Translate

Tuesday, January 8, 2013

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው


የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።
በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን  መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች  ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።

ግለሰቡ ወንጀሉን ከመፈጸሙ በፊት የተለዋወጣቸው መልእክቶች የFBI ወንጀል መርማሪዎች እጅ በመግባታቸው ሳቢያ እርሱና አብረው የሚኖሩ ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ ክትትልና ምረመራ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከተባባሪዎቹ ጋር  የተለዋወጣቸው መልእክቶች ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደቦስተን የመሄዱን አጋጣሚ በመጠቀም በመሳሪያ ተኩሶ የመግደል እቅድ አውጥቶ ድርጊቱን ለመፈጸም ወይንም ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ እንደነበር በግልጽ እንደሚያሳዩ ታውቋል።
የቦስተን ቅርንጫፍ FBI ቃል አቀባይ እና ልዩ መርማሪ ( special agent) የሆኑት ግሬግ ኮምኮዊች በምርመራው ሂደት  ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ FBI እንዲህ አይነት ወንጀሎችን በ ቸልታ እንደማያልፍ ገልጸው በውጭ መንግስታት ሰላዮችም ሆነ ተወካዮች የሌሎችን ሰብአዊ መብቶችን በሚገፍ ህገወጥ ወንጀል የተሰማሩ ካሉ ኢትዮጵያዊያን በቸልታ ማልፍ እንደማይገባቸው እና በአካባቢያቸው ለሚገኙ የFBI  ቅርንጫፎች ጥቆማ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል። መርማሪው አክለውም FBI እንዲህ አይነቱን ጥቆማ በአግባቡ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል። “
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመተቸት የሚታወቁት የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን የግድያ ሴራውን ያከሸፉትን የFBI መርማሪዎች አድንቀው ፣ ህወሃት አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ታውቆ ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካን ሀገር እንዲህ አይነት ወንጀል ሊፈጽም መንቀሳቀሱ በችልታ አይታይም ብለዋል።
በካምቦድያ በሰው ልጆች ላይ አስከፊ ሰቆቃና ጭፍጨፋ የፈጸሙ የካሜሩዥ ባለስልጣናትን ለፍርድ በማቅረብ አለማቀፍ እወቅና ያገኙት ፕሮፌሰር ስታንተን እንዲህ አይነቱ ወንጀል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ግኡሽ አበራን በቅርብ የሚያውቅ አንድ ኢትዮጵያዊ የቦስተን ነዋሪ፣ ግለሰቡ ከከፍተኛ የህወሃት ባልስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውና የቀድሞው አምባገነን መሪ የመለስ ዜናዊ አምላኪ እንደነበር፣ የእርሱ መዋረድና መሞት በጣም ካበሳጫቸው በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ የህወሃት ጀሌዎች አንዱ መሆኑን ገልጿል። በማከልም “ከሁሉ የከፋው ግለሰቡ በዘረኝነት ዛር የተለከፈ ስለሆነ ህወሃቶች እንዲህ አይነቱን ሰው ለእኩይ አላማቸው መጠቀማቸው የተለመደ ነው፣”  በማለት አስረድቷል::
ጋዜጠኛ አበበ ገላው “ህወሃት አሸባሪ የማፊያ ድርጅት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የነበሩብኝን የጽጥታ ስጋቶች ችላ ባለማለት ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት ከማመልከት አልፌ የቤተሰቤንም ሆነ የራሴን ደህንነት ለማረጋገጥ ቀደም ብዬ እርምጃ ወስጃለሁ ወደ ፊትም እወስዳለሁ” ብሏል።
የFBI መርማሪዎች ወንጀሉ እንዳይፈጸም አስቀድመው እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ቦስተን ውስጥ ሮክስቤሪ በመባል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን እና ግኡሽ አበራ ከሌሎች አራት ኢትዮጵያዊን ጋር በጋራ ይሚኖርበትን ቤት የበረበሩ ሲሆን፣  ወደ ሁለቱ የቤቱ ነዋሪዎች ስራ ቦታ ድረስ በመሄድ ምርመራ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

    No comments:

    Post a Comment