Translate

Friday, January 11, 2013

የሙስሊሙ ድል፤ የመንግስትና አጫፋሪዎቹ የሽንፈት ውሎ!!


ድምጻችን ይሰማ፡ በደሴ

የሙስሊሙ ድል፤ የመንግስትና አጫፋሪዎቹ የሽንፈት ውሎ!!
ዛሬም ይህን ጭራቃዊ ተግባሩን ለመፈፀም ደሴ ከተማን በፌደራል ፖሊሶች ሞልቷት የነበረ ሲሆን በሙስሊሙ የዳበረ አንድነት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ከትላንት ጀምሮ ከከሚሴ፣ ሃይቅ፣ ሃርቡና ሌሎች ከተሞች የፌደራል ፖሊሶችንና አድማ በታኞችን ወደ ደሴ ከተማ ሲያስገባ የነበረ ሲሆን እነዚህ አልበቁት ብሎ ዛሬ ጧት ከኮምቦልቻና ከቢስቲማ ከተማ ንደዚሁ ንፁሃን ሙስሊሞችን ለመጨፍጨፍ ወደ ደሴ ሲያግዝ ነበር፡፡

የደሴ ሙስሊም መስጂዶቹን ተቀምቶ፣ በኢስላማዊ ስነ-ምግባር አንፀው ያሳደጉት ኢማሞቹ እንደ ተራ ሰው ከመስጂድ ወጥተው ሲወረወሩበት የተመለከተው ይህ ጀግና ህዝብ የአሚሮቹን ትእዛዝ በመጠበቅ ገና በጧቱ ወደ ሸዋበር መስጂድ ይተም ጀመር፡፡ በተቃራኒው በሰላም አስከባሪ ስም ሰላምን የሚያደፈርሱት ሃይሎች የሸዋበር መስጂድን በመክበብ የጦር አውድማ አስመስለውት ነበር፡፡ ሁሉም ሙስሊም መስጂድ ገብቶ ሲያልቅ ኢማሙ ኹጥባ ለማድረግ ወደ ሚንበራቸው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ልዩ የሆነው ተቃውሞ የተጀመረው፡፡
ፕሮግራሙን ተረድተው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሶፍ ከያዙት የአህባሽ አቀንቃኞች ውጭ በመስጂዱ የተገኘው ሙስሊም በሙሉ ጀርባውን በመንግስት ለተመረጠው ኢማም ሰጥቶ ጆሮውን ያዘ፡፡ ኢማሙ ይህን ሲያይ በመደናገጥ ኹጥባው ለጥቂት ጊዜ ቆም አድርጎ እንደገና እየተርበተበተ የያዘውን ወረቀት ማንበቡን ቀጠለ፡፡ ኹጥባው ጨርሰው ለሶላት በሚቆሙበት ወቅት ሙስሊሙ መልሶ ፊቱን ወደ ኢማሙ በማዞር ከፍተኛ የሆነ የጭብጨባ ድምፅ አስተጋባ፤ ከዛም እንደገና መስጂዱ መፀጥታ ተዋጠ፡፡ ኢማሙ ከኋላቸው ያሉትን አራት ሶፍ የማይሞሉ ተከታዮቹን ይዞ ሶላቱን እስኪጨርስ ለዲኑ ዘብ የቆመው ሙስሊም እንደገና ቁጭ በማለት ጆሮውን በመያዝ ተቃውሞውን ገለፀ፡፡
በመስጂዱ ዙሪያ በመሆን የሙስሊሙን ደም ለመጠጣት እስከ አፍንጫቸው ድረስ በመታጠቅ ተዘጋጅተው የነበሩት የፌደራል ፖሊሶች የተክቢራ ድምፅ ቢጠብቁም ሙስሊሙ ልዩ በሆነ መንግድ ተቃውሞን አሰማቸው፡፡ ሶላት ተሰግዶ እንዳበቃ ሁሉም ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ መስጂዱን ለቆ መውጣት ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ግራ የገባቸው የፌደራል ፖሊሶች የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲደናበሩ እንደነበር ታይተዋል፡፡ መቼም ባዶ እጃቸውን አለመመለስ ልምዳቸው ነውና በጥቆማ ሁለት ወንድሞቻችንን በመኪናቸው ጭነው ተመልሰዋል፡፡ መንግስት ሙስሊሙን በከፍተኛ ሁኔታ በመደብደብና ከዚህም አልፎ የጥይት ቃታውን በመሳብ ሰላማዊ ተቃውሞውን ለማስቆም አስቦ የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለበለጠ ሽንፈትና ኪሳራ ተዳርጎ ውሏል፡፡ የዛሬው ልዩ የሆነ ተቃውሞ እስከዛሬ ከተደረጉት ሰላማዊ ተቃውሞዎች ለየት የሚያደርጉት ሙስሊሙ ለመንግስት ቅጥረኛ ለሆነው ኢማም ጀርባውን በመስጠትና ጆሮውን በመያዝ “በቃን አንፈልግህም” የሚል መልእክት ከማስተላለፉም በላይ ከፍተኛ የሆነ ሽንፈትንና ውርደትን ለሙስሊሙ ጠላቶች ያጎናፀፈ ነው፡፡
የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ማስቆም የሚቻለው ለተጠየቁት ቀላልና አጭር ጥያቄዋች መልስ በመስጠት እንደሆነ የዛሬው ልዩ የሆነ ተቃውሞ ይመሰክራል፡፡ እናም በመሳሪያና በዱላ ከመተማመን ይልቅ ለተጠየቁት ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ በመስጠት ከህዝብ ጋር ተታርቆ መቀጠል ይሻላል እንላለን፡፡ ይህን ለዲኑ ዘብ፣ ለአቋሙ የፀና፣ ለሃይማኖቱ ሟች የሆነ የደሴ ሙስሊምም አላህ(ሱ.ወ) ይጠብቀው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment