Translate

Thursday, January 24, 2013

አባ ሕዝቅኤል ለምን ስብሰባ ረግጠው ወጡ?


“የማንም አሿሿሚ አልሆንም የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም”በማለት አራት ወራት የቀረውን የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነታቸውን የሚለቁ መሆናቸውን በደብዳቤ ገለጡ እየተባለ ሰሞኑን

ethiopian orthodox church in Addis Ababa የሚወራላቸው አባ ሕዝቅኤል  ቀደም ሲልም ስብሰባ ረግጠው ቢወጡ የፈረሰው ቀኖና ይመለስ ብለው እንዳልሆነ መታወቅ አለበት
አባ ሕዝቅኤልና በአዲስ አበባ የሚገኙት የሲኖዶስ አባለት ለእርቅና ለሰላም እንዲሁም ለሀያ ዓመታት የዘለቀውን የቤተ ክርስቲያን መለያየት ወደ አንድነት ለማምጣት በቅንነት እና ግልጽ በሆነ መንገድ ቢጓዙ ኖሮ ለዚህ ለከፋ መከፋፈል እንዲሁም ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ባልተዳረጉ ነበር ይልቁንም አባ ሕዝቅኤል  የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አለ መባሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና ቅዱስ ሲኖዶስ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ደንቦችን ከማውጣት በቀር መንግሥት ጣልቃ አልገባም በማለት በአደባባይ ተናግረው ጸሐይ የሞቀውን እውነት የካዱ አባት ናቸው አቡነ ገብርኤልም ይሕንኑ ሀቅ ክደው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት ቃል የአባ ሕዝቅኤልን ውሸት ደግመውታል

ይልቁንም አባሕዝቅኤል በአፋቸው ስለ እርቅና ሰላም እያወሩ እሳቸውና መሰሎቻቸው  ከእኛም ወገን ይድረሰን ከሚሉት ግብረ አበሮቻቸው የሚፈልጉትን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የሚሄዱበት መስመር እየተዘጋ በመንግሥት የሚደገፉት የነ አባ ሣሙኤል ክንድ እየበረታ ሲሄድ  ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም ማለቱ እና  አራት ወር የቀረውን የጸሀፊነት ሥልጣን እለቃለሁ ማለቱ ምክንያታዊነቱ  ፈጽሞ አይታይም
በሐቅና በእውነት የአባ ሕዝቅኤል አቋም ሲታይ ፣
ethiopian orthodox church Addis Ababa, ethiopia
ከወያኔ ጋር አብረው አ/አበባ የገቡት አባ ተከስተ የአሁኑአባ ሳሙኤል
1ኛ/የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከሁለትና ከዚያም በላይ ተከፋፍላ የምትገኘው ፓትርያርክ መርቆሬዎስ ያለ አግባብ በፖለቲካ ውሣኔ መንበራቸውን እንዲለቁ መደረጉን አምነው አይቀበሉም፣
2ኛ/ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ ፓትርያርክ በሕይወት እያለ አባ ጳውሎስ መሾማቸው ቀኖና መሻሩን አምነው ለመናገር አይደፍሩም ታዲያ የአባ ሕዝቅኤል አቋም እና እውነት የት ላይ ነው ?
ሁሉም ማወቅ ካለበት እርቅ እንዲመጣ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እንዲመለስ ከተፈለገ ከእርቁ በፊት የምርጫ ሕግ ማውጣት ለምን አስፈለገ ? እርቁ መቅደም አልነበረበትም ? አውነት እንነጋገር ከተባለ የሰላሙን በር አስቀድመው የዘጉት አባ ሕዝቅኤል  አይደሉምን ?ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ይልቅ የቁጥር ስሌት ገብተው አምስት ስንል ኖረን አራት አንልም ብለው መግለጫ ከመስጠት አልፈው ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በፓትርያርክነት ለመቀበል አንችልም ይልቁንም  ታሪክ ይፋለሳል አምስተኛ ፓትርያርክ እያልን ኖረን ከ20 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ ይህ አስቸጋሪ ስለሆነ ቀኖናውንም ታሪኩንም የሚጥስ ስለሆነ ነው እንጂ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ቦታቸው እንዳይመጡ የጠላ ማንም የለም፡፡ ሁሉም ሰላሙን ፈልጓል፡፡ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር መጥተው በፈለጉበት ቦታ መቀመጥ ይችላሉ፡፡ ሰላሙ ተመስርቶ በውጭ የሚገኙ አባቶቻችን አዚህ መጥተው የመምረጥም የመመረጥም ዕድል ይኖራቸዋል፡፡በፈለጉበት ቦታ እንደማንኛውም ሰው ገብተው መቀመጥ ይችላሉ በማለት በአንድ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ደግመው አረጋግጠዋል
አባ ሕዝቅኤል እውነት ለመናገር የማይደፍሩ በተለያዩ ሚዲያዎች እንኳን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ አስተያየታቸውን  ለመናገር ቀጠሮ የሚያበዙ ነገሮችን በማድበስበስ ግልጽ አማርኛ ለመናገር ቋንቋ የሚያጥራቸው ግለሰብ ናቸው ታዲያ በምን መመዘኛ ነው አባ ሕዝቅኤልን ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ቆሙ የምንለው
ዘመነ ካሣ
ከጀርመን

No comments:

Post a Comment