Translate

Thursday, January 24, 2013

የህሊና እስረኞችን ለማነጋገር ወደ ቃሊቲ የተጓዘው የሽማግሌዎች ቡድን በተቃውሞ ተመለሰ



ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማስታወሻው ላይ እንዳሰፈረው ወደ ቃሊቲ በማምራት ርዕዮት አለሙን ያነጋገሩት ፓስተር ዳንኤል ‹‹የእስከዛሬው ተግባርህ የሚያስረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚክንፍመሆንህን ነው፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለሁም›› የሚልያልጠበቁትን መልስ በማግኘታቸው የይቅርታ አጀንዳውን ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡ የሙስሊሙማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ለፓስተር ዳንኤል እና ለፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ  ፦‹‹ያቀረባችሁትን የይቅርታ መጠየቅ ሀሳብ  በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነንም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡
ከርዕዮትና ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ያልጠበቁትን መልስ ያጘኙት  የሽማግሌዎቹ ልዑካን፤ እስክንድር ነጋን ሳያነጋግሩተመልሰዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎችውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡

ከቡድኑ አባላትመካከል ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ  ‹‹ጉዳያችሁበፍርድ ቤት እየታየ ነው፤ ስለዚህም ክሱ አሁን ባለበት ደረጃ ሊቋረጥ አይችልም፡፡ እናም ክርክራችሁን አቋርጡና ጥፋተኛ ነን በሉ፣ ከዛም ፍርድ ቤቱ ከፈረደባችሁበኋላ ‹ይቅርታ› ጠይቃችሁ እናስፈታችኋለን›› የሚል  መደራደሪያ አቅርበው ነበር፡፡
ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎች ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነኝም አንልም፣አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር ክፍላቸው መመለሳቸውንና በተጠቀሰው ዕለት እስክንድር ነጋ ዘለው   አንዱአለምአራጌን ነጥለው ማናገራቸውን ታውቋል።
ተመስገንአክሎም  የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው፣እናንተን እግረ መንገዳችንን ሰላም እንበላችሁ ብለን ነው›› ሲሏቸው፣ ለአንዱአለምም በተመሳሳይ  <የመጣነው የሙስሊም ኮሚቴዎችን ልናነጋግር ነው፤አንተን እግረ መንገድህን እናነጋግርህ ብለን> የሚል ምክንያት እንደሰጡ አመልክቷል።

ይህ ከሆነ ከ5 ቀናት ጥር 7-ቀን  2005 ዓ.ም ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን እንዳነጋገሯት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በማረሚያ ቤት ያለውን አያያዝ አስመልክቶ አስተያየቷን እንድትሰጣቸው በመጠየቅ ውይይታቸውን የጀመሩት ፓስተር ዳንኤል ከርዕዮት አለሙ ‹‹በቅድሚያ አንተ እኔን የምታየኝ እንደ አሸባሪ ነው ወይስ እንደ ፖለቲካ እስረኛ?›› የሚል አጸፋዊ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

ፓስተር ዳንኤል በበኩላቸው ጥያቄውን ለመመለስ ብዙ ደቂቃ የፈጁ ቢሆንም ሁሉንም ታራሚ በአንድ አይን ነው የምናየው የሚል የተድበሰበሰ መልስ መስጠታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመልሱ ያልተደሰተችው ርዕዮትም ‹‹ሁሉንም ታራሚ በአንድ አይን የምታይ ከሆነ እኔን ለይተህ ማነጋገር አያስፈልግህም፡፡ መንግስት አሸባሪ ናት ብሎኛል፡፡ እኔ ደግሞ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ እያልኩ ነው፤ ህሊናህ የአንዳችንን እውነት እንደተቀበለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ነገር ግን ልትናገረው ስለማትፈልግ ታድበሰብሰዋለህ፡፡ በቴሌቪዥን እየቀረብክ የኢህአዴግን ጥፋቶች ስታድበሰብስም ብዙ ጊዜ ተመልክቼሀለሁ፡፡ ስለዚህ ስለማረሚያቤቱ አያያዝ የምሰጥህ አስተያየት የለኝም፡፡›› በማለት መልሳለች፡፡
ፓስተር ዳንኤልም ይህንን መልስ ሲሰሙ ጥንካሬዋንና ድፍረቷን እንደሚያደንቁ በመግለጽ‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቆራርጦ የሚያሳየውን ነገር ተመልክተሸ እንዲህ አይነት ድምዳሜ ላይ መድረስ ትክክል አይደለም›› በማለት ሊሞግቷት ሞክረዋል።

በዚህን ጊዜ ርዕዮት፦‹ስለ ማረሚያ ቤቶች የምትሰጣቸው ምስክርነቶች ተቆራርጠው መቅረባቸውን ተቃውመህ መግለጫ ስትሰጥ አንድም ቀን አልታየም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን   ከእስከዛሬው አጠቃላይ ተግባርህ የምረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ክንፍ መሆንህን ስለሆነ  በምንም ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ ባለመሆኔ አዝናለሁ፡፡›› በማለት ወደ ክፍሏ መመለሷን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ የተነሳም ፓስተሩ ምንም አይነት የይቅርታ አጀንዳ ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡

    No comments:

    Post a Comment