Translate

Tuesday, January 29, 2013

ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ


ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ

ማስታወሻ፥ ከግብጽ ወጣቶች ምን እንማራለን
tahrir_sq_protest_BBC
እኛ የመጨረሻዎቹ የሚል አንድ ጽሁፍ በድረ ገጾች የሚሽከረከር አይቼ፣ እውን እንዴት ቀን ቀንን ዓመት ዓመትን እየተካው ዓለም ምንኛ በተጨባጭ በግብርም፣ በሃሳብ በመንፈስም እንደተሽከረከረች እንደገና ልብ ብዬ ነበር። እኔም የትላንት ሰው ስለሆንኩ።
ነገር ግን እዚህ የውይይት መድረክ ውስጥ ሰገባ፣ የሃገሬ ልጆች አሁንም የዛሬ ሰላሳ ዓመት የፖለቲካ ቡድኖች የተከራከሩበትን፣ የተናቆሩበትን፣ ከዚያም ብዙ መዘዝና መዓት ሃገራችን የገባችበትን የፖለቲካ ልዩነቶችና ነጥቦች (ለምሳሌ የትጥቅ ትግል ዛሬ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም፣ ወይንም ግንባር፣ አንድነት፣ ወዘተ) አንስተው ዛሬም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሲከራከሩበት ስሰማና ሳነብ፣ ጉድ ነው፣ ዛሬም እዛው የዛሬ ሰላሳ ዓመት ከገባንበት ጭቃ፣ ይቅርታ ይደረግልኝና፣ አልወጣንም ማለት ተገደድሁ። ስለሆነም ዝርዝር ውስጥ ገብቼ እንዲህ ቢሆን እንዲህ ማለቴ ነው፣ እያልኩ ላሳምንም ልከራከርም ከቶም አያምረኝም፤ እውነት ለመናገርም ሰፊው አንባቢና ባለጉዳይ፣ ሰፊው የተበደለው ህዝባችን እንዲህ ዓይነቱ ውሃ ቀጠነ ሰልችቶታል፤ በሰላምና በብልህነት የሚታገልና የሚያታግለው ነው የሚሻው፤ ይህን ደግሞ እሩቅ ሳንሄድ ባለፈው ዓመት ሙዝሊም የኢትዮጵያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አሳይተውናል። ከሰሜን አፍሪቃው፣ በቱኒዝያ ጀምሮ ወደ ግብጽ ዘልቆ እስከዛሬ ድረስ በቆራጥነትና በብስለት ከሚራመዱት ህዝቦች ትግል አያሌ ትምህርት በመቅሰም!
እንዲህም በመሆኑ ካላይ ያነሳሁት ውይይት ውስጥ ገብቶ በሬ ወለደ ከማለት፣ በተለይም የግብጽ ወጣቶች ትግል በምን ዘይቤና ብልሃት ወደ ህዝቡ ሰረጾ በሰላማዊ አመጽ፥ በአልገዛም ባይነት፣ ያን እስተአፍ ጢሙ ድረስ የታጠቀን የሙባረክ መንግሥትን እንዴት እንዳምበረከከ አገናዝቦ፣ ምን ትምህርት እንደሚቀመስ ማየቱን እመርጣለሁ። መንግስት በሰላማዊ ታጋይነታቸው ብቻ ፈርቶዋቸው (መንግሥት የታጠቀ ቡድን አይፈራም!) በእስር ላይ የሚያማቅቃቸው፣ እነ እስክንድርን፣ እነ አንዷለምን በመንፈስ ያጠናክርልን እያልን፣ እኛም /ማለትም የተረፈው ሌላው የህብረሰብ ክፍልም ማለቴ ነው/ ከግማሽ ጎናችን ከሙስሊም ወገኖቻችን ጎን ቆመን ይልቅ፣ ያን ምድር እንዴት በሰላም ትግል ልናንቀጠቅጠው እንችላለን ብለን ብንመራመር  እጅግ ይበጃል እላለሁ። በመሆኑም በአፍላው የግብጽ ወጣቶች ትግል ጊዜ፣ ከግብጽ ሰላማዊ አመጽ ምን እንማራለን ስል፣ የወሰድኳቸውን አንዳንድ ማስታወሻዎች እዚህ የውይይት መድረካችሁ ላይ ልጋብዛችህ እወዳለሁ። ስለጉዳያችን አንድ፥ሁለት ፍሬ ነገር አያጣውምና፣ እስቲ፣ ይህንን ከተጻፈ ጥቂት የሰነበተ ጽሁፍ ተመልከቱት:-
ሕሊና ብርሃኑ

No comments:

Post a Comment