Translate

Sunday, June 12, 2016

20 የሚሆኑ የሕወሓት ደጋፊዎች በአውስትራሊያ ኢትዮጵያዊውን የመንግስት ተቃዋሚ ደበደቡ | ቪዲዮ ይዘናል


(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሜልበርን አውስትራሊያ የጠራውን ሕዝባዊ ሰብሰባ ለመቃወም ከወጡ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ 20 በሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ደበደቡት:: ኒውስ 7 የተሰኘው የአውስትራሊያ የመረጃ ቴሌቭዥን የተጎጂውን ኢትዮጵያዊ ፊት በደም ተለውሶ አሳይቶታል::

ሰሞኑን በአውስትራሊያ የቆዩት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ; የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርና የሶማሊያ ክልል አመራሮች የተገኙበትን ይህን ስብሰባ እንዳይካሄድ እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብ አዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ከጠየቁት መካከል በፎቶግራፍና ከታች በቭድዮ የምትመለከቱት ወጣት መደብደቡ በዲያስፖራው ውስጥ ያለውን በተለይ የሕወሓት ደጋፊዎች እና የሌሎችን ኢትዮጵያውያን ልዩነት የበለጠ ያሰፋዋል ተብሎ ተሰግቷል::
በሕወሃት ደጋፊዎች በአውስትራሊያ የተደበደበው ወጣት ስሙ ፈይሳ እንደሚሰኝና የትውልድ ክልሉም ኦሮሚያ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
ኢትዮጵያውያኑ ተቃዋሚዎች በሕወሓት መንግስት ወኪሎች ላይ የከረረ ተቃውሟቸውን ከማቅረባቸውም በተጨማሪ የአውስትራሊያ መንግስት ይህንን በሰብ አዊ መብት ጥሰት; በግድያና በ እስራት የሚታወቀውን መንግስት እንዳይተባበርና እንዳይረዳ ጠይቀዋል::
ይህ ሕወሓት የጠራው ስብሰባ በሕዝቡ ብርቱ ተቃውሞ መቋረጡም ታውቋል::

No comments:

Post a Comment