Translate

Monday, December 10, 2012

በእብሪተኛው የወያኔ አገዛዝ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ሰው በላይ ሆነው ማውራት ተከለለክሉ


በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ጎጆ ቀልሰው ከሚኖሩበት ሰፈር ህገወጦች ናችሁ በሚል ሰበብ በማንአለብኝነት እብሪት በተወጠረው ወያኔ ትእዛዝ ጎጇቸው ፈርሶ እንዲፈናቀሉና ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረጉት ዜጎች በሀገራችን መኖር ካልቻልን ወደ ሌላ ሀገር ሄደን በስደተኝነት ለመኖር እንችል ዘንድ ሁኔታዎች ይመቻቹልን ማለታቸው ተሰማ።
ተፈናቃዮቹ በየአካባቢዎቹ በመዘዋወር ላነጋገራቸው የግንቦት 7 ዘጋቢ ሲገልጹ ህገወጡ ወያኔ ህጋዊ ሰነድ ይዘን ህገወጦች ናችሁ ይለናል በጣም የሚገርም ነው፤ ሌላው ቀርቶ በህገ ወጥ መንገድ የሰፈሩ አንዳንድ እንኳን ቢኖሩ ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት ቢሆን ኖሮ አስቀድሞ  መጠለያ በማዘጋጀት ሊያዛውራቸውና መሬቱን ሊጠቀምበት ይችል ነበር።ነገር ግን ለዜጎች አንዳችም ደንታ የሌለው ዘረኛውና ስግብግቡ ወያኔ ማንንም ከማንም ሳይለይ ከመሬቱ የሚያገኘውን ጥቅም ብቻ በመመልከት ቤቶቻችንን በላያችን ላይ በማፍረስ ሜዳ ላይ ጥሎናል ብለዋል።

አሁን ደግሞ ይግረማችሁ ብሎ  ለችግራችን ተወያይተን መፍትሄ እንኳን እንዳንሻ ከሁለት በላይ ሆናችሁ መነጋገር አትችሉም በማለት የግፉን መጠን በላይ በላዩ እየደረበብን ይገኛል በመሆኑም በሃገራችን መጠለያ የማግኘት መብት ከተነፈግን፣ ሁለት ሆነነ መነጋገር ከተከለከልን፣ በግፍ ከተደበደብን፣ ልጆቻችን ለሞት አደጋ እንዲጋለጡ ከተደረጉ እንደምን የዚች ሀገር ዜጎች ነን ማለት እንችላለን? ያሉት ተፈናቃዮች የትም ብንሄድ ከዚህ የባሰ ነገር ስለማይመጣ ዜጎቹ መሆናችንን የሚቀበል መንግስት እስኪመጣ ወደ ሌላ ማንኛውም ሀገር ለመሰደድ ወስነናል በማለት አብራርተዋል።
አንዲት እናት በበኩላቸው ይሄን ሁሉ ገንዘብ የሚያግበሰብሱት መቼ ሊበሉት እንደሆን አላውቅም፤ቤታችንን በላያችን ላይ በማፍረስ አውላላ ሜዳ ላይ የጣሉን መሬቱን ለመሸጥ ነው፤ እኔ የሚገርመኝ ከመለስ እንኳን አይማሩም፤እሱ ይሄው ከሰበሰበው ጥቂቱን እንኳን ሳይበላ አፈር ገባ፤ድሃን ቢንቁትም አምላክ አለው፤ የሱ ፍርድ የመጣ ቀን መግቢያ ይጠፋል፤ እናም ያክፉ ቀን ሳይመጣ እባካችሁ ግፍ ይብቃችሁ፤ስግብግብነት ይብቃችሁ፤ለወገኖቻችሁ አስቡ በልልኝ እንዳሉት ዘጋቢያችን ገልጿል።
በዚህ የሰሞኑ የቤት ማፍረስና ዜጎችን ሜዳ ላይ የመጣል ዘመቻ ከሰባ ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው፣መደብደባቸውና ሜዳ ላይ መበተናቸው መዘገቡ ይታወሳል።

    No comments:

    Post a Comment