  ኃላፊነት በጎደለው መልክ  የግል መንግሥታችን  የሚሉት ወያኔ በአፋጣኝ በብአዴን እና በጎንዳር ህዝብ  ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ከመወትወት አልፈው ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ናቸው።
የወያኔ ስልታዊ ተስፋፊነት-
  • በመጀመሪያ ከትግራይ ክልል ለሰፋሪነት መስፈርት  ያሟላሉ  የሚላችዉን ይመለምላል ፡፡ ከዚያም ሥልጠና ይሰጣል፣ ሥልጠናውም  በተናጠል  እና በቡድን  ለም በሆኑ  ሱዳንን በሚያዋስኑ  የኢትዮጵያ ይዞታዎች  አካባቢ በንግድና በእርሻ እንዴት አንደሚሰማሩ ፣ያደራጃል፡፡
  • ብአዴኖችን በቀጥታና  በሥውር ለወያኔ ሰፋሪዎች ሙሉ እርዳታ እንዲያደርጉ ይታዘዛሉ
  • ለተወሰኑ ተመልማዮች  ከፍተኛ  ገንዘብ  ለሥራ መቋቋሚያ  ከንድፈ ሃሳብ ጋር ይሰጣቸዋል
  • ለገሚሶች ደግሞ ያለ ቅድመ  ሁኔታ የባንኮች የመበደሪያ ሕግ  ተጥሶ  እስከ  5 ሚሊዮን ብር ድረስ እንዲበደሩ ይደረጋል።
  • ቀስ በቀስ ብዛት ያለው ወያኔ ከሰፈረና ሀብት ንብረት ካፈሩ  በኋላ <ማኅበረ ትግራይ> የሚባል ቡድን  ያቋቁማሉ፣ ከ30 በላይ አባወራዎች  ሲደርሱ  ደግሞ ከትግራይ ክልል በመጡ የወያኔ ባለሥልጣኖች  አዲስ አደረጃጀትና ሥልጠና ይሰጣቸዋል። ከገቢያቸውም ለትግራይ ክልል ግብር ይከፍላሉ።
  • ልጆቻቸው ትግርኛ እንዲማሩ መምህር  ከትግራይ  ያስመጣሉ
  • 50 አባወራዎች ሲደርሱ የራሳቸው ልዩ ዞን እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ
ለምሳሌ  በአብደራፊ ማለትም በታች አርማጭሆ ወያኔ የሠራው ቲያትር- በ1992-93 ደርግ እንደወደቀ በስደት ሱዳን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ  ሰዎች ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ይመለሱ በሚል ዘይቤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ  30 አባወራዎች ለሱዳን ቅርብ  ለሆነችው አብደራፊ ላይ እንዲሠፍሩ ሆነ። የአካባቢው ሕዝብም ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ተቀበላቸው፡፡ የመሬትም  ጥበት ስለሌለ  ሁሉም  መሬት አገኙ። ከድህነትም ተላቀቁ። ትንሽ ከቆዩ  በኋላ  ዘመዶቻውን  ከትግራይ  ማስመጣት ጀመሩ። የትግራይ  ሰዎች እየበረከቱ  መጡ፣ ከዚያም ለብአዴን ባለሥልጣናት ልዩ ዞን በአብደራፊ  ይፈቀድልን  ሲሉ ጠየቁ። ጥያቄው የአካባቢውን  ሕዝብ  አሳዘነ። ጉዳዩ ለአካባቢው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን  በመላ  ክፍለ ሀገሩ  ከፍተኛ  ትዝብትና ቁጭት ፈጠረ። በእንግድነት  መቀበላችን  ቀያችን  ያስወስዳል  እንዴ?  ሲሉ  ራሳቸውን  ጠየቁ። እንዳዉም ጥያቄው  ከልዩ ዞን አልፎ   የቲ ፒ ኤል ኤፍ -TPLF/  የሕዝብ  ደህንነት ሠራተኛ  ዘፀአት  በሚል ቅጽል ስም <ታህታይ አርማጭሆ የሠፈሩ ትግሬዎች ወደ ትግራይ አስተዳደር መዛወር  አለባችው  ሲል አዲስ አጀንዳ ይዞ ብቅ አለ። አብደራፊ  የት ላይ እንደሚገኝ እና እንዴት ከትግራይ ጋር ሊተዳደር እንደሚችል  ጉግል ማፕ አይቶ የራስን  ፍርድ መስጠት ይቀላል።ይህ የወያኔ ተስፋፊነት  በሠፈራ ስም በመተማ፣ በሽንፋ፣ በኦሜድላ፣ በቤን-ሻንጉል (ጎጃም) እና በጋምቤላ እየተካሄደ  ነው።
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሽንፋ ላይ በወያኔ ሠፋሪዎች እና በአካባቢው ሕዝብ  መካከል ልዩነቶች እየሰፉ መጡ።  በሠፈራ ስም የመጡት ወያኔዎች  ከጥቂት ዓመታት በኋላ  የአካባቢውን  ሕዝብ  እና  ብአዴን  የሚባለዉን  እንምራችሁ ማለት ጀመሩ። ብሎም –
  • በሠፋሪነት የመጡት ተቋቋሚ ሠፋሪዎች በቅጽበት ኢንቨስተሮች ናቸው ተብለው ከሠፈራ ወጥተው ከባንክ  በገፍ እንዲበደሩ ወያኔ አመቻቸ። የአካባቢው ሕዝብ  ከባንክ ብድር ለማግኘት ሲጠይቅ ከፈላጋችሁ   ወደ ቤን-ሻንጉል ሂዱና የእርሻ መሬትና የባንክ ብድር እንሰጣችኋለን ማለት ጀመሩ። ይህ እርምጃ ቀስ በቀስ የአካባቢውን  ተወላጆች ከአካባቢው በማስለቀቅ በምትኩ የወያኔ ሰዎችን ለማስፈር  ያሰበ ነው።
  • የወያኔ ሰዎች የሽንፋን ሕዝብ በእርሻ፣በጅምላ ንግድ፣ በችርቻሮ፣ በሆቴል  እና  በአራጣ አበዳሪነት  ከባንክ በተሰጣቸው ገንዘብ ሊያፈናፍኑት አልቻሉም። ስለሆነም የበላይነቱን  በአቋራጭ ተቆጣ ጠሩት፡፡.
  • በአካባቢው የሚገኘውን የደን  ሀብትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የከስል  ፈቃድ በብቸኝነት በመያዝ  አካባቢውን  ወደ ምድረ-በዳነት ለወጡት።
  • የእጣን/ሙጫ ፈቃድ  ከወያኔ ሰዎች ውጭ እንዳይሰጥ አስከለከሉ፣ብሎም ያለአግባብ  በአምራች  ዛፎች ላይ  ጉዳት በገፍ አደረሱ፡፡   ዛሬ የአካባቢው የእጣን ዛፎች 60% መክነዋል።
  • የአካባቢውን የተፈጥሮ  የቀርቅሃ ሀብት ከሱዳን  ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ወደሱዳን  በመላክ  እንዲጨፈጨፍ አድርገዋል።
  • በአካባቢው ወደ ሱዳን የአስመጭ እና የላኪነት የንግድ ፈቃድ ያለተወዳዳሪ እንዲይዙ ተደረገ።
  • ሽንፋ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ሰዎች  የወያኔን ድርጅታዊ  መዋቅር  ዘረጉ።
  • ከትግራይ ክልል የመጡ የወያኔ አመራሮች በ6 ወር አንዴ ምስጢር በሆነ መልክ ለ3 ቀናት ሰሚናር ይሰጣሉ።
  • አብዛኛዎቹ ግብር በዛብን በማለት ለአካባቢው አስተዳደር ለብዙ ዓመታት ግብር መክፈል አቁሙ።
  • የቀበሌና የመንግሥት መሰብሰቢያ አዳራሾችን ያለቅድሚያ ጥያቄ በፈለጉበት ጊዜ የመስብሰብ መብት እንዲሰጣቸው ከመጠየቅ አልፈው ማሳፈራራት ጀመሩ።
  • የአካባቢን ጸጥታ በተመለከተ ሃላፊነት ይሰጠን  አሉ።
  • የአካባቢውን ሕዝብ እየሰለሉ ፀረ ወያኔ ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን ሰዎች ከትግራይ ክልል በመጡ የፀጥታ ኃይሎች አሳፍነው ወደ ትግራይ እንዲወሰዱ አደረጉ።
  • በወያኔ የበዓላት ቀን ላይ የትግራይን  ክልል ባንዴራ ማውለብለብ  ጀመሩ።
  • የወያኔ ምሥረታ በዓል በአካባቢው በሕዝብ  ዘንድ በብዓልነት እንዲከበር ጠየቁ ..ወዘተ።
በአጣቃላይ  ግንኝነቱ  የገዠና ተገዥ እየሆነ መጣ። ለሠፈራ  የመጡ ሰዎች አልፈው ተርፈው የፖለቲካውንና የኢኮኖሚውን  አውታር የግል አደረጉት።   የአካባቢው ሕዝብ ብአዴን ለሚባሉ የወያኔ አስፈጻሚዎች አቤቱታ  ቢያቀርብ  ሰሚ  ጠፋ። በዚሁ ያላሰለሰ የወያኔ ሠፋሪዎች በደል ምክንያት ተቃውሞው እየበረታ መጥቶ የውስጥ እሳት ሆነ። ብሎም አመፅ ቀሰቀሰ። በተነሣው ተቃውሞ ድንጋይ በአንዳንድ ሱቆች ላይ ተወረወረ። ዘረፋ ግን አልተፈጸመም። የወያኔ ሠፋሪዎች <ጌታውን የተማመነ በግ..> እንዲሉ ለሳምንት ያክል ንብረታቸውን  ሳይከታተሉ  ሰነበቱ፡፡ ከዚያም የአካባቢውን  አስተዳደር አልፈው ወደ አዲስ አበባ  እና ባሕርዳር ጮኹ። የጠፋ ንብረት ካለ ዝርዝሩን  አቅርቡ  ሲባሉ ከነበራቸው ንብረት ከአሥር እጥፍ በላይ እንዲከፈላቸው ጠየቁ።  ብአዴንም ምንም ሳያቅማማ  ለመክፈል ከፍ ዝቅ እያለ  ነው።
አዉነቱ ይህ ሆኖ እያለ ተገልብጦ የአካባቢው ሕዝብ በበዳይነት ተፈርጆ የወያኔን ፍርድ እየጠበቀ ይገኛል። ወያኔዎች ተደፈሩ ቁጪት እና ትእቢታዊ  ጩኸት  ጎንደር፣ ባሕር ዳር፣  አዲስ አበባን አልፎ  የአድዋን  ከተማ  እያስፈከረ  ነው።  የወያኔ የአሁኑ የሽንፋ ጩኸት ዋና ዓላማው ወያኔን በመሸከም የጎበጠውን  አሮጌ  ብአዴንን አፈራርሶ  በአዲስ  ሹመኞች አመራር መቀየር ነው። ወያኔ ወልቃይት ላይ ያለበትን የሕዝብ ተቃውሞ  የትግራይ ሰዎች ተፈናቀሉ  በሚል ማምታታት  እና  ብአዴንን መብላት ነው። ለዚህ የወያኔ አዲስ እቅድ  በዋና አስፈጻሚነት ካሣ ተክለብርሃን  እና ዓለምነው መኮንን ተመልምለው አዲስ ቃለ መሓላ ፈጽመዋል። ውጤቱን በቅርቡ የምናየው ይሆናል። በአጎረስኩ እጄን ተነከስኩ እንደተባለው ለሠፈራ የመጣ ሕዝብ ያስፋሪውን ሕዝብ እጅ ሊነክስ አይገባም።   በደል በበዛ  ቁጥር በተቃራኒው አመፅን ይፈጥራል።  የሽንፋ አመፅ የዚሁ የተራዘመ የውያኔዎች የበደል ዉጤት ነው። በርግጠኝነት ግን የትግራይ ጥላቻ እንዳልሆነ ሙሉ በሙሉ መናገር የቻላል።

No comments:

Post a Comment